Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, November 29, 2015

ያልተዘመረላቸው ጀግና ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ!

ያልተዘመረላቸው ጀግና ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ!
==============================
ቀኑ ዓርብ ሚያዝያ 16/2001 ዓ.ም ነበር ። ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌድራል ልብስ የለበሱ ፖሊሶች መሳሪያቸውን አቀባብለው ወደቤት በመግባት <<ስልካችሁን አጥፉ ወደማንም እንዳትደውሉ >> በማለት ለወ/ሮ እማዋይሽ ቤተሰቦች ትእዛዝ ይሰጣሉ ። ቀጥሎም ቤቱን ለመፈተሽ የተፈቀደላቸውን ወረቀት እያሳዩ << ቤት ለመፈተሽ ነው የመጣነው ወ/ሮ እማዋይሽ በቁጥጥር ስር ውለሻል >> በማለት የመጡት ደህንነቶች እና የፌድራል ፖሊሶች ወ/ሮ እማዋይሽን አሳወቋቸው ። ቀኑ ዓርብ ስለነበረ ወ/ሮ እማዋይሽ ሰለሚፆሙ ገና ከስራ ገብተው የሚበላ እየጠየቁ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት ምግብ አፋቸው ላይ ሳያደርጉ ይዘዋቸው ወጡ ።
ወ/ሮ እማዋይች ከቤታቸው ከተወሰዱ ለ4 ወር ከማንም ባለመገናኘታቸው በህይወት ይኑሩ ወይም አይኑሩ የሚያውቅ አልነበረም ። አንድ ቀን ከወ/ሮ እማዋይሽ ጋር አብራ ታስራ የነበረች አንዲት ሴት ትፈታና ከወ/ሮ እማዋይሽ ለልጃቸው ለናርዶስ መልእክት ይዛ ትመጣለች ። መልእክቱም << አንቺ ደህና ከሆንሽ ሽሮና ጎመን ሰርተሽ ላኪልኝ ። እኔ ደግሞ ደህንነቴን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ ። ደህና ካልሆንኩኝ ግን ያ ነገር ይቀራል ። >> የሚል ነበር ። በዚህ መንገድ ወ/ሮ እማዋይሽ ከልጃቸው ከናርዶስ ዘሪሁን ጋር ግኑኝነታቸውን ቀጠሉ ።
ወ/ሮ እማዋይሽ ሕገ - መንግስቱን በሃይል ለመናድ በህቡዕ ሰርተዋል በሚል በእነ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ መዝገብ የተከሰሱት ናቸው ። 25 ዓመት እስር የተፈረደባቸው ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ዛሬም በእስር ይገኛሉ ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials