Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 10, 2014

አቡጊዳ – አገር ቤት በሰላም የሚታገሉ አንጋፋ ወጣት ፖለቲከኞች ታሰሩ !

አገር ቤት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚታገሉ ወጣት ፖለቲከኞች መታሰራቸዉን የደረሰን ዘገባ ገለጸ። ከታሰሩት ወጣቶች ዉስጥ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋና የአረና አመራር አባል እና ታዋቂ ብሎገር አቶ አብርሃ ደስታ ይገኙበታል።
በጉዳዩ ላይ የአንድነት ፓርቲ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፣ ድርጊቱን መንግስታዊ ዉንብድና ብሎታል። ከተለያዩ ማእዘን በርካታ ኢትዮጵያውያን በድርጊቱ መበሳጨታቸውን እየገለጹ እንደሆነም ለመረዳት ችለናል። እስረኞቹ እስከአሁን ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ሲሆን፣ በምን ወንጀልና ክስ ሊታሰሩ እንደቻሉ በገሃድ የታወቀ ነገር የለም።
ኢቲቪ የግንቦት ሰባቱን መሪ አቶ አንዳርጋቸዉን ባቀረበበት ወቅት ፣ በሰላም እንታገላለን በሚሉ ድርጅቶች ተሰግስገው ፣ ከግንቦት ሰባትና የግንቦት ሰባት ልሳን ከሆነ ኢሳት ጋር ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦችም ተይዘዋል» ሲል በዘገበው መሰረት ታሳሪዎቹ በኢሳት በመቅረባቸው ፣ እነ አንዱዋለም አራጌ፣ እስክንደር ነጋ እንዳደረጉ “”ግንቦት ሰባቶች ናችሁ» የሚል ክስ ይመሰርታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አቶ መለስ ዜናዊ ከመቶ በኋላ የተተኩት አዲሱ ጠ/ሚኒስተር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ በወቅቱ ወደ መሀል በመምጣትና የፖለቲካ መሻሻሎችን በማድረግ ሕዝብን ያቀራርባሉ፣ የፖለቲካ እስረኞቹን ይፈታሉ ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፣ የታየዉ ግን ፍጹም ከዚያ ተቃራኒ እንደሆነ ሁኔታዎች እያሳዩ ነው። እንኳን የታሰሩ የሕሊና እስረኞች ሊፈቱ ቀርቶ፣ ቁጥራችው እጅግ በርካታ የሆኑ ሰላምዊ ዜጎች ወደ እሥር እየታጎሩ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶች በጥይት በአምቦና ጊምቢ መረፍረፋቸዉን ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials