Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 10, 2015

በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናት በቤ/ክርስቲያናቱ እንዳያገለግሉ አገደ* አቡነ ሚካኤል የሲኖዶሱ ረዳት ጸሐፊ ሆነው ተሾሙ




* በፖለቲካው አሸባሪ ብሎ እንደሚፈርጀው ሁሉ በተሐድሶ ስም በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥ ያሉ መምህራንን መንግስት ባሰማራቸው ካድሬ ሰባኪያን ለማጥቃት እየተሞከረ ነው
* የጳጳሳት አስመራጭ ኮሚቴዎችን ስም ዝርዝር ይዘናል
* ከ9 በላይ አዳዲስ ጳጳሳት ይሾማሉ
* አቡነ ሚካኤል የሲኖዶሱ ረዳት ጸሐፊ ሆነው ተሾሙ


የቅዱስ ሲኖዶሱ ረዳት ዋና ጸሐፊ ሆነው የተሾሙት አቡነ ሚካኤል

(ተጨማሪ የዘ-ሐበሻ ሰበር ዜና) በኮለምበስ ኦሀዮ; ከጥቅምት 24 እስከ ጥቅምት 26, 2008 ዓ.ም በደብረ መድሃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል በተደረገው የስደተኛው ሲኖዶስ ዓመታዊ ጉባኤ አዳዲስ መመሪያዎችን ማውጣቱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

ከዚህ በፊት በነበረው የዘ-ሐበሻ ሰበር ዜና ቅዱስ ሲኖዶሱ በ እድሜ መግፋት ምክንያት ብዙ ለመስራት በማይችሉት አቡነ መልኬጼዲቅ ረዳት ዋና ጸሐፊ የሾመ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል:: በዚህም መሠረት በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ረዳት ሊቀጳጳስ አድርጎ የሾማቸው ብጹዕ አቡነ ሚካኤል መሆናቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል:: ብጹዕ አቡነ ሚካኤል የምዕራብ ካናዳ ሃገረ ስብከት (የካልጋሪ) ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ናቸው:: አዲሱ የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አብዛኛውን የአቡነ መልከጼዲቅን ሥራ ተክተው እንደሚሰሩ በጉባኤው ጸድቆላቸዋል::

በዚህ ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው ሲኖዶሱ በቅርቡ ከ9 በላይ ጳጳሳትን ይሾማል:: አዲስ የሚሾሙትን ኤጲስ ቆጶሳትን ለማስመረጥም ከቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ከምዕመናኑ አስመራጭ ኮሚቴዎች መመረጣቸውን ያስታወቁት ምንጮቻችን ስምዝርዝራቸውን አድርሰውናል::

በዚህም መሠረት አዳዲስ የሚሾሙትን ጳጳሳት የሚያስመርጡት ሰዎች
1ኛ. አቡነ ሚካኤል
2ኛ. ሊቀ ካህናት ምሳሌ
3ኛ. መምህር ልዑለ ቃል (የፓትርያርኩ ጸሐፊ)
4ኛ. መምህር ፍሬሰው
5ኛ. ቀሲስ ልሳነወርቅ (ከአውሮፓ)
6ኛ ቀሲስ መንግስቱ
7ኛ ዶ/ር አምባቸው (ከምእመናን) ናቸው:: በአማካሪነት ደግሞ ብጹዕ አቡነ ኤሊያስ ተመርጠዋል::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ አዳዲስ የሚሾማቸውን ጳጳሳት (ኤጲስ ቆጶሳት) በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ባሉ ሃገረ ስብከቶች ያስቀምጣል:: በዚህም መሠረት:

ለአውሮፓ 2
ለአፍሪካ 1
ለካናዳ 2
ለአውስትራሊያ 1 አዳዲስ ጳጳሳት የሚሾሙ ሲሆን ቀሪዎቹ በአሜሪካ ይሾማሉ ተብሏል::

በኦሃዮ በተደረገው የሲኖዶሱ ጉባኤ አዲስ የወጣው መመሪያ ደግሞ በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ውስጥ እያገለገሉ በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥም የሚያገለግሉ ካህናትን ይመለከታል:: ሲኖዶሱ ባወጣው መመሪያ መሠረት በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ውስጥ እያገለገሎ በተጨማሪም በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናት ከዚህ በኋላ አንዱን መምረጥ ይኖርባቸዋል:: ይህ ካልሆነ ግን በሁለቱም ሲኖዶሶች ውስጥ በአንድ ጊዜ ማገልገል እንደማቻል ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል::

በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶሱ ባወጣው መግለጫ መንግስት ተቃዋሚዎችን አሸባሪ ብሎ እንደሚከሰው ሁሉ አሁን ደግሞ በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥ እያገለገሉ ያሉትን ካህናት እና መምህራንን ተሐድሶ በሚል ከሕዝብ ጋር ለመነጠል የሚደረገውን ሴራ አውግዟል:: ሕዝቡ እንዲህ ያለውን ማደናገሪያ እንዳይቀበል የጠየቀው ሲኖዶሱ ሆን ብሎ በተሐድሶ ስም ስደተኛው ሲኖዶስን ለማጥቃት የሚደረገውን ሴራ እንዲያወግዝ አሳስቧል:: ሲኖዶሱ እንዳሳሰሰበው መንግስት ያሰማራቸው ካድሬ ