Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, November 29, 2015

በሚቀጥለው ወር ለሱዳን ሊሰጥ የታሰበው የ ኦሮሞ፥የጋምበላ፥ የ አማራ ክልል መሬት ጉዳይ ለመቃወም እንነሳ

ለሱዳን በሚቀጥለው ወር የሚሰጠው ድንበር በርካታ ታሪካዊ ቦታዎችን ያቀፈ ነው።
ለሱዳን ሊሰጥ የታሰበው መሬት ጉዳይ አሁንም አወዛጋቢነቱን ቀጥሏል


በዳግማዊ አፄ ምንሊክ ዘመን በወቅቱ የሱዳን ቅኝ ገዢ የነበረችው የእንግሊዝ ተወላጅ የሆነው ጉዌን የተባለ ግለሰብ ያለማንም ፈቃድ የሱዳንን ካርታ አዘጋጅቶ ለእንግሊዝ መንግሥት ያቀረበ ሲሆን የእንግሊዝ ነገሥታቶች በካርታው ዙሪያ ከኢትዮጵያው ንጉሥ አጤ ምንሊክ ጋር ሳይስማሙ በመቅረታቸው የእንግሊዝ ፍላጎት ሳይሳካ ቀረ ሆኖም ጊዜ እና ዘመን ሲጠብቁ የኖሩት የሱዳን መሪዎች ፀሎታቸው ሰምሮ ኮትኩተው ያሳደጉት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም በተቃራኒ የቆመ ሕወሐት የተባለ መንግስት አገኙ ጫካ እያሉ እኔ የትግራይ ገዢ እንጂ የተቀረው የኢትዮጵያ መሬትን ጉዳይ እንደፈለጋችሁ በሚሉ ምክንያቶች ስምምነቶች ላይ የተፈራረሙ በመሆኑ ሕወሐት ስልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ ይህ ስምምነት ይፈፀም ዘንድ ቀን ሲጠብቁ ኖረው ዛሬ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ ደርሰዋል።
ለሱዳን የሚሰጠው መሬት ከጎንደር ተነስቶ ኦሮሚያን ቆርሶ የጋምቤላ ምድር ድረስ የሚደርስ ሲሆን ርዝመቱ እስከ1600 ኪሎ ሜትር ይደርሳል ይህም ማለት ምን አልባት ከአዲስ አበባ ዳሕላክ ወደብ የሚደርስ መሬትን ያህል እኩሌታ ማለት ነው
ይህ የሚሰጠው መሬት ወደኢትዮጵያ ድንበር ከ47 እስከ 50 ኪሎ ሜትር የሚገባ መሆኑም ታውቋል ሌላው አስደንጋጩ ጉዳይ የኢትዮጵያ ንጉሥ የነበሩት አጤ ቴዎድሮስ የተማሩበት ማህበረ ሥላሴ የተሠኘው ገዳምም በድንበር ማካለሉ ስምምነት ምክንያት የሱዳን አካል የሚሆን ሲሆን አፄ ዮሐንስ ከሱዳን ማህዲስቶች ጋር ጦርነት ላይ በነበሩበት ወቅት የተሰዉበት ሞፈር ውሃ የተሰኘው ታሪካዊ ቦታም አብሮ ለሱዳን የሚሰጥ ይሆናል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ የአማራ፣ የኦሮሚያ እና የጋምቤላ ተወላጅ የሆኑ በድንበሩ ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜግነታቸውን እንዲለውጡ ወይም አካባቢውን ለቀው ሊሰደዱ የሚችሉበት አጋጣሚ ሰፊ ነው።
ከዚህ ቀደም እንዳልኩት የሕወሐት መሪዎች ትልቁ ችግራቸው ለሱዳን ተላልፎ የሚሰጠው መሬት የአማራና የኦሮሞ እንጂ የኛ አይደለም የሚል የዘረኝነት ልክፍት ውስጥ መግባታቸው ነው።
ስለዚህ እኛው መሬታችን ለሱዳን ሊሰጥብን የተፈረደብን የ ጋምቤላ የ አማራ የኦሮሞ እና ሌሎችም በ አንድላይ ሆነን እንቃወም። ወያኔን እንኩዋን ሌላ መሬት ለሱዳን መሰጠት ይቅርና ያስወሰድክብንን ክልሎች ሁሉ መልስልን ለማለት እንነሳ።

አብርሃም

No comments:

Post a Comment

wanted officials