Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, July 20, 2014

እውነት የማይመስሉ እውነቶች (ሰውን የማሰቃያ አይነቶች በኢትዮጵያ)

እውነት የማይመስሉ እውነቶች (ሰውን የማሰቃያ አይነቶች በኢትዮጵያ)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) አንድ ሰው ከታሰረ በኋላ፤ እንደ እስረኛ ሰባዊ መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። ይህንን ሰብአዊ መብት ለማክበር ቢያንስ የራሱን ህሊና፣ ህጉን ወይም አምላኩን መፍራት ይኖርበታል። ይህ ግን በኢትዮጵያ ስፍራ ያለው አይመስልም። የ እስረኛ አያያዝ በተቃራኒ መንገድ በምድራዊ ሲኦል የተሞላ፤ እጅግ አሰቃቂ ተግባር የሚፈጸምበት የ”ጥቁር ሽብር” ወቅት ላይ ደርሰናል። የድብደባ አይነቶቹን በቀይ ሽብር ዘመን ይፈጸማሉ ሲባል የምንሰማቸው አይነቶች የማይተናነሱ ወይም የከፉ ናቸው። እነዚህን የማሰቃያ መንገዶች አንዳንዱን እኛም ኢትዮጵያ በነበርንበት ወቅት የሰማነው እና የምናውቀው ሲሆን፤ ባለፉት አስር አመታት በኢትዮጵያ ያለው ሰብአዊ መብት አያያዝ በዘቀጠ ደረጃ ላይ መሆኑን ለመገንዘብ በፍቃዱ ጌታቸው ከኢትዮጵያ ያስተላለፈውን ዝርዝር መረጃ መመልከቱ በቂ ነው። የበፍቃዱ ጌታቸው ዘገባ ከዚህ ቀጥሎ እንዲህ ቀርቧል።
በእዉነት እንነጋገር ከተባለ ከአገሪቱ ኢኰኖሚ ይልቅ እጅግ በጣም በተራቀቀ መንገድ ያደገዉና በማደግ ላይ ያለዉ ነገር ቢኖር በመንግስት የፀጥታ አካላት በተቋቋሙት የምርመራ ቦታዎች ዉስጥ በንፁሀን የአገሪቱ ዜጐች ላይ የሚደረጉት የሰዉ ልጅ ህሊና ከሚገመተዉ ወጣ ያለ እጅግ አስቃቂ የሆኑ የድብደባ ዘዴዎች ናቸዉ …
ከነዚህ የድብደባ አይነቶች በጥቂቱ ብንጠቅስ ….
=> በአለንጋ፤ በኤሌትሪክ ሽቦ፤በአጠና የዉስጥ እግርና ጀርባ በመግረፍ የዉስጥ እግር እንዲበጣጠስ ማድርግ
=> በተበከለ ዉሃ ዉስጥ አንገት መድፈቅ
=> እጅን ወደሖላ አስሮ ጣራ ላይ በመስቀል አንጠልጥሎ ለረጅም ጊዜ ማቆየት
=> የሰዉን እግር በጩቤ ቆራርጦ እንኪነፈርቅ ከተደረገ በሖላ ጨዉና በርበሬ በመጨመር ማሰቃየት
=> እስረኞች በቂ እንቅልፍ እንዳያገኙ ማድረግ
=> በሴቶች ብልት ዉስጥ ባዕድ ነገር በመክተት(እንጨት፤የብረት ዘንግ፤የመስታዉት ስባሪ) ማሕፀናቸዉን መጉዳት
=> በወንዶች ብልት ላይ ዉሃ ወይም አሸዋ የተሞላ ጠርሙስ ማንጠልጠል
=> ጥፍር በጉጠት መንቀል፡ ጣትን በሚስማር መምታት፤ጣትን በትንሸ በትንሹ መቁረጥ
=>የጡት ጫፍን በጉጠት መወጠር
=>ደረቅ ሰዉነትን ወይም አጥንትን በጣዉላ መፋቅ
=>በጉጠት አፍንጫንና ጉንጭን መቁረጥ፤ የሴቶችን ጡት ላምባ በተነከረ ጨርቅ ማቃጠል፤ በሰለት መቁረጥ
=> ጀርባና ሆድን በእሳት ወይም ደግሞ በጋለ ካዉያ ማቃጠል
=> ከተመርማሪዉ አጠገብ ሰዉ መግደል
=> የሕክምና እርዳታ መከልከል
=> ተመርማሪዉን በ እሳት ነበልባል መለብለብ
=> ወ.ዘ.ተ.

No comments:

Post a Comment

wanted officials