Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, July 6, 2014

የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ የተጠረጠሩበትን የሽብርተኝነትን ክስ ተቃወሙ

የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ የተጠረጠሩበትን የሽብርተኝነትን ክስ ተቃወሙ

የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ኡቻላ (ቅጽል ስም መኖሪያ ካዋናሞ)፣ ሦስት የደቡብ ሱዳን ዜጐችና አራት ኢትዮጵያውያን የተጠረጠሩበትን የሽብርተኝነት ክስ በመቃወም ለፍርድ ቤት ሰኔ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. አቤቱታ አቀረቡ፡፡
የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ፣ በተለይ አቶ ኦኬሎ ከ1996 ዓ.ም. እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ በጋምቤላ ክልልና ከኢትዮጵያ ውጪ ሆነው ፈጽመዋል የተባለው የወንጀል ድርጊት በሽብርተኝነት አዋጁ የሚሸፈን አለመሆኑን በማስረዳት ተቃውመዋል፡፡
የተቃወሙበትን ምክንያት አቶ ኦኬሎ ሲያስረዱ፣ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ፀድቆ የወጣውና በሥራ ላይ የዋለው እሳቸው ባልነበሩበት ጊዜ በነሐሴ ወር 2001 ዓ.ም. ነው፡፡ በመሆኑም የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ባልነበረበት ጊዜ የተፈጸመ ድርጊት በአዋጁ የሚሸፈን አለመሆኑን ጠቁመው ክሱ ሊሰረዝ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ የተጠቀሱትን የሽብር ወንጀል ለመፈጸም ማቀድ፣ ማሴር፣ መዘጋጀትና መሞከር እንዳለበት የሚደነግገውን ሁሉም ተጠርጣሪ ተከሳሾች የተዘረዘሩትን ለመፈጸም የሚገልጽ አለመሆኑን ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ማመልከቻ ያስረዳል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ይልቁንም የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ጋሕነን) ወይም በጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋዴን) ውስጥ አባል ሆነው ይንቀሳቀሱ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ የሚያስረዳ በመሆኑ፣ ክሱ ከወንጀል መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 112 ድንጋጌ ጋር የሚጋጭ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ በመሆኑም የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 7(1)ን በመጥቀስ ክሱን በወንጀል መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 119 መሠረት ዓቃቤ ሕግ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ተጠርጣሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡
አቶ ኦኬሎ ከ1996 ዓ.ም. እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው መሥራታቸውን፣ በዚህ ወቅት በክልሉ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ለተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን የተዛቡና ወገንተኝነት የተሞላባቸው መግለጫዎችን መስጠታቸውን፣ በዚህም ምክንያት የብሔሩን ተወላጆች ለእልቂት ካነሳሱና ግጭቱን ካባባሱ በኋላ ከግል አጃቢያቸውና ከሾፌራቸው ጋር በመሆን አገር ከድተው መውጣታቸውን ጠቅሶ ዓቃቤ ሕግ ክስ አቅርቧል፡፡ አቶ ኦኬሎ ከአገር ከወጡ በኋላም ለኤርትራ ቴሌቪዥን፣ ለኦነግ ሬዲዮ፣ ለቢቢሲ፣ ለቪኦኤ፣ ለካናዳው ጋምቤላ ቱደይና ለሌሎችም መገናኛ ብዙኃን ግጭቱን የሚያባብሱ መግለጫዎች መስጠታቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ መጥቀሱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials