አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ኢቲቪ ለሁለተኛ ጊዜ አቀረባቸው።
በዚህ ቪዲዮ ውስጥ በድብቅ ካሜራ ከሚቀረጹት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ድምጽ በላይ ጎልቶ የሚሰማ አንድ የጣር ድምጽ አለ።
ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአቶ አንዳርጋቸው አንደበት ጥብ ጠብ የምትል ቃላት ለቃቅሞ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ትውላለች ብሎ ሲያስብ ገጣጥሞ አቀረበልን። ኢቲቪ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ እንዲህ ሲያደርግ ይሄ ሁለተኛው ነው። በዚህ ቪዲዮ ውስጥ የፖሊስ እና ህብረተብ ፕሮግራም፤ አቶ አንዳርጋቸው፤ ለኢህ አ ዴግ ፍጆታ የሚውል በርካታ መረጃ ሰጥተውናል ቢለንም አቶ አንዳርጋቸው ግን ለአሳሪዎቻቸው የሚጠቅምም ሆነ የጀመሩትን ትግል የሚጎዳ እዚህ ግባ የሚባል ነገር ሲናገሩ አለሰማንም አላየንም። ይሄንን እርስዎም ቪዲዮውን አይተው የሚያረጋገጡት ነው።
ይልቅስ በዚህ ቪዲዮ ውስጥ በድብቅ ካሜራ ከሚቀረጹት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ድምጽ በላይ ጎልቶ የሚሰማ አንድ የጣር ድምጽ አለ። እርሱን የሰሙ ጊዜ ”ሰዎች እንዲህ እየተገረፉ እንኳን ግንባት ሰባት ጷግሜ ሰባት ነህ ቢሉህ ታምናለህ” እንዳለው ወዳጃችን፤ ይሄ ልጅ ምንስ ብሎ ቢናገር ማን በርሱ ይፈርዳል…! የሚያስብል ነው።
እየተገረፈ ላለው ወንድማችን መቻሉን ለገራፊዎችም ልቦና እንዲሰጣቸው እንመኛለን፤ ግን ይህንን የጣር ድምጽ እንዲህ በአደባባይ የኢትዮጵያ ህዝብ ያየዋል ይሰማዋል ብለው በሚያስቡት ቴሌቪዥን ሊያቀርቡት ለምን ፈለጉ ገመናቸውን ለማውጣት የውስጥ አርበኞች የሰሩት ስራ ይሆን ወይስ ለማስፈራራት ሆነ ተብሎ የተለቀቀ…!
የሆነው ሆኖ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚበቃኝን ያክል ስላላልኩ እመለስብት ይሆናል… ለጊዜው ግን እንሆ የኢቲቪ ቪዲዮ፤https://www.youtube.com/watch?v=j5E-GkjMyd8
Abe tokichaw
No comments:
Post a Comment