Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 30, 2014

Ukraine lessons to reuinite Eritrea and Ethiopia

የዩክሬን / ስኮትላንድ መንገድ-እና ኢትዮጵያ
ዩክሬን በሶቭየት መፈራረስ ነፃ ሪፑብሊክ ከሆኑ ሐገራት አንዷነች፡፡ነጻ ብትሆንም ግን በቋንቋ ፣ሐይማኖት እና ባህል ለዩክሬናውያን ከሩሲያኖች በላይ የሚቀርባቸው የለም፡፡የዩክሬንና ሩስኪ ቋንቋዎች አማርኛ እና ትግርኛ ከሚመሳሰሉት በላይ እጅግ ተመሳሳይ ናቸው፣ባንድ ወቅት እንዲያውም ብሔሩ ሊትል ሩሲያ ሁሉ ይባል ነበር፡፡ሁለቱም ኦርቶዶክሶች ናቸው፡፡ ኢኮኖሚውን በተመለከተም ዩክሬን ነጻ ሐገር ነች ወይ ለማለት እስከሚያጠራጥር ድረስ በሩሲያ ላይ ጥገኛ” ነበረች”፡፡
ከዚች ሀገር የወጡ ክሊችኮን የመሳሰሉ ቦክሰኞች ግን አውሮፓዊ ለመሆን ሩሲያን መጥላት እና መራቅ እንዳለባቸው እና በኢኮኖሚውም ከሩሲያ መቆራረጥ እንዳለባቸው ይሰማቸው ነበር ፡፡ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ነውጥ አስነሱና የሚሆነው ሁሉ ሆነ፡፡
በሌላ በኩል በ ብሪትሽ ኢምፓየር ፀሐይ አትጠልቅም ይባልላት የነበረችው ብሪታኒያ ውስጥ የምትገኘው ስኮትላንድ ፖለቲከኞች ስኮትላንድ ካላት ከፍተኛ የነዳጅ ክምችትእና ግዛቲቱ ለብሪታኒያ ከምታበረክተው ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅዖ አንፃር ብትገነጠል ስኮትላንዳውያን ይበልጥ ተጠቃሚ እንሆናለን እያሉ ሪፈረንደም ለማካሔድ ቀን ቆርጠዋል፡፡

የስኮት ፖለቲከኞች መገንጠልን ቢቀሰቅሱም ግን አንድ ደሴት እና በርካታ ክፉና በጎ ታሪኮችን ስለሚጋሩዋቸው ኢንግላንዶች አንድም አሉታዊ ጥላቻን የሚፈጥር ቅስቀሳን አላደረጉም፤ የቅስቀሳቸው ሁሉ ማጠንጠኛ በመገንጠል ስለሚያገኙት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ ስለሚፈጠረው ተጨማሪየስራ እድል፣ስለሚጨምረው ኢንቨስተመንት፣በአውሮፓ ህብረት ስለሚኖራት ቦታ እና ተጠቃሚነት፣…..ወዘተ ነው፡፡ ምክንያቱም ስኮቶች ቢገነጠሉም ባይገነጠሉም ከኢንግላንዶች ጋር በደም፣ በታሪክ፣ በኢኮኖሚ፣… እጅግ የተሳሰሩ መሆናቸውን እና የሪፈረንደሙ ውጤት ይህንን የሚቀይር እንዳልሆነ እና መሆንም እንደሌለበት ስለሚያውቁ ነው፡፡
ወደ እኛ ሐገር ስንመለስ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ የመገንጠል አቀንቃኝ የሆኑት ኤርትራውያን የተከተሉት መንገድ የየክሬኖቹን ነበር፡፡ከኢትዮጵያ ጋር ከሚጋሩዋቸው የሺ አመታት ታሪኮች፣ሐይማኖቶች፣ባህሎች ማንነቶች …..ሁሉ ይበልጥ የሚለያዩበቸውን እያጎሉ(ለምሳሌ የ50 አመት ቅኝ መገዛትን)፣ ብዙ ጊዜ ደግሞ የበሬ ወለደ ታሪክ ሁሉ እየጨማመሩ በኤርትራውያን ዘንድ የጥላቻ እና ንቀት ስሜትን ማስረፅ እና ለመገንጠል ትግሉ ህዝቡን ከጎን ለማሰለፍ ተጠቅመውበታል፡፡ከእንጀራ ይልቅ ፓስታ መብላት እንኳን እንደ ልዩነት ማጉያ ሆኖ በፕሬዚደንት ደረጃ ባለ ሰው ትንታኔ ይሰጥበት የነበረ መሆኑ ምን ያህል ልዩነትን ለማጉላት እንደሚጥሩ ማሳያ ነው፡፡ከብሔርም አማራ ተለያቶ በኤርትራውያን ዘንድ እንዲጠላ እንደተደረገ፣ ለኢትዮጵያ ትግሬዎች ንቀትን ለማስረፅ እንደተደከመ፣ ሌላው ቀርቶ ጥላቻው ከሁለቱም ወገን እንዲመጣ በ1977 ድርቅ ለትግራይ የተላከ ርዳታን በሻዕቢያ ነፃ ግዛት እንዳያልፍ መደረጉ፣ በባድመ ጦርነት ወቅት ሆን ተብሎ ህፃናት የሚማሩበት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት (አይደር)መደብደቡ ….ወዘተ ስር የሰደደ ጥላቻ ማስረፅ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ምን ያህል እንደተሰራበት ማሳያዎች ናቸው፡፡


ነገር ግን ፓርቲው(ድርጅቱ)ኤርትራውያን መገንጠሉንም ሆነ አብሮ መኖሩን በተመለከተ የተሟላ እና ትክክለኛ መረጃ ኖሮት የሚበጀውን ራሱ እንዲመርጥ ከማድረግ ይልቅ ለፖለቲካ ስኬት ሲባል ህዝቡ ከወንድመቹ ጋር እንዲቆራረጥ ፣ የተዛባ አመለካከት እንዲኖረው፣ በኢኮኖሚ ሊኖር የሚችለው የጋራ ተጠቃሚነት እንዲቀር ካደረገ ፓርቲው ለህዝቡ ሳይሆን ለራሱ ስልጣን ሲል ህዝቡን ዘርፈብዙ መስዋትነቶችን እያሰከፈለ ነው ማለት ነው፡፡
የሚያሳዝነው ግን ይህ የ ኤርትራውያን ፖለቲከኞች አካሔድ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ሁሉ ተመራጭ መንገድ መሆኑ ነው፡፡ሕወሐት ሲጀምር አካሔዱ እንደዚህ ነበር፡፡ኦነግ አካሔዱ እንደዚሁ ነው፡፡የኦነግን ለየት የሚያደርገው ብዙሐንን የሚወክል ሆኖ እያለ የአናሳ ጥያቄን ማንሳቱ ና ይህንኑ አስተሳሰብ ማስረጹ ነው፡፡የፖለቲካ አስተሳሰቡ ተሳክቶ ኦሮሚያ ነፃ ሐገር ብትሆን በክልሉ ያሉትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማሮች የኦሮሚያ ዜጎች እንደሚሆኑና እነሱን እኩል ማስተዳደር እንዳለበት፣አማራ ክልልም ጎረቤቱ እንደሚሆን እና ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ እና የደም ትስስሩ እንዳለ ያሰበበት አይመስልም፡፡


የአሁኖቹ ተቃዋሚዎችም አንዳንዴ ፖለቲካዊ ድጋፍን ለማግኘት ጥላቻን ማስረፅ እንደተመራጭ አካሔድ ይከተላሉ፡፡ምንም አይነት የፖለቲካ አላማ ይኑረን የህዝብን ታረካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለፈተና የሚያቀርብ ፖለቲካዊ አካሔድ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህልነቱ ልናስቀረው ይገባል፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials