ላለፉት ሀያ ሶስት አመታት የኢትዮዽያን አንጡራ ሀብት ወደ ትግራይ ሲያግዝ የኖረዉ ወመኔዉ የዘራፊ ቡድን እንደልማዱ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መራብቴ ወረዳ አለም ከተማ በጠራራ ጸሀይ ያደረገዉ የዝርፊያ ሙከራ ከህዝቡ የለመደዉን ይሁንታ ሳይሆን የተኩስ ሩምታ የጠበቀዉ ሲሆን እስካሁን ከወንበዴዉ ቡድን ሰባት ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን ከህዝብ ወገን አንድ የተሰዋ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።ዝርዝሩን በመረጃ አስደግፈን እንመለስበታለን ይከታተሉ።
በሰሜን ሸዋ የመርሃቤቴ ወረዳ ህዝብ ከወያኔ የፀጥታ ሃይሎችና ፌደራል ጋር ከባድ ውጊያ እያካሄደ ነው፣
ለወረዳው አለም ከተማና አካባቢዋ አገልግሎት ይውላል ተብሎ ከብዙ ጊዜ በሁአላ የገባውን መብራት የወያኔ መንግስት ህዝቡ የሚገለገልበትን መብራት አቁሞ ትራንስፎርሜሽኖቹን ነቅሎ ለአስቸኩአይ ጉዳይ ይፈለጋል ብሎ ወደ ትግራይ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የወረዳው 27ቱም ቀበሌ ተጠራርቶ ትራንፈርመሩን በቁጥጥር ስር በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት የወያኔ የፀጥታ ሃይሎች ጋር ኣሁን ድረስ ውጊኣ እያደረገ ሲሆን እስካሁን 7 የወያኔ ወታደሮች የሞቱ ሲሆን ከህዝብ ታጣቂ በኩል 1 ሞቷል።
ባሁኑ ሰዓት ወረዳውን መሉ በሙሉ የህዝቡ ታጣቂ ተቆጣጥሮት ይገኛል። ወያኔ ከአዲስ አበባና ከተለያዩ አካባቢወች ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው እያንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቁኣል።ሁኔታው የሚመለከታችሁ ወገኖች ሁሉ እየሆነ ያለውን ሁሉ በመከታተልና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉ ያስፈልጋል።