Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, July 19, 2014

የብአዴን እና የህወሃት ታጣቂዎች ተፋጠው እንደሚገኙ ታወቀ

የብአዴን እና የህወሃት ታጣቂዎች ተፋጠው እንደሚገኙ ታወቀ
የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በጸገዴ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ በአማራው ክልል ስር ተካለው የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎችን መውሰዳቸውን ተከትሎ ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ድርጊቱን በመቃወም ከትግራይ ክልል ታጣቂዎች ጋር ተፋጠው እንደሚገኙና በማንኛውም ሰአት ግጭት ይፈጠራል ተብሎ እንደሚፈራ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ወደ 400 የሚጠጉ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ወደ ድንበሩ የተጠጉ ሲሆን፣ በትግራይ ክልል በኩል ምን ያክል ታጣቂዎች እንደተሰለፉ ለማወቅ አልተቻለም።
የመከላከያ ሰራዊት ሆነ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው አይታዩም። አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ መሆኑንም ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል።
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በብአዴንና በህወሃት ታጣቂዎች መካከል የተጀመረው ግጭት እየሰፋ ሂዶ ኢህአዴግን ሊበትነው ይችላል በማለት እየተናገሩ ነው። የዚህን ዜና ዝርዝር እየተከታተልን እናቀርባለን።


No comments:

Post a Comment

wanted officials