Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 4, 2014

ሰሚ ያጣው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጩኸት


ሰሚ ያጣው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጩኸት
.
.
የሙስሊሞች የሀይማኖት እንቅስቃሴ የተፈጠረው ከሁለት አመት በፊት ነበር፡፡ በወቅቱ የእንቅስቃሴያቸው ነጥብ ሶስት ጥያቄዎች ቢሆኑም መንግስት በተለመደው ጉልበታምነቱ ጥያቄዎቹን ለመደፍጠጥና ለማዳፈን የወሰደው የሀይል ርምጃ የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ከማብረድ ይልቅ ይባስ ብሎ እሳት ላይ ጋዝ ሊሆን ችሏል፡፡ በተደራጀና ፍጹም ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ተጀምሮ እስካሁን የዘለቀውን የሀይማኖት ነጻነት ጥያቄ መንግስት የተለያዬ ስም በመለጠፍ ለማወናበድ ታትሯል፡፡ እንቅስቃሴውንም የትንሽ ጽንፈኞች ነው ሲል በተለመደው ዋሾነቱ ለማጭበርበር ሲውተረተር ይስተዋላል፡፡ ይህንን ጭብጥ ቅቡል ለማድረግ ሲልም የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ጨምሮ ንጹሃንን በየ እስር ቤቱ በማጎር፤በማሰቃየት አለፍ ሲልም በመግደል ለማስቆም የወሰደው ርምጃ ትግሉን የበለጠ እንዲቀጣጠል አደረገው እንጅ ሊያስቆመው አልቻለም፡፡ አቡቦከርን ማሰር መፍትሄ የመሰለው መንግስት ሺህ አቡቦከር ነኝ ባዮችን እንደሚያፈራ አላወቀም፡፡ ያሲን ኑር፤አህመዲን ጀበል እና ሌሎቹንም እንዲሁ የሚዘክሩ መንሰሰፈ ጠንካራዎች እና እኛም ኮሚቴዎቹ ነን የሚሉ ሚሊዮኖችን የትግሉ ፍሬ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ በእውነቱ ከአርባ ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን ህዝበ ሙስሊም ወክለው የታሰሩትን የኮሚቴ አባላት ጥቂት አሸባሪዎች ማለት እንደ መንግስት የሚያሳፍር ተግባር ነው፡፡ እንደ ሀገርም የሚያዋርድ ስራ ነው፡፡ ጥቂት የተልዕኮው አስፈጻሚዎችን በየ ቀበሌው በመሰብሰብ የታሰሩትን አሸባሪ ለማባ ሲደክም ማየት የተለመደ ተግባር ሁኗል፡፡ በነገራችን ላይ ሀገራችን አርባ ሚሊዮን አሸባሪ ካላት ለምን በአለም የድንቃድንቅ መዝገብ እንዳልተመዘገበች የሚያውቀው ሽፈራው ተ/ማርያም ብቻ ነው፡፡
ሞት ፤እስር ፤እንግልት፤ ፍረጃ እና መፈናቀል የማያስቆመው የሙስሊም ወንድሞቻችን ጩኸት ዛሬ ሰሚ ያጣ ቢመስልም የማታ ማታ መንግስትን እሳት ሆኖ ሊለበልበው እንደሚችል ይታወቃል፡፡ የአንባገነኖች ትልቁ ድንቁርናቸው ከጓደኞቻቸው አለመማራቸው ነው፡፡ ትናንት የነ ጋዳፊን እና ሙባረክን መጨረሻ ያዬ ዛሬ እንዴት ትምህርት ሊሆነው አልቻለም፡፡ ቀን እባ ያ በህልሙ በልጥ ለምን አይበረይም፡፡ ሙስሊም ወንድሞቸ እናንተ የያዛችሁት የእውነት መንገድ ነው፤እውነት እያደር እያሸነፈ ይሄዳል እንጅ አይሸነፍም፡፡ የሌላ እምነት ተከታዮችም ጥያቄው ከእስልምና አልፎ የሰብአዊ መብት ወደመሆን እየተሸጋገረ ያለውን የነጻነት ትግል እንድትቀላቀሉት ስል ጥሪየኝ አቀርባለሁ፡፡ ይህ ነገር ነግ በእኔ ነው፡፡
በነገራን ላይ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ዛሬም በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥል ድምጻችን ይሰማ ነግሮናል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ሰው እነዚህም ፍትህ ያጡ ወንድሞቻችን እንዲያስባቸው ስል አጠቃልላለሁ፡፡
ድል የሕዝብ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials