ሰማያዊ ፓርቲ ህዳር 18 ህዝባዊ ስብሰባ ጠራ • መስተዳደሩ ለ5ኛ ጊዜ ማሳወቂያ ደብዳቤውን አልቀበልም ብሏል • ‹‹መልካም አስተዳደር የሚባለው ከወሬ ያለፈ እንዳልሆነ ያሳያል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት –
ሰማያዊ
ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር ውይይት ለማድረግ ህዳር 18/2008 ዓ.ም በመብራት ኃይል
አዳራሽ ህዝባዊ ሰብሰባ እንደሚያደርግ ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
ይሁንና የማሳወቂያ ደብዳቤውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት በአካል ለማድረስ ጥረት ቢደረግም በሰራተኞቹ ዘንድ ለአምስተኛ ጊዜ ‹‹ኃላፊዎቹ የሉም፡፡ እኛ አንቀበልም›› መባላቸውን ም/ሊቀመንበሩ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
‹‹ጠዋት ስንሄድ፣ ከሰዓት ኑ፣ ከሰዓት ስንሄድ፣ ስብሰባ ላይ ናቸው ጠዋት ኑ እያሉ 5 ጊዜ አንቀበልም ብለውናል፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ‹‹ለአንድ መስሪያ ቤት ደብዳቤ ለማድረስ በመዝገብ ቤት አሊያም በፀኃፊ በኩል መቀበል በቂ ነው፡፡ ኃላፊውን የግድ መጠበቅ አያስፈልግም ነበር፡፡›› ያሉት ኢ/ር ይልቃል ‹‹ይህ አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ ህገ መንግስታዊ መብትን የሚያግዱበት ስልት ነው›› ብለዋል፡፡
ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ስለመልካም አስተዳደር በሚያወሩበት በአሁኑ ወቅት አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ መብትን እያገዱ መቀጠላቸው መልካም አስተዳደር የሚባለው ከወሬ ያለፈ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው›› ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ለ5ኛ ጊዜ የሰማያዊ ፓርቲን የስብሰባ ማሳወቂያ ደብዳቤ በአካል መቀበል ባለመፈለጉ ፓርቲው ደብዳቤውን በሪኮመንዴ ለመላክ መገደዱን ፓርቲው ለፅ/ቤቱ በላከው ደብዳቤ ላይ አመላክቷል፡፡ በዚህም መሰረት ዛሬ ህዳር 1/2008 ዓ.ም ፓርቲው ማሳወቂያውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት በሪኮመንዴ መላኩን ሊቀመንበሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

No comments:
Post a Comment