Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, July 6, 2014

ወያኔ በህዝቦች ላይ የጀመረው ጥላቻ እንዴት እንደሚያስቀጽፈው በተግባር እናሳየዋለን !!!

ወያኔ በህዝቦች ላይ የጀመረው ጥላቻ እንዴት እንደሚያስቀጽፈው በተግባር እናሳየዋለን !!!
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የህዝቦች እኩልነት ያልተረጋገጠባት ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰብ መብቶች ለይስሙላ በሚሰበኩባት አገር ዜጎች ህግ ይከበር ብቻ ስላሉ በሌላው አለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አሸባሪ ተብለው ወህኒ የሚወርዱባት ኢትዮጵያ የሃይማኖት ምሁራን ከአያት ቅድማያቶቻቸውን የተረከቡትን እምነታቸውን በነጻነት ለማካሄድ ሲሰሩ ታፍሰው ለ እስር የተዳረጉባት አገር ፡ እያለማን ነው እየሰራን ነው በሚል ሽፋን ዘረፋ ላይ እና ዜጎችን ማሳደድ መግደል ማፈን እና ማሰር ላይ የተሰማራ መንግስት በነገሰበት አገር ውስጥ የምንኖር ተጨቋኝ ብዙሃን የህዝቦች የጋራ መተባበር እና ለለውጥ መነሳት አስፈላጊ እና እጅግ ወሳኝ ወቅት ላይ መሆኑን በማወቅ እያንዳንዳችን ከትግሉ በመቀላቀል ለነገው ትውልድ እና ለዛሬው እኛነታችን ነጻነት መሳካት ድርሻችንን ማበርከት ግድ ይለናል። ምንሊክ ሳልሳዊ
ወያኔ የያዘው መንገድ አጥፍተህ ጥፋ የሚል ጸረ ሰላም እና ጸረ ሕዝብ ከመሆኑም በላይ በጸረ አሸባሪነት ቁማር ምእራባውያንን ተገን በማድረግ ዜጎችን ለከፍተኛ እንግልት እና ሰቆቃ እየዳረገ ሲሆን በየትኛውም አለማችን ክፍል ያልታየ እና የሽብርተኝነት ውጊያ እናካሂዳለን የሚሉ ሃያላኖች እንኳን በተግብር በሃገራቸው ወንጀል እና ሽብር ሲፍጠር በፍጹም ዜጎቻቸውን የማይወነጅሉበትን ህግ ወያኔ ግን ህግ ይከበር የሰው ልጆች እኩልነት እና ነጻነት ይረጋገጥ ባሉ ዜጎች ላይ አጸያፊ እርምጃ ለመውሰድ እና የተቃወመውንም ይሁን የሚመክረውን ሁሉ አሸባሪ በማለት እየወነጀለበት ይገኛል። ይህ የማያዛልቅ የወያኔ ጸሎት ይህን ሰሞን አደገኛ ቅጽፈት ይዞበት መምጣቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል። ምንሊክ ሳልሳዊ
ወያኔ የጀመረው የስልጣን ማስረዘሚያ ስልት ራሱን እና በክሎኒግ ያባዛቸውን ጭፍሮቹን ወደ መቃብር እያወረደ መሆኑ ለአፍታ ቆም ብሎ ማስብ አልቻለም። ካለወያኔ መኖር የማይችሉ በጥቅም የታሰሩ በደረቅ ፖለቲካ የታወሩ እውቀት አልባ ካድሬዎች እና ሹምባሽ ደህንነቶች የአገሪቱ አንጡረ ሃብት በመዝረፍ እና ዜጎችን በመግደል በዚሁ የሚቀጠል መሆኑን አስበውት ከሆነ ተሳስተዋል። በአሁን ሰአት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለውጥ ፈላጊ ሃይል በመሆኑ ወደ ትግሉ መሰማራቱን ወደው ሳይሆን በግድ እውነትን እንዲውጡ እናደርጋቸዋለን። ለሃገሪቱ እና ለህዝቡ በማሰብ በሂደት ለውጥ ለማምጣት የተጀመረው ጉዞ ወደ በቀላዊ መንገድ የተቀላቀለ በመሆኑ በቅርብ ቀናቶች ውስት ወያኔ የጀመረው የማያዛልቅ ጸሎት እንዴት እንደሚይስቀጽፈው በተግባር እናሳየዋለን ። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment

wanted officials