Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, May 29, 2014

በደብረማርቆስ ከተማ ከ400 በላይ ቤቶች በዶዘር እየፈረሱ ነው morethan 400 houses destroyed

በደብረማርቆስ ከተማ ከ400 በላይ ቤቶች በዶዘር እየፈረሱ ነው


በዛሬው ዕለት ደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶች በዶዘር እየፈረሱ እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡ በተለይ ቦሌ እየተባለ የሚጠራው ሰፈር የሚገኙ ቤቶች በዛሬው ዕለት እየፈረሰ እንደሚገኝና ህዝብ ይቃወማል በሚል ቡችሌ፣ ሚሊሻ፣ ህዝባዊና ልዩ ፖሊስ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
(ደብረማርቆስ ከተማ)
ይህ ቦሌ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ትናንት ሊፈርስ የነበረ ቢሆንም በግንቦት 20 ምክንያት እንደታለፈ ተገልጾአል፡፡
ደብረ ማርቆስ ውስጥ ቤቶችን ማፍረስ የተጀመረው ግንቦት 18ና 19/2006 ዓ.ም ሲሆን ቀበሌ አራት (4) በተለይም ሞንቃ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር 400 ያህል ቤቶች እንደፈረሱ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ቦሌ የተባለው ሰፈር እንዳይፈርስ በተደረገበት በትናንትናው ቀን ከ23 አመት በላይ ግብር ሲከፈልበት የኖረ የአንድ ግለሰብ ቤት መፍረሱም ታውቋል፡፡ አፍራሽ ግብረሃይሉ የቤቱን ጣራ ካፈረሰ በኋላ ግለሰቡ ለ23 ዓመት ግብር ሲከፍልበት የነበረ መሆኑን በመገለጹ ግድግዳው ብቻ እንደቆመ ወደ አቤቱታ መመራቱን ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ደብረ ማርቆስ ውስጥ አብዛኛዎቹ ቤቶች ከ1997 ጀምሮ የተሰሩ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ቤቶች አርሶ አደሮች
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30779

No comments:

Post a Comment

wanted officials