Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 24, 2014

ኢሉሚናቲ በኢትዮጵያ፡ ተረት እና እውነት

ኢሉሚናቲ በኢትዮጵያ፡ ተረት እና እውነት



በግደይ ገብረኪዳን

በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ስለ ኢሉሚናቲ ማውራት ከአመት በፊት ከነበረው ሁኔታ እንኳ በእጅጉ ተቀይሯል፡፡ አሁን ቢያንስ ስሙን እንኳ የሚያውቀው ሰው ቁጥር እጅግ በዝቷል፡፡ ሆኖም ግን አሁንም ስለ ኢሉሚናቲ ምንነት የጠራ ወይም በነባራዊው የዓለም ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ መድረክ ዙርያ ያለውን ወይም የሌለውን ሚና በቅጡ መረዳት ላይ አልተደረሰም፡፡ በዚህ ፅሁፍ በተለይ በሃገራችን ላይ አትኩሮት በማድረግ ትክክለኛ የምርምር መርህ ተጠቅመን ስውሮቹን እጆች ለመዳበስ እንሞክራለን፡፡

 
ኢሉሚናቲ ምንድን ነው?

አንዳንዶች የኢሉሚናቲ ብቸኛ ፈጣሪ አዳም ዉሻፕት ነው፣ ኢሉሚናቲም ገናናነትን ለማግኘትና ለመጥፋት የ12 ዓመታት እድሜ ብቻ ነበረው ብለው ቢናገሩም አብዛኞቹ የባእድ ሚስጥራቱን የሚያቁ አባሎች እንደሚፅፉት ግን የባቫርያ ኢሉሚናቲ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ወንድማማችነት መገለጫና መሰረቱም እስከ መካከለኛው ዘመን የነበሩት ናይትስ ቴምፕላርስ (የቤተመቅደሱ ባለሟሎች) ድረስ የሚሄድ እንደሆነ ይፅፋሉ፡፡
ማንሊ ፒ. ሃል 33 መዓርግ የደረሰ ሰፊ ተቀባይነት ያለው የራሳቸው የፍሪሜሶኖች ፀሃፊ “Masonic Orders of Fraternity” በሚል ፅሁፉ ለዘመናት ሳይታይ ለለውጥ ሲሰራ የነበረ “የማይታየው ግዛት” ስለሚለው ነገር ያብራራል፡፡ በታሪክ በተለያዩ አጋጣሚዎች የተለያየ ስም በያዙ የተለያዩ ድርጅቶች አንዳንዴ ይታያል ይላል፡፡ እሱ እንደሚለው እኚህ ቡድኖች የማይታወቅ ግን ታላቅ ተፅእኖ በማህበረሰቡ ላይ ፈጥረዋል ይላል፡፡ ይህም ቀጣዩን ትውልድ ለመቅረፅ የትምህርት ስርአቱን በመቀየርም ሳይቀር ይላል፡፡ በዚህ ፅሁፉ ሃል በ17ኛው እና በ18ኛ ክ/ዘመን የባቫርያ ኢሉሚናቲ በንቃት በሚንቀሳቀስበት ወቅት የሚስጥር ማህበራትን ስራ በተመለከተ “ዝምታና” የመረጃ እጥት እንደነበር ይገልፃል፡፡ በዚህ ግዜ ነው የሚስጥር ማህበራት አብዮቶችን በማስነሳት፣ ዘውዳዊና ሃይማኖታዊ ስልጣናትን በማናጋት ስራና የባንክ ስርአቱን በመቆጣጠር እንቅስቃሴዎች ተወጥረው የነበሩት፡፡ የባቫርያ ኢሉሚናቲ ሃል የሚለው የማይታየው ግዛት አካል ነበር? ዛሬስ እየተንቀሳቀሰ ነው ወይስ ጠፍቷል? መጀመርያ አዳም ዉሻፕትንና አሳፋሪ የሚስጥር ማህበሩን እንመለከታለን፡፡
በዚህ ዙርያ የበለጠ ለመረዳት የሚከተለውን ፅሁፍ ያንብቡ፡ ኢሉሚናቲ፡ አነሳሱ የሚስጥር ማህበራቱ እና ተፅእኖው

ኢሉሚናቲ እና የዓለም አቀፋዊነት እና ፅንፈኝነት ፖለቲካ ታሪክ
የኢሉሚናቲ ብዙም ስውር ያልሆኑ እጆች (እንዲህ ግዙፍ ሴራ መቶ በመቶ መሰወር ይከብዳልና) በታሪክ አጋጣሚ ተደጋግመው ተከስተዋል፤ ለአብነት ያህል የመጀመርያውን የፈረንሳይ አብዮትን እንመልከት፡፡
በ1789 የደረሰው የፈረንሳይ ዘውድ በሃይል መገልበጥ ለብዙዎች የሚያመላክተው ከባህላዊ ተቋማቱ ይልቅ የአብዮተኞቹ ጃኮቢኒዝምና ኢሉሚኒዝም የበላይነት ማግኘትን ነው፡፡ በወቅቱም የታወጀው የሰብአዊ መብቶች እወጃ ሰነዱ ሜሶናዊና ኢሉሚናቲ ሃሳቦችን ወደ ፈረንሳይ መንግስት ስርአት ያስገባ ነበር፡፡ የሃገሪቱ አዲሱ መፈክሯ የሆነው፡ ነፃነት፣ እኩልነት እና ወንድማማችነት አስቀድሞ ለዘመናት በፈረንሳይ ፍሪሜሶን ሊጆች ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ነው፡፡

