Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 16, 2014

በወለጋ ዩኒቨርስቲ ፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ተማሪዎች መገደላቸው ተሰማ

በወለጋ ዩኒቨርስቲ ፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ተማሪዎች መገደላቸው ተሰማ
May 15/2014
ግንቦት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊስ በተማሪዎቹ ላይ በወሰደው ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ 3 ተማሪዎች መገደላቸውን የኢሳት የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንና የፌደራል ፖሊሶች ተማሪዎቹ የመጀመሪያ እርዳታ እንዳያገኙ መከልከላቸውን ተከትሎ በሃኪሞችና በፖሊስ አዛዦች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደበር ምንጮች አክለው ገልጸዋል። የሆስፒታሉ ሰራተኞች በአቋማቸው በመጽናታቸው ተማሪዎች ህክምና ለማግኘት መቻላቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች መታሰራቸውን እንዲሁም በዛሬው እለት ፖሊሶች ግቢ ውስጥ የቀሩ አንዳንድ ተማሪዎች ከግቢ እንዳይወጡ ከልክለው ከፍተኛ ጥበቃ ሲያደርጉ ውለዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ እየወሰደ ያለው የሃይል እርምጃ የአካባቢውን ማህበረሰብ እያስቆጣና ምናልባትም ለተቃውሞ ወደ አደባባይ እንዲወጣ ሊያደርገው ይችላል በማለት አስተያየታቸውን ተናግረዋል።
መንግስት እስካሁን ድረስ በግጭቱ ዙሪያ የሰጠው መግለጫ የለም፣ የአካባቢውን መስተዳድርና የዩኒቨርስቲውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራም አልተሳካም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም በለንደን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውመውታል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials