Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 25, 2014

ኢህአዴግ ሰራዊቱን በከፍተኛ ቁጥር ወደ ሰሜን እያጓጓዘ ነው

ኢህአዴግ ሰራዊቱን በከፍተኛ ቁጥር ወደ ሰሜን እያጓጓዘ ነው

ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የደህንነት አባላት በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ፣ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሰራዊቱን አባላትና ከባድ
መሳሪያዎችን በምሽት ወደ ሽሬ፣ ተከዜ፣ ወልቃይት፣ መተማ፣ አርማጭሆ በመሳሰሉት የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እያጓጓዘ ነው።
ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን ጋር በተያያዘ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የታው የህዝብ ቁጣ ያስደነገጠው መንግስት፣ ማንኛውም አይነት ተቃውሞ ቢነሳ በሚል ሰራዊቱንና ደህንነቱን እያሰማራ ነው።
ከሰሜን አካባቢዎች የመጡ የደህንነት አባላት፣ ግንቦት7 ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር ለአርሶ አደሩ የጦር መሳሪያ በማደል እስከ መሃል አገር ሊገባ ይችላል የሚል አስተያየት መስጠታቸውን
ተከትሎ ፣ ግንባሩ በድንበር አካባቢዎች ላሰማራቸው የድርጅቱ አባላት ባለሀብቶች ዘመናዊ ስልኮችን በማደል የስለላ ስራ እንዲሰሩ እንዳሰማራቸው ታውቋል።
ከተለያዩ የሰራዊቱ ክፍሎች የሚከዱ ወታደሮች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ ኢህአዴግ የሚጠፉ ወታደሮችን ለመተካት በሚል ያወጣው የቅጥር ማስታወቂያ
የተፈለገውን ያክል የሰው ሃይል አላስገኘለትም።
የኢህአዴግ ሰራዊት በከፍተኛ የሞራል ውድቀት ላይ መሆኑን የሚናገሩት ከሰራዊቱ የሚከዱ ወታደሮች፣ በዘር ላይ የተመሰረተው አደረጃጃት፣ የምግብ አቅርቦት መበላሸት እና የሰራዊቱ የኑሮ ሁኔታ ማሽቆልቆል
ለሰራዊቱ ሞራል መውደቅ ዋና ምክንያቶች ሆነው ይጠቀሳሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢህአዴግየመከፋፈልአደጋእንዳንዣበበት ምንጮች ገልጸዋል የገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር በተለይ ከአቶ መለስ ሞት በኃላ አገሪትዋን መምራት ካለመቻሉ ጋርተ ያይዞ በዜጎች ላይየሚወስደው የጅምላ እስርና የማሳደድ ዘመቻ በራሱ አባላት ጭምር ጥያቄ እያስነሳ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ፓርቲዎች በሽብርተኛነት ሰም ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞች ላይ ያነጣጠረ የእስር እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉ በተለይ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራሩ አካባቢ ተቃውሞናጉ ምጉምታ እየተሰማ ነው፡፡
ምንጮች እንደገለጹት በኢህአዴ ግበኩል የሚወሰደውኢ-ዴሞክራሲያዊ እርምጃ የህዝብ አመኔታ
በማሳጣት የግንባሩን ሕልውና ችግር ላይ ይጥላል የሚሉ እና እየተወሰደያለውንጉልበትየታከለበትእርምጃ
በሚደግፉ አባላትና ከፍተኛ ካድሬዎች መካከል መቃቃር እየተፈጠረ መሆኑታውቋል፡፡
ግንባሩ በተፈጥሮው ከግምገማ በዘለለ የውስጥ ቅራኔን የሚፈታበት መንገድ የሌለው መሆኑና ልዩነቶች ከባድ ዋጋ የሚያስከፍሉ በመሆናቸው ምክንያት ቅሬታዎቹ ታምቀው እስካሁን መቆየታቸውን የገለጹት ምንጮቻችን በተለይ በሠላማዊ መንገድቅሬታውን ከሁለት ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ እየገለጸ ያለውን ሰ ፊየሙስሊም ማህበረሰብየተቃውሞድምጽለማፈንኃይልየታከለበትተደጋጋሚእርምጃ በረመዳን የጾም ወር መወሰዱ ሙስሊም የግንባሩን አባላት ጨምሮ በበርካታ አባላት ዘንድ ተቃውሞ እንዲቀጣጠል ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡
ኢህአዴግ በአሁኑ ወቅት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ከጋዜጠኞች ፣ከሲቪል ማህበረሰብአባላት፣ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ፣ በብዛት ወጣቶችን ካቀፈው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማህበረ ቅዱሳን እንዲሁም
በኑሮ ውድነት ከሚሰቃየው ሰፊህብረተሰብ እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመላተሙ በመጪው ምርጫ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሊመረጥ እንደማይችል መገንዘቡን ያስታወሱት ምንጮቹ በዚህ የተነሳ የትኛውንም ዓይነት ተቃውሞ በኃይል ለመደፍጠጥ ወስኖ ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
ይህየግንባሩ እርምጃ ትክክል አይደለም የሚሉ አባላት ብቅ ብቅ ማለታቸው ግንባሩ በቀጣይ ከባድ የመሰነጣጠቅ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል የመጀመሪያው ምልክት መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials