Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 10, 2014

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) 
የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ተቃዋሚዎችን በማሰር፣ በማሰቃየት እና በመግደል ስልጣን ማራዘም አይቻልም!!
በሀገራችን ኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ስርዓት ባለመስፈኑ ምክንያት እንደልቡ በሚፈነጨው ህውሓት/ኢህአዴግ ስልጣን በጠመንጃ አፈሙዝ ከተቆናጠጠ ጀምሮ የተለያዩ በደሎች እየተፈፀሙ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ የተቃዋሚ ድርጅት አመራር እና አባላት ላይ ሰበብ እየተፈለገ ህውሓት/ኢህአዴግ በሚፈለገው መንገድ እየፈረጀ ያስራል፣ የሰቃያል፣ ይገድላል፡፡ 
በትናንትናው ዕለት 02/11/2006 የመኢአድ የቦሌ ክፍለ ከተማ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ታምራት ዘውዴን የፌደራል ፖሊስ መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመምጣት ያለ ፍርድቤት ትዕዛዝ ቤታቸውን ለሁለት ሠዓታት ያህል ከፈተሸ በኋላ አቶ ታምራትን ወደ አልታወቀ ቦታ ወስዶአቸዋል፡፡ እስካሁንም ያሉበት ቦታ ሊታወቅ አልቻለም፡፡
ያፈና ስልቱን እየቀያየረ አመራሮቻችንንና አባሎቻችንን ተለጣፊ ስም በመስጠት፣ በማሰርና በመግደል ሰላማዊ ትግላችንን ለማጥፋት ህገ-ወጥ ተግባሩን ቀጥሎበታል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በአቶ ታምራት ዘውዴ የተወሰደውን ህገ-ወጥ አፈና አጥብቆ እያወገዘ በአስቸኳይ እንዲለቀቅ ይጠይቃል፡፡
መኢአድ ይህ ስርዓት በሰላማዊ ትግል ከስልጣን እስካልወረደ ድረስ የዜጎችንም ሆነ የአባላት እንግልት፣ እስራት፣ ግድያ ይቆማል ብሎ አያምንም፡፡
የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ስውርና ግልፅ እኩይ ደባዎችን በእኛ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ እየፈፀመ ይገኛል፡፡ ከእንግዲህ ግን ሊቀጥል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
ስለሆነም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መኢአድ ከሚያደርገው እልህ አስጨራሽ የሰላማዊ ትግል ጐን እንዲሰለፉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሐምሌ 03 ቀን 2006 ዓ.ም


No comments:

Post a Comment

wanted officials