Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 10, 2014

የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ባለቤት የምሥራች ኃይለማርያምና ወንድማቸው ብዙነህ ፅጌ

የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ባለቤት የምሥራች ኃይለማርያምና ወንድማቸው ብዙነህ ፅጌ…

ባለቤታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ያገኛሉ ብለው እንደማያምኑ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ባለቤት ወ/ሮ የምሥራች ኃይለማርያም ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ወንድማቸው አቶ በዛብህ ፅጌም የወ/ሮ የምሥራችን ሃሣብ አጠናክረው “አንዳርጋቸው በቴሌቪዥን ሲናገር የተሰማው ከተፈጥሮው ጋር የማይጋጭ እንዲያውም የሚያጠናክረው ነው” ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ዜጋው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ኢትዮጵያ ውስጥ በእሥር ላይ የሚገኙበት የእንግሊዝ መንግሥት የየመንን አድራጎት አውግዞ ኢትዮጵያ ውስጥ በሌሉበት የተላለፈባቸው የሞት ፍርድ ተፈፃሚ እንደማይሆንና ፍትሐዊ የፍርድ ሂደት ይደረግላቸዋል ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጿል፡፡
ለዝርዝር ዘገባውና ለሙሉ ቃለ ምልልሶች የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡
source VOA

No comments:

Post a Comment

wanted officials