አቶ ሽመልስ ከማል በኢትዮጵያ የሽብር ህግ በማዘጋጀት እና አሁን በእስር ላይ የሚገኙትን የሙስሊም ኮሚቴዎች፣ ጋዘጠኞች እና ሰላማዊ ታጋዮችን በህግ ሽፋን በማሳሰር ይታወቃል። አርአያ ተስፋማርያም እንደገለጸው ከሆነ ደግሞ ይህ ከፍተኛ የኢህ አዴግ ባለስልጣን ምግባር የጎደለው ባለጌ ሰው መሆኑን አጋልጧል። እንደአርአያ ጥቆማ ሽመልስ ከማል ከ5 ሴቶች አስር ልጆች ማስወለዱን ወይም መወስለቱን ገልጿል። በቀጥታ ወደ ጥቆማው ሙሉ ቃል ንዲህ ይላል።የኮሚኒኬሽን ሚ/ር ባለስልጣን የሆነው ሽመልስ ከማል ሁለት ልጅ የወለደችለት ሚስቱን በቅርቡ በመፍታት ከቤት እንዳባረራት ታማኝ የቅርብ ምንጮች አረጋግጠዋል። ከኢትዮጵያ ሱማሌና የመን ወላጆች የምትወለደው እንዲሁም ሁለት ልጆች የወለደላት ሽመልስ በሴቶች እህቶቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው ግፍ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ተብሏል። ይህቺ ሴት አምስተኛ ሚስቱ ስትሆን ከአምስቱም ሴቶች ሁለት- ሁለት ልጅ ባጠቃላይ 10 ልጅ ሽመልስ ከማል እንደወለደ ማረጋገጥ ተችሏል። አራተኛ የነበረችው ሚስቱ የቅርብ ጓደኛው የሆነው ጋዜጠኛ ተፈሪ መኰንን ታናሽ እህት ስትሆን ሁለት ልጅ ካስወለዳት በኋላ ከቤቱ አውጥቶ ከነልጆችዋ እንደጣላት ታውቋል።
ሽመልስ ከማል ከ5 ሴቶች ለወለዳቸው 10 ልጆች ምንም አይነት የማሳደጊያ እገዛ እንደማያደርግና እንዳውም መብታቸውን እየገፈፈ በግፍ እንደሚያባርራቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። ..ሽመልስ ከማል ከሴት እንዳልተፈጠረ፣ ሴት እህቶች እንደሌሉት ይህን አይነት ጭካኔ የተሞላበት ነውረኛ ድርጊት በተለያዩ እንስቶች ላይ መፈፀሙ ከአሳፋሪነቱ ባሻገር ይህቺ አገር በምን አይነት ጭራቆች እንደምትመራ ፍንትው አድርጐ ያሳያል። ሽመልስ ከማል የሚዋሸው፣ ንፁሃንን የሚወነጅለው፣ የሚቀባጥረው፣ ..ከምንም ተነስቶ አይደለም፤ እንዲህ አይነት ርካሽ ተግባር ባለው ስርአት መፈፀም ስለሚችል ነው።

No comments:
Post a Comment