Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, July 6, 2014

UK Where is your Citzen? Yemen and Weyane shall pay the price


የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ፣
_________________________________________________________________________________________________________________________
ከግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና
ተግባሪዊ የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪ
ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!


የመንን በተመለከተ
የየመን መንግሥት የዓለም ዓቀፍ ህግም ሆነ የየመን የራሷን ህግ በመተላለፍ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል።
ከመጀመሪያው ጀምሮ ለየመን መንግሥት የተደረገው ተማጽኖ ሰሚ ጆሮ አላገኘም። እስካሁንም ድረስ የየመን መንግሥት አቶ
አንዳርጋቸውን ማሠሩና ለወያኔ አሳልፎ መስጠቱ በይፋ አላመነም። እኛ ባለን መረጃ መሠረት በአይሮፕላን ማረፊያው ከማገት
ጀምሮ በልዩ በረራ ወደ ኢትዮጵያ እስከ መላክ ድረስ ያለውን የውንብድና ሥራ በየመን በኩል ሆኖ የሠራው ቀጥታ ተጠሪነቱ
ለየመን ፕሬዚዳንት የሆነው የስለላ ድርጅት ነው። በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ሊቀለበስ የማይችል እና በቀላሉ የማይፋቅ
ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የየመን መንግሥትና ሕዝብ ይህን እንዲያውቁት ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው የተግባር እንቅስቃሴ
አካል ነው።
የመንን በተመለከተ የሚቀጥለው ሳምንት ዘመቻችን ግብ ቁጣችንን የየመን ፕሬዚዳንት እና የየመን መንግሥት ብቻ ሳይሆን የየመን
ሕዝብም እንዲያውቅ ማድረግ ነው። የሚከተሉት ተግባራት ለአብነት ያህል ተጠቅሰዋል።

1. ለየመን ፕሬዚዳንት አዲስ መረር ያለ ደብዳቤ ተጽፎ በፋክስና በኢሜል በየመን መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶችና
ኤምባሲዎች አድራሻዎች መላክ። በመልዕክት መጨናነቅ ከሚገባቸው የየመን ተቋማት አንዱ አዲስ አበባ የሚገኘው
የየመን ኤምባሲ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሆናችሁ በዘመቻው የምትሳተፉ የሕዝብ ስልኮችን እንድትጠቀሙ፤
የኢንተርኔትና የፋክስ መልክቶችን ስትልኩ ራስን ለጉዳት በማያጋልጥ መንገድ መደረግ ይኖርበታል።
2. የየመን ኤምባሲዎችን ሥራ ማወክ በሚችሉ ሰልፎችና ተቃውሞዎች ማጨናነቅ። የፕሬዚዳንቱን ፎቶና የአገሪቱን
ባንዲራ ማቃጠል። ይህ በውጭ አገራት ብቻ መደረግ ያለበት ነው።
3. በውጭ አገራት በየከተሞች ለሚገኙ የየመን ኮሚኒቲዎች ደብዳቤ መፃፍና መንግሥታቸውን እንዲቃወሙ መገፋፋት፤
ይህንን ካላደረጉ ግን የመናዊያን ከመንግሥታቸው ጎን ተሰልፈው በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት እንዳወጁ የምንቆጥረው
መሆኑን በማያሻማ መንገድ መንገር፤
4. በየመን አየር መንገድና በማናቸው የየመን ቢዝነስ ላይ እቀባ ማድረግ፤ በቢዚነሶቻቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማድረግ።
ይህ ተግባር በኢትዮጵያም ከኢትዮጵያ ውጭም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መተግበር የሚኖርበት አቢይ ተግባር ነው።
5. በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የየመን ቢዝነስን መርጦ ምርቶቶቻቸው እና አገልግሎቶቻቸው እንዲጠሉ ማድረግ። ከእንግዲህ
በየመን ገንዘብ የተሠራ ወይም ከየመን የመጣ ብስኩትም ይሁን ሲጃራ የወገናች ደም የነካው እቃ ነው።

ብርታኒያን በተመለከተ

የእንግሊዝ መንግሥት ማድረግ የነበረበትን እና ማድረግ ይችል የነበረውን ሁሉ አድርጓል ብለን አናምንም። እርምጃው ፈጣን
አልነበረም፤ አሁንም አይደለም።
ስለሆነም እንግሊዝን በተመለከተ የዘመቻችን ግብ የእንግሊዝ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት በመንፈጉ መክሰስ እና ከአሁን በኋላም
ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለውና መሪያችንን እንዲያስፈታ መወትወት ነው። የሚከተሉት ተግባራት ለአብነት
ተዘርዝረዋል።

1. የእንግሊዝ መንግሥትን በህግ መክሰስ (ይህ በንቅናቄው ጽ/ቤት የሚሠራ ነው)፤ 2. ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ ደብዳቤ ጽፎ በፋክስና በኢሜል ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ለኤምባሲዎች በብዛት
መላክ። አንዱ ትኩረት የሚደረግበት ኤምባሲ አዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ
በዘመቻው የሚሳተፉ ወገኖች አስፈላጊው ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
3. በለንደን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደጃፍ፤ በሌሎች አገሮች ደግሞ በእንግሊዝ ኤምባሲዎች ቁጣ የተቀላቀለበት
የተቃውሞ ሰልፎችን ማካሄድ።

ወያኔን በተመለከተ

ወያኔን በተመለከተ የሚደረጉ ትግሎች በሙሉ ወያኔን ከስልጣን ማስወገድን ያለሙ መሆን ይኖርባቸዋል። ወያኔም ለመጣል
ትልቁን ድርሻ የሚያበረክተው ሕይወታቸውን ለመስጠት የቆረጡ ወገኖቻችን የሚያደርጉት ተግባር ነው፤ እንቀላቀላቸው።
በተለያዩ ምክንያቶች ወሳኙን ትግል መቀላቀል የማይችሉ ወገኖቻችን በያሉበት ሆነው ይህንኑ የሚያግዙ ተግባራት መፈጸም
ይኖርባቸዋል። እነዚህ ተግባራት፣ የወያኔ ባለሟሎች በገቡበት እየገቡ በማሳፈር እረፍት በመንሳት፤ የፈፀሟቸውን ወንጀሎች
በአደባባይ በመናገር እንዲሸማቀቁ በማድረግ፤ ማንነታቸው ለሸሪኮቻቸው ወይም ለሥራ ባልደረቦቻቸው በመንገር ወዳጅ
በማሳጣት፣ ቢዚነሶቻቸው እንዲከስሩ በማድረግ የፋይናንስ አቅማቸውን በማዳከም ረገድ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ቀላል
እንዳልሆነ ሊጤን ይገባል። ከዚህ አኳያ ሊደረጉ ከሚገቡ ተግባራት የሚከተሉት በምሳሌነት ተዘርዝረዋል።
1. በየአገሩ በተለያዩ ሽፋኖች ተሰግስገው ያለት ወንጀለኞች የወያኔ ሹማምንትና ደጋፊዎችን ለፍርድ ማቅረብ፤
2. የወያኔ ኤምባሲዎች ሥራ መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ መፍጠር፤
3. የወያኔ አባላትና ደጋፊዎችን ከያሉበት (በሰፈር፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በንግድ የተሰማሩ ..) በማደን ማስነወር፣ ማግለል፣
ማዋረድ፤ ከእነሱ ጋር አንዳችም የንግድም ሆነ የሥራ ትብብር አለማድረግ፤ በሥራዎቻቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳዎችን
ማካሄድ። ይህ ኢትዮጵያም ውስጥ በስፋት በሥራ ላይ መዋል ይኖርበታል።
4. ለሥራ ወይም ለሽርሽር የሚዘዋወሩ ከፍተኛ የወያኔ ባለሥልጣኖችና የጦር መኮንኖችን እየተከታተሉ ማሸማቀቅ፣
ማስነወር፣ መገታተር፤
5. የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በወያኔ መንግሥት የሚመሩ ቢዝነስች ላይ እቀባ ማድረግ፤ በእነሱ ላይ አሉታዊ
ቅስቀሳ ማድረግ። ይህ በኢትዮጵያም በውጭ አገራትም መደረግ ይኖርበታል።
6. በዌስተር ዩኒየን እና በወያኔ ደጋፊዎች በኩል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ አለመላክ፤ በየአካባቢው አማራጭ መላኪያ
መንገዶችን መፈለግ።
7. ከወያኔ ጋር የሚሠሩ የውጭ አገር ድርጅቶች ከወያኔ ጋር ያላቸውን ሽርክና እንዲያቋርጡ መወትወት፤ አልሰማ ካሉ
በቢዝነሳቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማካሄድ።
8. የምዕራብ አገራት ዩኒቨርስቲዎች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት እንዲመረምሩ ማሳሰብ። በወጉ ሳያስተምሩ ለወያኔ
ሹማምንቶች ዲግሪ የሚያድሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማስጠንቀቅ፤ ተግባሮቻቸውን ለተማሪዎቻቸው ጭምር መንገር
(ለምሳሌ University of Greenwich ከ International Leadership Institute ጋር ያለውን ግኑኝነት እንዲሰርዝ፣
እስከዛሬ የሰጣቸውንም የማስትሬት ዲግሪዎች እንዲመረመር የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፎ በብዛት በፋክስ መላክ፤ ተመሳሳይ
ደብዳቤ Open University እና ከወያኔ ጋር ተሻርከው ለሚሠሩ ዩኒቨርስቲና ኮሌጆች መላክ)
9. ይህ ዘመቻ ለጊዜው በወያኔ ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም፣ የሕዝቡን የነፃነትና የፍትህ ጥረት የሚያደናቅፉ የሀገር ውስጥም ሆነ
የውጭ አገር ዜጎች በሆኑ ቱጃሮች የተያዙ ቢዝነሶችም የዘመቻው ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ። በመጨረሻም የወጣቱ የማያልቅ የፈጠራ ችሎታ ከላይ በዝርዝሩ ውስጥ ያልተካተቱ ሆኖም ግን ውጤታማ የሆኑ የተቃውሞ
መግለጫ ዘዴዎች ያፈልቃል ብለን እናምናለን። ስለሆነም ዘመቻውን በየአካባቢው በሚገኝ ሀሳብና ፈጠራ ማዳበር ይቻላል።
ይህ ዘመቻ ወያኔን ከስልጣን ለማባረር ምድር ላይ ከምናደርገው የመረረ ትግል ጋር ሲቀናጅ የሚፈለገውን ውጤት ስለሚያስገኝ
ለነፃነቱ ግድ ያለው ዜጋ ሁሉ በሙሉ ሃይሉና አቅሙ ተሳትፎ እንዲያደርግ ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገራዊ
ጥሪ ያቄርባል ::

በመስዋዕትነት ድልን እንቀዳጃለን !!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials