የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረጉት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ህገ መንግስቱና የጸረ ሸብር አዋጁ በሚያዙት መሰረት እጃቸው ከተያዘበት አንስቶ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባቸውና በቤተሰቦቻችውና በጠበቃቸው መጉብኘት መብታቸው መሆኑን ከግምት በማስገባት ጠበቆቻቸው ያልተሟሉላቸው መብቶች በፍርድ ቤት ጣልቃ ገብነት ይከበሩ ዘንድ በዛሬው ዕለት ክስ መስርተው የማዕከላዊ አመራሮች ለቀረበባቸው ክስ በአካል በመገኘት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ሃላፊዎቹ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ምላሽ ሰዎቹን ፍርድ ቤት በ2/11/2006 ዓ.ም ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል፡፡የታሳሪዎቹ ጠበቆች የሆኑት ጠበቃ ተማም አባቡልጉና አቶ ገበየሁ ደምበኞቻቸውን ማግኘት አለመቻላቸውን ፍርድ ቤት ሲቀርቡም እንዲያውቁ አለመደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ጠበቆቹ ደምበኞቻቸውን ማየት እንዲፈቀድላቸውና በቤተሰቦቻቸውም እንዲጎበኙ እንዲደረግ ትዕዛዝ እንዲሰጥ አቤት ብለዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካደመጠ በኋላ ታሳሪዎቹ በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙ እንዲደረግና ከጠበቆቻቸው እንዲመካከሩ ይደረግ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ ከዚሀ በተጨማሪም በማዕከላዊ እንደሚገኙ የተነገረላቸውን ታሳሪዎች የፊታችን አረብ 4፡00 እንዲቀርቡ ሲል አዟል፡፡የማዕከላዊ ኃላፊም በፍር ቤቱ የተሰጠውን ትዕዛዝ መፈጸሙን እንደሚከታተሉ ተናግረዋል፡፡