የአብዮቱ መታሰብያ በሚለው ፅሁፍ ላይ እንዳየነው ዋናው የዶክመንቱ ቅጂ ብዙ የሚስጥር ማህበሩን ምልክቶች የያዘ እንደሆነ አይተናል፡፡ መጀመርያ ከላይ ሶስት መአዝን ውስጥ ያለው የሚያበራው የሆሩስ ዓይንን እናያለን፡፡ 
ከአርእስቱ ስር እራሱን የሚበላው የሂወት ኡደትን ያለማክታል የሚሉት የኦሮቦሩስ እባብ ምስል ይገኛል፡፡ ይህ ከአልኬሚ፣ ግኖስቲሳውያን እና ኸርመቲዝም ሁሉም ከሜሶን ትምህርቶች ኮር የሆኑት ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ከኦሮቦሮሱ ስር ቀዩ የፍሪግያ ኮፍያ ጦር ላይ ተሰክቶ ይታያል፡፡ ይህ በወቅቱ በአለም ዙርያ የአብዮቶች ምልክት የነበረ ነው፡፡ የአዋጁ ክፈፍ የታጠረው በሜሶናዊ ጥንዶቹ ቋሚ አምዶች ነው፡፡ እነዚህ ሁለት አምዶች የሜሶን ቀንደኛ ምልክት ናቸው፡፡ ሌሎችም አሉበት፡፡
ፒራሚዱ እና ዓይኑ ምልክት 
ይህ የሚታየው የአሜሪካን ገንዘብ አንድ ዶላር ሲሆን፣ ገንዘቡ ላይ ከቀኝ በኩል የሚታየው ከ1935 ዓ.ም ጀምሮ የተጨመረው ከአሜሪካ ሃገር ማህተም በስተጀርባ የነበረ ነው፡፡ ማህተም የጀርባ ቅርፅ እንዴት ሊኖረው እንደቻለ የቀረፁት ያውቁታል፡፡ ይህ አርማ የአዲስ የአለም ስርአትና የኢሉሚናቲ የሀረም/ፒራሚድ ማህተም የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ማህተም የሴራው እቅድ የንድፋዊ መግለጫ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከላይ "Annuit Coeptis—ጅማሪያችንን መርቆታል” ሲል ከስር ደግሞ፣ "Novus Ordo Seclorum—የዘመናቱ አዲስ ጅማሮ” ይላል፡፡ ከሀረሙ ጫፍ ያለችው ዓይን የሆሩስ--የፀሃይ አምላክ ሁሉን ተመልካች ዓይን የሚሉት ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን መልአክ /ሉሲፈር የነበረውን ነው፡፡ በባእድ አምልኮ ዶክትሪን መሰረት እንደሚታመነው በመንፈስ እና ቁስ አካል ውህደት (ሀረሙ ከድንጋይ፣ አለትና አፈር የተሰራው የማያውቀውን (unconscious) አካል ሲወክል ከላይ የምታበራው ዓይን ያለባት ደግሞ ቁሳዊ ባልሆነ አካል --ብርሃን ወይም መንፈስ-- የሚወክል ሲሆን አዋቂው (conscious) አካል ነው፡፡ ከስር ጀምሮ ወደ ላይ የደረሰም አዲስ ሁኖ ይፈጠራል፡፡ ሀረሙ የሚያመላክተው ከሚስጥር ማህበራቱ ገብቶ ሚስጥር የሚነገረው ሰው የሚያልፍባቸውን የእድገት መአርጎች ነው፡፡ ሁሉንም ፈተናዎች ያለፈ ወደመጨረሻው መንፈሳዊ አካል ይወሃዳል፡፡ ዶላር ሌሎችም ብዙ ምልክቶች በስውር አሉበት፡፡
የአሜሪካን ማህተም የሰሩት ሰዎች ይህን አርማ በጀርባው ሲቀርፁ ማህተም የጀርባ ምስል ለምን አስፈለገው ሊያሥብል ይችላል ግዚያቸውን ጠብቀው ኢኮኖሚዊ ድቀት ካስገኙ በውኋላ ይፋ አደረጉት፡፡
“ሶስት-መዓዝን (ትሪያንግ) በኢሉሚናቲ የተለያዩ መገለጫዎች፡-  በሮዚክሩሽያኖችም ሆነ በሜሶኖች ወይም በመተተኞች፣ ኮከብ ቆጣሪዎች እና ጥቁር አስማት /ጠቋዮች እና ሌሎችም ኢሉሚናቲ ተከታዮች ዘንድ በበዓላት አከባበር ግዝያት ወሳኝ ስፍራ ይይዛል፡፡

