Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, May 18, 2014

የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረውና ባለትዳሮችን የገደለው ከማእከላዊ ማምለጡ ተሰማ

የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረውና ባለትዳሮችን የገደለው ከማእከላዊ ማምለጡ ተሰማ ። (SEE PHOTO)

የሕግ የበላይነት ባሌለበት አገር ባለጊዜዎች ይሾልኩበታል ..ንፁሃን ይጠመዱበታል.... ይህ ወንጀለኛ ግለሰብ አንድም የግድያ ተልእኮ ተሰቶት ዘምቷል አሊያም ባለጊዜነቱን ተጠቅሞ ባለጊዜዎች እንዲያመልጥ አድርገውታል::ወገኖቻችን በአመለካከታቸው ብቻ በጨለማ እስር ቤት በሚዳክሩበት ማእከላዊ ተኖ መውጣት መንግስታዊ ወንጀለኝነትን አግጥጦ አውጥቷል:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረውና ባለትዳሮችን የገደለው ከማእከላዊ ማምለጡ ተሰማ ። 

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ነጭ ጋዝ መሸጫ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የካቲት 24 ቀን 2006 ገዳይ እና ሟች ባል እና ሚስት በሚኖሩበት የቀበሌ ቤት የማዕድ ቤት ይገባኛል ምክንያት በመከላከያ ሰራዊት አባልነቱ ተሰጥቶት በነበረ EC 40-00 መሳሪያ በሟች አባወራው እና በባለቤታቸው ላይ 30 ጥይት በመተኮስ ለሞት ያበቃው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ ባለበት ሰዓት ማምለጡ ተሰምቷል

ድሬቲዩብ ያነጋገራቸው የፖሊስ አካላት እንዳሉት ከሆነ ከሚመለከተው አካል ግለሰቡ ስለመምለጡ የተሰጠ ኦፊሴላዊ ደብዳቤ ባይቀርብም ግለሰቡ ማምለጡን መስማታቸውን ገልጸዋል፡፡

ተጠርጣሪው በማእከላዊ እስር ቤት ይገኝ እንደነበረ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራውን እያካሄደ እንደነበር የተቀሱት የፖሊስ አካላቱ ከተለያዩ አካላት እስረኛው ማምለጡን መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡ ግድያውን የፈጸመው የመቶ አለቃ ጌትዬ ፤ በመከላከያ ሰራዊት በሰሜን ኮር 31ኛ ክፍለጦር አባል ነበረ :: www.DireTube.com

Image

No comments:

Post a Comment

wanted officials