ዳኞች ፣ የፖሊስ አዛዞች ፣ ከፍተኛ ካደሬዎችና የካቢኔ አባላት እንዲሁም የየክፍለ
ከተማ መጅሊስ አመራሮች ተገኝተዋል ፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ እስከ አስር የሚደረሱ
ሰዎች በድብደባው ተገድለዋል ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ጥቂቶቹ ሙስሊም ያልሆኑ
ኢትዮጵያዊያን ናቸው :: “ ሂጃብ እና ኮፊያ ተቃጥሏል ፣ መስጂድ ተረግጧል የሚል
ጥያቄ ስታነሱ ትንሽ አታፍሩም ? መስጂድ ሊጠብቁ የሄዱት ፖሊሶቻችን ሲገደሉ ግን
ምንም አላላችሁም ” የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራር አባል አቶ ይደግ
በሳምንቱ መጀመሪያ አካባቢ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህና ፀጥታ ቢሮ
በአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት አዳራሽ ለሁለት ቀናት ባደረገው ስብሰባ የመጅሊስ
አመራሮችን ወቀሰ ፡፡ ዳኞች ፣ የፖሊስ አዛዞች ፣ ከፍተኛ ካደሬዎችና የካቢኔ አባላት
እንዲሁም የየክፍለ ከተማ መጅሊስ አመራሮች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ የአዲስ
ከተማ አስተዳደር አመራር አባል የሆኑት አቶ ይደግ ለተሰብሳቢዎቹ እንደገለፁት “
አርብ እለት በአንዋር መስጂድ ለተፈጠረው ሁከት ትልቁን ሃላፊነት ሊወስዱ የሚገባው
የመጅሊስ ተመራጮች ናቸው ፡፡ ገና ዱሮ ሁከት ፈጣሪዎችን ከየወረዳቸው በማጋለጥ
ለመንግስት ጠቁሙ ሲባሉ ወደ ኋላ ሸሹ ፡፡ ሌላው ቀርቶ የፀጥታ ሰዎቻችን በቁጥጥር
ያዋሉዋቸው ሁከት ፈጣሪዎች ላይ መስክሩ ተብለው የመሰከሩት እኮ በጣም ጥቂቶች
ናቸው ፡፡ እኛ ምስካሪ አጥተን ክርስቲያኖችን ማህተባቸውን እያስወለቅን እኮ ነበር
ስናመሰክር የነበረው ፡፡ ይሄው ዛሬ ውጤቱን አየነው ፡፡ አይናችን እያየ ተቃውሞው
“ከድምፃችን ይሰማ” ወደ ፖለቲካ ፖለቲካ መፈክሮች ተቀየሩ ፡፡ በርካታ ፖሊሶቻችን
ቆሰሉ ፡፡ ህይወታቸውንም ያጡ አሉ ፡፡ መጅሊሶች ሌላው ቢቀር የተረከቡትን
መስጂዶች እንኳ መቆጣጠር አልቻሉም ፡፡አሁንም የአክራሪዎች መፈንጫ እየሆኑ
ነው” በማለት ወቅሰዋል ፡፡ የመንግስትን ጥቁር ሽብር ጥቃት ተከትሎ ስለተጎዱ ሰዎች
አቶ ይደግ ሲገልፁም “እኛ እንዳውም ከዚህ የበለጠ ቁጥር ያለው ሰዎችን መጉዳት
አላቃተንም ነበር ፡፡ እንኳን ለራሳችን ለሰውም ሀገር የሚተርፍ ጦር አለን፡፡ አልሸባብን
የመሰለ ሀይል ድመጥማጡን አጥፍተናል ፡፡ እንደዜጋ ስናስበው ግን እስካሁን ድረስ ከ
500 በላይ ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ ቆስለውብናል ፡፡ ከ400 የሚልቁ ሰዎች
በፓውሎስና ሌሎች ሆስፒታሎች እየታከሙ ሲገኙ ከ 120 በላይ የሚሆኑት ደግሞ
እኛው ጋር በፖሊስ ሆስፒታል እየታከሙ የሚገኙ ናቸው ” ብለዋል ፡፡በጥቃቱ ከ10
በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ከመድረኩ የተገለፀ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት
ሙስሊም ያልሆኑ ዜጎች እንደነበሩ ተገልፇል ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነች ሴትም
በብጥብጡ መካከል እንደነበር የገለፁት አቶ ይደግ ይህም ፖለቲካ ፓርቲዎችም
ተሳታፊ እንደነበሩ አመላክቶናል ፣ልጅቱ ፖሊሶች ሲይዟት “መብቴ ነው ቪዲዮ ልቀርፅ
ነው የመጣሁት” ብላለችና ምን አግብቷት ነው የምትቀርፀው ? ሲሉ እንዳሾፉም
የፍትህ ሬዲዮ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ አንዳንድ አባላቶቻችንም በሬድዮ መገናኛ በኩል
ለበላይ አካል የሚተላለፉ ሪፖርቶችን እየጠለፉ ለአክራሪዎቹ ሚዲያ እንደሰጡ
በማግስቱ የወጡትን ፍትህ ሬዲዮና መሰል አየክራሪ ሚዲያዎችን መታዘብ ይቻላል
ያሉት አቶ ይደግ ይህ አይነቱ ግዴለሽነት መንግስት እንደማይታገሰውና አባላቶችም
ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስፈራርተዋል ፡፡ አንድ የዋልታ ኢንፎርሜሽን ተወካይም
ተነስቶ እኛ በድብቅ ካሜራ የቀረፅነውን ሁሉ ኢሳቶች ሳተላይት በመጠቀም እያነሱብን
ተቸግረን እንጂ ከዚህም በላይ መስራት እንችል ነበር ሲል አስተያየት ሰጥቷል ፡፡ የአቶ
ይደግን ንግግር ተከትሎ በርካታ ጥያቄዎች ተስተናግደው ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን
ከነዚህ ውስጥ “ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች መስጂድ ተረገጠ ፣ ሂጃብና ኮፊያ
ተቃጠለ እያሉ ህዝብን እና መንግስትን እያቃቃሩ ነውና ይህ ምን ያህል እውነት ነው ”
የሚል ጥያቄ የተነሳ ሲሆን አቶ ይደግ እጅግ ስሜታዊ ሆነው “ በጣም ያሳዝናል
ሂጃብ እና ኮፊያ ተቃጥሏል ፣ መስጂድ ተረግጧል የሚል ጥያቄ ስታነሱ ትንሽ እንኳ
አታፍሩም ? መስጂድ ሊጠብቁ የሄዱት ፖሊሶቻችን ሲገደሉ ግን ምንም አላላችሁም
፡፡ ” ሲሉ የተዳፈነ ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡ ይህን የአቶ ይደግ ምላሽ አብዛኛው ተሰብሳቢ
ልክ ነው አቃጥለናል ምን ታመጣላችሁ እንደማለት ተቆጥሯል ሲሉ በስፍራው የነበሩት
የፍትህ ሬዲዮ ምንጮች ገልፀዋል ፡፡