ሴጣናውያንና መተተኞች፣ ጥንዱ ሶስት መዓዝን፣ የሰለሞን ማህተም (ሄክሳግራም) የሚባለው ሰፊ ቦታ አለው፡፡ ይህ ማህተም በተጨማሪም የአይሁዶች “ማገን ዴቪድ” ይባላል፣ ይህ ኮከብ ከሁለት ትሪያግሎች የተሰራ ነው፡፡ አንዱ ትሪያግል ወደ ላይ የሾጠጠው ስጋ ወይም ቁሳዊውን አካልና የወንድ የመራባት ተግባርን ይወክላል፤ ወደ ታች የሚጠቁመው ትሪያግል የሴት ወሲባዊነትንና መንፈሳዊ አለምን ይወክላል፡፡ ስለዚህም እዚህ የወንዴውና የሴት ትሪያግሎች ተጠላልፈው እናያለን፡፡ ይህ ወሲባዊ ውህደትን ይወክላል፡፡ በተጨማሪም የተቃራኒዎች መጣጣምን /መታረቅን፣ ዪን እና ያንግ (በሩቅ ምስራቆቹ)፣ እግዚአብሄርና ሴጣንን ያሳያል፡፡ ይህ መገዳደር የበዛበት የምልክቱ ትርጉም ግልፅ ሆኗል፡፡” ቴክሴ ማርስ “Codex Magica” (361)
ይበልጥ ለማንበብ የሚከተለውን ፅሁፍ ያንብቡ፡ ፒራሚዱ እና ዓይኑ ምልክት

ኢሉሚናቲ በኢትዮጵያ፡ ተረት እና እውነት
መጀመርያ ደረጃ እስካሁን ባለኝ ውሱን መረጃ መሰረት በቀጥታ የኢሉሚናቲ ተፅእኖ ወይም ሙሉ ቁጥጥር የለም፡፡ ሆኖም ግን በተዘዋዋሪ ዓለሙን ሁሉ እንደሚቆጣጠሩት ኢትዮጵያም ከዚህ ውጪ አይደለችም፡፡ ይህም ከኢትዮጵያ አብዮታዊ ንቅናቄዎች ጋር ይበልጡኑ ይተሳሰራል፡፡ ዘውዳዊ አገዛዙ ከዚህ ቀጥተኛ ያልሆነ የርእዮተ ዓለም የሚያመጣው እስር ነፃ ነበር፡፡
አሁን ከስር የማቀርብላቹ ምልክቶች በእርግጥም ኢሉሚናቲ ኢትዮጵያን ሲገዛ ነበር ብሎ አስረግጦ የሚያሳይ ማስረጃ አይደለም፡፡ ገፋ ቢል ሊጠቁመን የሚችለው የኢሉሚናቲ ስውር እጆች ከበስተጀርባ እንደነበሩ ነው፡፡ ለዚህም ዋና ምክንያት የሚሆነው በመንግስት ደረጃ ቅድሚያ ለብሄራዊ ፖሊሲዎች የሚሰጥ በመሆኑ ነው፤ ኢሉሚናቲ ደግሞ በተቻለ ፍጥነት ዓለም አቀፋዊነትን እንዲከተሉ ይፈልጋል፡፡ 


የላሊበላ ስልጣኔ እና የቴምፕላሮች እጅ
ቴምፕላሮች እንተዋወቃቸው

በ1118 ዓ.ም የመስቀል ጦርነት በክርስቲያኖቹ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ወደ እየሩሳሌም የሚደረገውን መንፈሳዊ ጉዞ ለመጠበቅ በሚል ያሸነፉት በሁጎ ደ ፓይኔ እና ጎድፈሮይ ደ ሰይንት-ኦሜር መሪነት ማህበር መሰረቱ፡፡ በእስራኤል ዘውዱን የተረከበው ባልድዊን ሁለተኛ ለማህበሩ የሰለሞን ቤተ መቅደስ በነበረበት አካባቢ ቤት ሰጣቸው ስያሜአቸውንም --የቤተ-መቅደሱ ባለሟሎች - Knights Templar-- ከዛው አገኙ፡፡ በ1128 ዓ.ም በትሮይ በተደረገው ስብሰባ ማህበሩ በሰይንት በርናንድ በተቀረፁ ደንቦች መሰረት የቤተ-መቅደሱ ባለሟሎች እራሳቸውን በድህነት፣ በድንግልናና በታዛዥነት ለመያዝ ቃለ-መሀላ ፈፅመው እውቅና ተሰጣቸው፡፡
መተዳደርያቸው ምፅዋት በሚደረግላቸው ላይ እንደመሆኑ ይህ ደግሞ እጅግ እየበዛ በመሄዱ በድህነት ለመኖር የገቡትን ቃል አስረሳቸው፣ በ12ኛው ክ/ዘመን መጨረሻም በመላው አውሮፓ የተስፋፉ እጅግ ሃያል እና ሃብታም ማህበር እንዲሆኑ አደረጋቸው፡፡ ከዚህም ሌላ ከአረቦቹ ገዳዮቹ ጋርና ከደማስቆ ጋር በስምምነት ይሰሩ ነበር፤ በዚህም የእውነት መመርያቸውንና እምነታቸውን ይከተሉ ነበር ማለት ከባድ ነው፡፡ በ13ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ በቀሳውስቱ ብቻ ሳይሆን በተራው ህዝብም ጭምር በክህደት መጠርጠር ጀመሩ፡፡ የሰው መመኘታቸው፣ ግድ የለሽነታቸው፣ ለቅንጦት ያላቸው ፍቅርና ስስታምነታቸው በግልፅ የህዝብ ትዝብት ውስጥ ገብቶ ነበር፡፡ ምግባራቸው ለተረትም ተርፎ፡- “መጠጣትስ እንደ ቴፕላሮች ነው” ይባል ነበር፡፡
የቴምፕላሮቹ ወዳጅ የነበረው የፈረንሳዩ ንጉስ ፊሊፔ ሌ ቤል ለጳጳስ ክለመንት አምስተኛ ጉዳዩን እንዲያጣራ መልእክ ይልክለት ነበር፤ ጳጳሱ ግን አስቀድሞ መሪያቸውን ጃኲ ደ ሞላይን ለጥያቄ ጠርቶትም ነበር፡፡ የፈረንሳዩ ንጉስ ጉዳዩን በራሱ እጅ በማድረግ ጥቅምት 13፣ 1307እ.አ.አ ቴምፕላሮችን በፈረንሳይ ማጣራትና መክሰስ እንዲጀመር አስደረገ፤ የተጠረጠሩባቸው ጉዳዮች፡
  1.    በማህበሩ የአባልነት መግቢያ ስነ ስርአት ላይ መስቀሉን መሳደብ፣ ክርስቶስን መካድ እና አፀያፊ የነውር ምግባሮች ማድረጋቸው፤
  2.  እውነተኛው አምላክ ነው የሚሉትን ምስልን ማክበር፤
  3.  በቅዳሴ ግዜ ለስርአተ ቁርባኑ የሚደረገው ፀሎት ማስቀረት፤
  4.  ተራዎቹ አለቆች ሃጥያት የማስተሰረይ ስልጣን አለን ማለት፤
   5.    ጋጠወጥ የሆኑ ጥፋቶችን መፍቀድ፡፡
ሙሉ ፅሁፉን ይመልከቱ፡ ቴምፕላሮች --THE TEMPLARS

ላሊበላስ?
ላሊበላ በ12ኛው ክ/ዘ መጨረሻ እና በ13ኛው ክ/ዘ መጀመርያ ኢትዮጵያን የገዛ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ፃድቅ የሆነ ንጉስ ነበር፡፡ ስሙ የተገኘው ከወላጅ እናቱ ሲሆን መነሻውም በጨቅላነቱ ከተኛበት ንቦች በዙርያው አርፈው ከበውት ስለተገኘ ለወደፊቱ ንጉስ እንደሚሆን ትንቢት ተደርጎ ስለተወሰደ ይህን ለመጠቆም የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡
በንግስና ዘመኑ እየሩሳሌም በአረቦቹ መሪ ሳላዲን ተይዛ ስለነበረች ለመንፈሳዊ ተጓዦች የሷ ምትክ የሚሆን ለማነፅ ያስጀመራቸው ከተራራ ተፈልፍለው የሚወቀሩ አብያተ ክርስትያናቱ እስካሁን የታላቅነቱ ህያው ምስክሮች ሁነው ይታያሉ፡፡  
አንዳንዶች ታድያ ላሊበላ ይህን ሊሰራ የቻለው እየሩሳሌምን ጎብኝቶ ስለነበረ ከቴምፕላሮቹ ጋር በፈጠረው ትውውቅ ብሎም ይዟቸውም በመምጣት በነሱ ድጋፍ የሰራው ነው ይላሉ፡፡ ይህን የሚሉትም አንዳድ ምልክቶችን ከአብያተ ክርስትያናቱ በመውሰድ ከቴምፕላሮቹ የተዋሰው ነው በማለት ነው፡፡
ሆኖም ግን ይህን ውድቅ የሚያደርጉ ማስረጃዎች አሉ፡፡ አንድ የቤተክርስትያኑ አወቃቀር ወይን ስነ ህንፃ ጥበብ በምድረ አውሮፓ በቴምፕላሮቹ ረዣዥም ህንፃዎች ከምድር ወደላይ ሲገነቡ በላሊበላ ግን ከዚህ በተቃራኒ ወደ ስር ተፈልፍለው ነበር የታነፁት፡፡ ይህ ሃሳብ ከላሊበላ ውጭ የትም ዓለም የለም፡፡
ምልክቶቹስ ታድያ? የተባለ እንደሆን ቴምፕላሮች ከመፈጠራቸው ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት በአክሱም ስልጣኔም የነበሩ መሆናቸውን ልብ ስንል፡ እንግዲህ ቴምፕላሮቹ ጥንታዊ ሚስጥራቱን ወስደው የሚያጣምሙ መሆናቸወን እንድንገነዘብ ያደርገናል፡፡  ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን የቴምፕላሮች ዋና ምልክት የሆነው መስቀላቸው ነው፡፡

ላሊበላ ይህ ምልክት ከመከተቡ በፊት በአክሱማዊው ንጉስ ካሌብ መቃብር ላይ ማየት ይቻላል፡
ስለዚህ ሌሎቹም የቴምፕላር ብለን የምናውቃቸው ምልክቶች ሌላ ትርጉም ወይም መልእክት እና ዓላማ ይዘው ቀድሞኑ በጥንታዊ ኢትዮጵያ ስልጣኔ እንደነበሩ መገመት ይቻላል፡፡ 


ቀዳማዊ ኃይለስላሴ እና ኢሉሚናቲ
አፄውንም ቢሆን ከሚስጥር ማህበራቱ ጋር ለማገናኘት የሚቀርበው ማስረጃ ውሃ አይቋጥርም፡፡ አንዳንድ አፄው ፈጣሪ ናቸው የሚሉ ራስታዎች እጃቸውን ቁልቁል በተደፋ ሶስት መአዝን ሲይዙ ሲያይዋቸው እንደ ሚስጥራዊ ምልክት እንደተጠቀሙ አድርገው ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ ሆኖም ግን ይህ የእጅ አያያዝ በኢትዮጵያ የተለመደ መሆኑን ስናስብ የአጋጣሚ ጉዳይ ወደ መሆኑ እንጂ የሚስጥር ምልክት ሁኖ አይታየንም፡፡
ከዚህ ይልቅ የሚያሳስበን ሃይለስላሴ አባል የሆኑባቸው ሜሶናዊ ማህበሮች ዝርዝር ነው፡-
Chief Commander of the Order of the Star of Ethiopia - 1909
Grand Cordon of the Order of Solomon - 1930
Riband of the Three Military Orders Of Christ
Knight of the Order of the Most Holy Annunciation - 1928
Order of the Elephant - 1954
Order of the Gold Lion of the House of Nassau of Luxembourg - 1924
Collar of the Order of the Seraphim - 1954
Maha Chakri - 1954
Order of Suvorov 1st class of USSR - 1959
Collar of the Order of Muhammad Ali of Egypt - 1930
Grand Cross of the Legion d'Honneur - 1924
Chief Commander of the Legion of Merit - 1945
Grand Collar of the Order of Pahlavi - 1964
Collar of the Order of the Aztec Eagle - 1954
Royal Victorian Chain (RVC) - 1930
Knight of the Order of the Garter (KG) - 1954
Knight Grand Cross of the Order of the Bath (GCB) - 1924
Knight Grand Cross of the Order of St Michael and St George (GCMG) - 1917
Knight Grand Cross of the Royal Victorian Order (GCVO) - 1924
Collar of the Order of the Chrysanthemum-1956 (Grand Cordon-1930)
Order of St James of the Sword of Portugal
Order of the Liberator San Martin of Argentina
Order of the Nile of Egypt
Order of Pius IX of the Vatican - 1970
Order of Idris I of Libya
Order of Independence of Tunisia
Order of Hussein ibn Ali of the Jordan
Order of Muhammad of Morocco
Chain of Honor of the Sudan
Grand Order of the Hashemites of Iraq
Order of the Crown of Italy - 1917
Order of Leopold (Belgium) - 1924
Order of Saints Maurice and Lazarus - 1924
Order of the Tower and Sword of Portugal - 1925
Knight Grand Cross of the Order of William - 1954
Knight Grand Cross of the Order of the Netherlands Lion - 1930
Order of the White Eagle of Poland - 1930
Collar of the Order of St Olav of Norway - 1949
Collar of the Order of Charles III of Spain
Collar of the Order of the White Rose of Finland
Grand Cross of the National Order of Vietnam- 1958
Order of Truth of Burma - 1958
Collar of the Order of the Southern Cross of Brazil - 1958
Collar of the Order of the Leopard of Zaire
Order of the Lion of Senegal
Order of the Lion of Malawi
Order of Valor of Cameroon
Order of the Sun of Peru
Collar of the Order of the Bust of the Liberator Simon Bolivar of Venezuela
Order of the Condor of the Andes of Bolivia
Special Grade of the Order of the Propitious Clouds of China
Order of Oummaya of Syria
Order of Mono of Togo
Order of Congolese Merit of the Republic of the Congo
Order of the Leopard of Somalia - 1960
Order of the Equatorial Star of Gabon
Order of the Federal Republic of Nigeria
Order of the Source of the Nile of Uganda
Order of the Eagle of Zambia
Special Class of the Order of Merit of the Federal Republic of Germany - 1954
Collar of the Order of the Republic of Italy - 1955
National orders of Lebanon, Chile, Central Africa,Upper Volta, Chad, Benin, Mali, Madagascar, Mauritania, Guinea and Niger.
Collar of the National Order of Honor and Merit of Haiti - 1966
Knight Grand Band of the Order of the Pioneers of Liberia
Grand Chief of the Order of the Golden Heart of Kenya
Grand Star of the Decoration of Honor for Merit of Austria - 1954
Star of the Republic of Indonesia, 1st Class - 1958
Raja of the Order of Sikatuna of the Philippines
Commander of the Order of the Shield and Spears of Uganda - 1964
Order of the Yugoslavian Grand Star - 1954
Order of Pakistan, 1st Class - 1958
Order of the State Crown of Malaysia - 1968
Order of King Abdul Aziz, 1st Class, of Saudi Arabia
Order of the Star of Ghana - 1970
Banner of the People's Republic of Hungary, 1st Class with Diamonds - 1964
Military Medal of France - 1954
Honorary citizen of the Socialist Federal Republic of Yugoslavia - 1972
Honorary citizen of Belgrade – 1954

ከነዚህ ውስጥ ናይትስ ኦፍ ጋርተር የአውሮፓ ነገስታት ማህበርን እንየው፡፡ የአውሮፓ ነገስታት የዘር ሃረግ የሚገኘው ከፍሎረንስ ነገስታት ሲሆም የብላክ ኖቢሊቲ ወይም ጥቁር መሳፍንትበመባል ይታወቃሉ፡፡ ይበልጥ ለመረዳት የሚከተለው፡ ጥቁር መሳፍነት” – "Black Nobility" ያንብቡ፡፡ እኚህ ባላባቶች ከኢሉሚናቲ በስተጃርባ እንዳሉበትና አሁንም በዘመናዊው ዓለም ፖለቲካም ንቁ ተሳታፊ ለመሆናቸው ጥያቄ የለውም፡፡
ከስር ሃይለስላሴ ለናይት ኦፍ ጋርተር አባል ሲሆኑ እንደ ማህበሩ ልማድ መሰረት የተደረገላቸውን ስነ ስርዓት ያሳያል፡፡

ከስር የአፄው የናይት ኦፍ ሴራፊም አርማ ይታያል፡
ሆኖም ግን ይህም በእርግጠኝነት የኢሉሚናቲዎች ጭፍራ ሆኑ ማለት አይደለም፡፡ አፄ ኃይለስላሌ የዚህ ማህበር አባል መሆናቸው የሚስጥር ማህበራቱን አሰራር ለማያውቁ ሊያስገርም ይችላል፡፡ በእነዚህ ሜሶናዊ ማህነራት በዝቅተኛ መአርግ አባል የሚደረጉት እጩዎች መጨረሻ መአርጎች ላይ ሲደርሱ ወይም ኢሉሚናቲ አስኪሆኑ ድረስ የማህበሩ አባል መሆኑ ትክክለኛ ሚስጥር አይገባቸውም፡፡ እናም በመልካም ስማቸው አባል እንዲሆኑ ሲጠሩ እንደክብር ከመቁጠር ውጪ ስለሴጣናዊው ሚስጥር የሚያስቡት ነገር አይኖርም፡፡ 

ድህረ-ነገስታት ኢትዮጵያ እና ኢሉሚናቲ
ነገስታቱ ከሃይማኖት ጋር ባላቸው ቁርኝት ከሚስጥር ማህበራቱ ጋር ቁርኝት ሊኖራቸው ይችላል የሚለውን በቀላሉ ላይሆን እንደሚችልም አይተናል፡፡ አሁን ደሞ ከነገስታቱ በኋላ ኢትዮጵያን የሚመሩቱ በሚያንፀባርቁት ርእዮተ ዓለም እና የሚጠቀሙበትን ምልክቶች ተጠቅመን የኢሉሚናቲን ስውር እጆች ማግኘት እንችላለን፡፡ እዚህ ጋርም ግን ክፍተት አለ፡፡ የምልክቶች መተሳሰር የኢሉሚናቲ ምንንነትን ከማሳየት ውጪ በሁለት ነገሮች ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡
አንድ ምልክቶቹ ከህዝባዊ ንቅናቄ ታሪክ ጋር የተሳሰሩ እንደመሆናቸው ከሚስጥር ውጪ ሌላ ህዝባዊ ትርጉምም አላቸው፣ እናም በዚህ ህዝባዊ ትርጉማቸው ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፤  
ሁለት ድህረ ነገስታቱ የመጡት መሪዎችም ቢሆኑ ብሄራዊ ፖሊሲዎች የሚያስቀድሙ እንደመሆናቸው የኢሉሚናቲ ምልክት ቢገኝባቸው በውስጣቸው ምልክቶቹን እንዲጠቀሙ ያደረጉ አካላት መኖራቸውን ብቻ ያሳያል እንጂ ሙሉ ለሙሉ የኢሉሚናቲ ተከታዮች መሆናቸውን አያሳይም፡፡
ፒራሚዱ እና ዓይኑ ምልክት የሚለውን ፅሁፍ ካነበብነው ከታች የምናየውን ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን አንድ ዓይና ምልክት በኢትዮጵያ ማግኘት በውነቱም ያስደንቃል፡፡ ይህኛው ለየት የሚያደርገው አንፀባራቂው የዐዓይን ምልክት ከኢትዮጵያም ሆነ ዓለም አቀፋዊ አብዮታዊ እንቅስቃሴ ጋር የማይገናኝ መሆኑ ነው፡፡




ከስር ደሞ አሁንም አንድ ዓይናማ የኢትዮጵያ ካርታ ምስል ማግኘት ይቻላል፡፡ ይህን ምስል ይዘው የወጡት ወታደሮች ከምሁራኑ ፓርቲ ይልቅ ወታደራዊው ደርጉ የበላይ ሁኖ የወጣበትና ሰራዊቱ ለደርጉ ያለውን ድጋፍ ያሳያበት ሰልፍ ግዜ የታየ ካርታ ነበር፡፡ ይህኛው ልክ የአሜሪካ ዶላር ላይ እንዳለው አይን እና ፒራሚድ ቅርፅ ነው፡



