Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 25, 2014

የቋራ ነዋሪዎች በመልካም አስተዳደርና በማህበራዊ አገልግሎት እየተሰቃዩ መሆኑን ገለጹ

የቋራ ነዋሪዎች በመልካም አስተዳደርና በማህበራዊ አገልግሎት እየተሰቃዩ መሆኑን ገለጹ

ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 
የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የብአዴን ከፍተኛ ሹሞች ለመጪው ምርጫ ይረዳቸው ዘንድ በተለያዩ የአማራ
ክልል በሚገኙ ወረዳዎች የህዝብ ተወካዮችን እየዞሩ በማነጋገር ላይ ሲሆኑ፣ የህዝቡ ተወካዮች ግን ችግሮቹን ሳይፈራ እያቀረበ ነው።
አንድ አስተያየት ሰጪ “የኢትዮጵያ መብራት ዝናብ የሚፈራ ነው” በሚል ዝናብ በዘነበ ቁጥር መብራት እንደሚጠፋባቸው ተናግረዋል። “ቋራ የሽፍታ አገር ነበረች” ያሉት አስተያየት ሰጪው፣ የአጼ ቴውድሮስ
አገር የሆነቸው ቋራ እናቶች በወሊድ የሚሞቱባት፣ የመንግስት ሰራተኛው እየፈለሰ የሚሄድባት የተረሳች ከተማ ሆናለች ብለዋል።
አንዲት ሴት አስተያየት ሰጪ ደግሞ የአጼ ቴዎድሮስ ሃውልት እስካሁን በቋራ አለመሰራቱ ጥያቄ እንደፈጠረባት ገልጻ፣ የመብራት፣ የዘይት እና የስኳር ችግር እንዳማረራቸው ተናግራለች።
ወደ ደጋው የሚኖረው የቋራ ህዝብ  በኢህፓ፣ በደርግ፣ በኢህአዴግና በኢዲዩ ሲሰቃ እንደነበር ያስታወሱት ሌላ አስተያየት ሰጪ፣ አሁንም በመሰረታዊ አግልግሎት አሰጣጥ እየተቸገረ መሆኑን ገልጸዋል
የመብራት ስራው ሁሉ ” ፎርጅድ” ነው ያሉት ሌላ አስተያየት ሰጪ፣ የመብራት ችግር እንዳማረራቸው ገልጸዋል። እኝሁ አስተያየት ሰጪ “አብዛኛው ነዋሪ ሰፊ መሬት አለ ተብሎ ወደ አካባቢው መጥቶ
እንዲሰፍር ቢደረግም፣ የተሰጠው 2 ሄክታር መሬት ቤተሰብን ለማስተዳዳር እንደላስቻለ ” ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials