ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢ.ሕ.አ.ግ/ የተሰጠ መግለጫ
የማፈኛ መዋቅሩን መሰረት በማድረግ በርካቶች ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን እጅግ በከፋና በሚዘገንን ሁኔታ በማጥፋት እኩይ ተግባሩ የሚታወቀው አረመኔው የወያኔ ስረአት በሃገራችን የተንሰራፋውን መጠነ_ሰፊ
ተግዳሮት ከመሰረቱ ለመንቀል በሚደረገው ትግል ብርቱ ጥረት እና እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን መንግስት ጋር በማበር የአንድን ሰው ከአገር ሃገር የመንቀሳቀስ መብት በመጣስ የየመን መንግስት ለወያኔ ማስረከቡ አጥብቀን የምናወግዘውና የምንቃወመው ድርጅታችን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በደረሰው አፈና መሰረት በማድረግ ማንኛውንም አይነት እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን አበክረን እናስታውቃለን፡፡
ለአገርና ለወገን ዕድገት ብልጽግና ሲሉ በመታገላቸው ሳቢያ የየመን መንግስት እሳቸውን አፍኖ በማስረከቡ ምክንያት አገር ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ትግል ለአንድም ደቂቃ ቢሆን የሚገታው አለመሆኑን እብሪተኛው ቡድን ሊረዳው ይገባል፡፡
በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በደረሰው የተቀነባበረ አፈና ዛሬ ላይ መግለጫ የማውጣታችን ምክንያት ጉዳዩ እስኪረጋገጥ በሚል እንጂ ቀደም ባሉት ቀናቶች ማውጣት ይጠበቅብን እንደነበረ እናምናለን ስለሆነም መላው የአገራችን ለውጥ ናፋቂ ወገናችን ሁሉ ይሄንን ሃሳባችንን በቅጡ እንዲረዳልን እናስገነዝባለን፡፡
እንደ አንድ ታጋይና አታጋይ እሳቸውን በተቃውሞ ትግል ማጣታችን ቃል ሊገልጸው ከሚችለው በላይ በውስጣችን ቁጣ ፈጥሮዋል፡፡ አገዛዙ አቶ አንዳርጋቸውን ከየመን መንግስት መረከቡ ለውጥ ናፋቂው ህዝብ በፍርሃት ተሸብቦ ለትግል እንዳይነሳሳና ማንኛውም ተቃዋሚ የትም ሄደ የትም ከገባበት ገብተን በእጃችን ለማስገባት የሚያስችለን ዲፕሎማሲ ግንኙነት አለን በሚል ስጋት ለመፍጠር የተሰራ ቀመር ስለመሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡
ትምክህተኛውና ዘራፊው ቡድን ያልተረዳው ነገር ቢኖር ሕዝቡ ለሚያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ትኩረት ሰጥቶ በማዳመጥ አግባባዊበሆነ መልኩና ሕዝቡን ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል መልኩ ምላሽ እስካልሰጠ ድረስ በማፈን በማሳደድ በማዋከብና በመግደል የሚመጣ መፍትሄ አለመኖሩን ብቻም ሳይሆን በሕዝቡ ላይ የሚወሰዱ ጭፍን ኢ_ሰብአዊ ድርጊቶች በጨመሩ ቁጥር ስረዓቱጋሱን ወደ መቃብር ጉድጓድ እያስጠጋ እንዳለ ሊረዳው ይገባል፡፡
አንድነት ሃይል ነው!
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ኢሕአግ/
ሰኔ 28/ 2006 ዓ/ም