በተጨማሪም የችቦው ጥያቄ ነው፡፡ ይህም በሕብረተሰባውያን ንቅናቄ ችቦው ለህዝቡ እንደተነገረው ከሆነ የነፃነት ብርሃን ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በሚስጥር ማህበራቱ ግን ሌላ ትርጉም አለው፡
አልበርት ፓይክ ያአሜሪካ ፍትህ ቢሮ ሃውልት የተሰራለት 33ኛ መዓርግ የደረሰው ፍሪሜሶን (Morals and Dogma, 321) በሚለው መፅሃፉ እንደሚከተለው ይላል፡- ሉሲፈር፣ ብርሃን [ችቦ] ያዢው! ለጭለማ መንፈስ ይህን ስም መስጠት እንግዳ ነው፡፡ ሉሲፈር፣ የንጋት ልጅ! እሱ ነው ብርሃን የሚይዘው…
እርግጥ ነው ሴጣን በትእቢቱ ምክንያት ከገነት ከመባረሩ በፊት የንጋት ልጅ፣ ብርሃን ያዥ ይባል ነበር፣ ይህ መዓርጉ መገፈፉ ግን ለሚስጥር ማህበራቱ አልተዋጠላቸውም፣ አሁንም ድረስ እውቀት ይሠጣል፣ ብርሃኑን ይዞ ነው ከገነት የወጣው ብለው ያስተምራሉ፡፡ ይህ ሉሲፈራዊነት ይባላል፣ የዚህ ታሪክ የግሪክ አቻው ፕሮሚትየስ ይባላል፣ እናም ፕሮሚትየስን ሲያገኑ ከሰማችሁ ሉሲፈርንም እያሰቡ መሆናቸውን እወቁ፡፡ ፕሮሚቲየስ በግሪክ አፈታሪክ በማስዋል ብቃቱ ይታወቃል፡፡ ሆኖም የአማልክቱ ፈጣሪ/አለቃ ዜኡስን እሳት በመስረቅ ለሰው ልጆች በመስጠት ክዷል፡፡ በዚህም ምክንያት ለሰው ልጆች የስልጣኔ ጥበብን፡- ፅሁፍ፣ ሂሳብ፣ ግብርና፣ ህክምና እና ሌሎች ሳይንሶችን በማስተማር ይመሰገናል፡፡ ለጥፋቱም ከአለት ጋር ታስሮ ታላቅ ንስር በየቀኑ ጉበቱን እንዲበላውና መልሶ ሲያድግ ዳግም እንዲበላው በማድረግ ቀጥቶታል፡፡
“ፕሮሚቲየስ [አርቆ ማሰብ ማለት ነው] ሞኝ አልነበረም፣ ለምንድነው ዙኡስ ላይ ያመፀው? (ሁሉንም የሚያየውንና የሚያውቀውን) ዜኡስን በሃሰት መስዋእት ሊያታልለው ሞከረ፡፡ ከዚህ በላይ ሞኝ መሆን ይቻላል? በተጨማሪም ፕሮሚቲየስ እሳት ከዜኡስ ሰርቆ ምድር ላይ ላሉ ሟቾች ለኋላ ቀሮቹ ለሰዎች ሰጣቸው፡፡ ዜኡስ ፕሮሚቲየስን ለብቻው አልቀጣውም በዚህ አመፀኛ አምላክ ድፍረት ምክንያት ዜኡስ ዓለሙን በሞላ ቀጣ፡፡” ስቴዋርት
በሉሲፈር እና በፕሮሚትየስ ያለው ትስስር ግልፅ ነው፡ ፕሮሚትየስ ሲሳልም ሆነ ሃውልቱ ሲቀረፅ ችቦ ይዞ ነው፡


በዚህ ዙርያ የበለጠ ለማወቅ፡ የሮክፌለር ማእከል – Rockefeller Center ይመልከቱ፡፡

ይችቦ ምልክቶች በሃገራችን:

ሌሎችም የህብረተሰባውያን ምልክቶች እንዲሁ በቀላሉ ከሚስጥር ማህበራቱ ጋር ባላቸው ሚስጥራዊ ፍቺ ማስተሳሰር ይቻላል፡ ለምሳሌ የማጭዱ እና መዶሻው ምልክትን ብናይ መዶሻው ዜኡስ የተባለው የጥንታውያን ግሪክ አምላክ የሚይዘው ሲሆን ማጭዱ ደሞ በሌሎች ጥንታዊ አውሮውያን ባእድ እምነት የሞት መልአክ የሚይዘው ይሆናል፡፡

ንድፈ ሃሳብ አመንጪዎች የሚስጥር ማህበራቱ በመሆናቸው ነው፡፡ የህብረተሰባውያኑ መመርያ መፅሃፍ የሆነችው ኮሚውኒስ ማኒፌስቶ የያዘችው አስር ትእዛዛት ከፃፉት ማርክስ እና ኢንግልስ ከመወለዳቸው ከሺህ ዓመታት በፊት የነበሩ የተወገዙ የሚስጥር እምነቶች ዶግማዎች ነበሩ፡፡

እዚህ በተጨማሪ በመጨረሻ ላይ ልናያት የምንችለው የኮኮብ ምልክትን በተመለከተ ይሆናል፡፡ ባለ አምስት ጫፉ ኮከብ ወይም ፔንታግራም ከጥንት ከፓይታጎረስ የሚስጥር ማህበር ጀምሮ ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ሚስጥራዊ ምልክት ነበር ሆኖም ግን ከአብዮታውያኑ ንቅናቄ በኋላ ሁለት ትርጉም ይዞ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ 


በሚስጥራዊ አስተምህሮ ፊቺው እንደሚከተለው ነው፡ አምስቱም ጫፎች የየራሳቸው ፍቺ አላቸው ወደላይ ያቀናው አንዱ ጫፍ መንፈሳዊውን ይወክላል የተቀሩት አራቱ ደግሞ እሳት፣ ምድር፣ አየር እና ውሃን ይወክላሉ፡፡ 
በሚስጥር ዶግማ እያንዳንዱ ሰው ኮከብ ነው በሚለው የትእቢት አስተምህሮ (ይህ እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ የሚለውን የእባቡን ምክር ተከትሎ የመጣ ነውና) በዚህ ደግሞ ሰውን በአምስቱ ጫፎች ሚዛን ጠብቀው ይስላሉ፡፡ 

ወደሃረጋችን ስንመጣ እንደማንኛውም የዓለም ህዝቦች ባለ አምስት ጫፉ ኮከብን በተለያየ መልኩ ድህረ-ነገስታት ኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ተጠቅመውበታል፣ አሁንም ይጠቀሙበታል፡፡ ከስር ኮከብ ያለው ደርግ ፓርቲ ባጅ ይታያል፡





ከስር ደግሞ በደርግ ግዜ የነበረ ሃውልት ክብ ውስጥ የገባች ፕንታግራም እና ችቦ ያሳያል፡





አሁን የኢትዮጵያ አርማ የሆነውና ባንዲራው መሃል ላይ ያለው ኮከብም ልክ በወታደራዊው ደርግ ግዜ እንደታየው አንድ አይና ምልክት ወጣ ያለ ነው፡፡ ይህም ኮከቡ በተጠላለፉ ዘንጎች የተሰራ መሆኑ ነው ዘንጎቹ ሲጠላለፉ ለየት ያለ ትርጉም ስለሚሰጡ ነው፡፡ እንዲሁም የሚያንፀባርቅ መሆኑ ከንጋት ብርሀን ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡

የሆነ ሁኖ ግን በዚህ ዘመናዊ አለም ላይ ባለው ሰፊ የመወራረስ ልማድ መሰረት ባእድ ምልክቶች እና ዘመናዊ የህዝባዊ ንቅናቄዎች ምልክቶችን ይወራረሳሉ፡፡ ስለዚህም ሁሌም ቢሆን ትርጓሜ በሁለት መስመር ሊሄድ ይችላል፡፡ ምልክቱ ልክ ህገ መንግስቱ ላይ እንደሚለው ከሆነ ግን ልዩነትንና አንድነትን የሚያመላክት ጨረሩ ደሞ ብልፅግናን ሰመያዊው ሰሃን ሰላምን ይወክላል፡፡ 



መደምደምያ
እስከአሁን አንዲትም ቀጥተኛ ማስረጃ አላቀረብኩም፡፡ ቀጥተኛ ሊሆን የሚችለው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ የሜሶናዊ ማህበራት አባል መሆን ነው ግን ይህም ቢሆን ማህበራቱን የተቀላቀለ ሁላ ሚስጥራቱን ሁሉ አውቆ ተስማምቶበት አይደለምና ምንም አለማለት ሊሆን ይችላል፡፡ በግሌ የምረዳውም በዚህ መልኩ ነው፡፡
ቀጥተኛ ትስስር ያላቸው ምልክቶች ያሉበትን ስናይ ደሞ ሃገሪቱ የዓለም አቀፋውያንን ፖሊሲ የማታራምድ መሆኗ ከበስተጀርባ መጠነኛ ተፅእኖ ያለው ሰው ስራ ነው ሊያስብል ይችላል ምክንያቱም ዋና መሪዎቹ ኢሉሚናቲ ቢሆኑ ኖሮ በኢትዮጵያ ብዙ ብሔራዊነት የሚንፀባረቅበት ፖሊሲ አይራመድም ነበር፡፡ ለምሳሌ ያክል፡ የዓለም ፍርድ ቤት እና የዓለም ንግድ ድርጅት አባል አለመሆናችን፣ በዙርያችን እና በአህጉራችን ያሉ ሜሶናዊ ፖለቲከኞች አንድ ገንዘብ፣ ነፃ ኢኮኖሚ ቀጠና ይኑረን እያሉ ሲወተውቱን አለመተግበራችን፣ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሞኖፖል የሚሰጡ ስትራቴጅያዊ ዘርፍች ማጠራችን ወዘተ ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡ ስለዚህም ኢሉሚናቲ ኢትዮጵያ ውስጥ በትንሹ ምልክቶቹን ቢያሳይም እንደሌሎች ሃገሮች ግን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮናል ማለት አይቻልም፡፡ ይህ ባለኝ ውሱን መረጃ የደረስኩበት ነው ከዚህ የተሻለ መረጃ ያለኝ አለ የሚል ካለ ለመማር ዝግጁ ነን፡

1 comment:

wanted officials