የኣብራሃ ደስታታናሽ እህት ወይዘሪት ተክለ ደስታ የኣብራሃ ደስታ እህት በመሆንዋ ብቻ ከስራዋ ታገደች። ወይዘሪት ተክለ ደስታ የሄልዝ ኦፊሰር(HO) ባለሞያ ስት ሆን የህወሓት ኣባልና የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጤና ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ሁና ስትሰራ ነበር።
የወረዳዋ ሃላፊዎች ተክለ የኣብራሃ ደስታ እህት መሆንዋ ያወቁት በቅርብ ግዜ ሲሆን ወድያውኑ የካብኔ ስብሰባ በመጥራት…. “ኣንቺ እንደወንድምሽ ዓረና ነሽ፣ ስለዚ እዚህ ላንቺ የሚሆን የህወሓት ሃላፊነትም ይሁን የሞያ ስራ የለንም”. በማለት ማህተምና የቢሮዋ ቁልፍ ቀምተዋታል።
የወረዳዋ ኣስተዳዳሪዎች….. “ላንቺ እንኳን ስራ መሬቱም እሳት ሆኖ ያቃጥልሻል”…. በማለት ከየጠና ፅህፈት ቤት ምክትላ ሃላፊነትዋ፣ ከየኤክስፐርት ስራዋና ከህወሓት ኣባልነትዋ ኣግደዋታል።
ህወሓቶች ልክ በደርግ ገዜና ይደረግ የነበረው በቤታሰብ ደረጃ የማይመለከታቸው ንፁሃን ዜጎች እየደረሱ ማሰቃየት ጀምረዋል። ከዚህ ቀደምም የስየ ኣብራሃ ቤተሰብ በስጋ ዝምድናቸው ብቻ ለእስራትና ለእንግልት ተዳርገው ነበር።
ወኢዘሪት ተክለ ደስታ የህወሓት ኣባል እያለች….. “ወንድምሽ ዓረና ነው። ኣንቺም የወንድምሽ ተከታይ ነሽ”…. በማለት የደረሳት ጥቃት በጭፍኑ የወሰኑት መሆኑ ያስታውቃል።
የህወሓት ሊቀ መንበር ኣቶ ኣባይ ወልዱ ታላቅ ወንድም የሆነው ኣቶ ኣውዓሎም ወልዱ የዓረና መስራችና ኣመራር ኣባል ነው።
እስቲ ወንድ የሆነ የህወሓት ኣመራር ኣቶ ኣባይን የ”….ወንድምህ የዓረና ኣባል የሆነው ኣቶ ኣውዓሎም ወልዱ ተከታይ ስለሆንክ ከትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪነጥ፣ ከህወሓት ሊቀመንበር ነት ህና ከህወሓት ኣባልነጥ ውረድ”….. ይበል።
እስቲ ወንድ የሆነ የህወሓት ኣመራር ኣቶ ኣባይን የ”….ወንድምህ የዓረና ኣባል የሆነው ኣቶ ኣውዓሎም ወልዱ ተከታይ ስለሆንክ ከትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪነጥ፣ ከህወሓት ሊቀመንበር ነት ህና ከህወሓት ኣባልነጥ ውረድ”….. ይበል።
ህወሓቶች ፓርቲው የቤተሰብ ሃብት ኣድርጎዋት ስላሉ ሌሎች ፓርቲዎችም እንደየነሱ እየመሰላቸው በጅምላ ፍረጃ ተያይዘውታል።
የዓረና ኣባል እህት፣ወንድም ፣ ኣባት፣ እናት፣ ዘመድ፣ ጓደኛ መሆን ዓረና ከማስባሉ ኣልፎ ስራና ሃላፊነት የሚያስቀማ ወንጀል እያደረጉት ነው።
ኣብራሃ ደስታን ማስር፣ ማንገላታት፣ መደብደብ ሳይበቃቸው ወደ ቤተስብ ተሸጋግረዋል። የህወሓት ጉዞ የህዋሊት መራመድ ከጀመረ የቆየ ሲሆን ኣሁንም ቁልቁል እየተምዘገዘግ መሆኑ የሚጦቁም ነው።
ነፃነታችን በእጃችን ነው….!!!
No comments:
Post a Comment