Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 10, 2014

የሺዋስ አሰፋ ማዕከላዊ ሲወሰድ ሐብታሙ አያሌው ያለበት አልታወቀም

የሺዋስ አሰፋ ማዕከላዊ ሲወሰድ ሐብታሙ አያሌው ያለበት አልታወቀም

የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሺዋስ አሰፋ ብዛት ያላቸው ፌደራል ፖሊሶች፣የደህንነት አባላትና ፖሊሶች መኖሪያ ቤቱን በመክበብና ወደ ውስጥ በመግባት ከያዙት በኋላ ቤቱን በመበርበር ለጊዜው ያልታወቁ ንብረቶችን በመያዝ ከየሺዋስ ጋር ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መውሰዳቸው ታውቋል፡፡
ቤት ፈታሾቹ የየሺዋስን ቤት በሚበረብሩበት ወቅት የየሺዋስን ባለቤት ጭምር ወደ ውስጥ እንዳትገባ ማድረጋቸው አግራሞትን ፈጥሯል፡፡
በዚሁ ዕለት ማለዳ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት በማምራት ላይ የነበረው አቶ ሐብታሙ አያሌው ቦሌ ደምበል አካባቢ እንደደረሰ ብዛት ያላቸው የደህንነት አባላት በፌደራል ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ሐብታሙን ይዘውት ሄደዋል፡፡የአንድነት አመራሮች ወደ ተጠቀሰው ቦታ በማምራት ድርጊቱ ሲፈጸም ከተመለከቱ ሰዎች የሐብታሙ መያዝን አረጋግጠዋል፡፡እስካሁን ድረስ ግን ሐብታሙን ይዣለሁ ያለ አካል አልተገኘም፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials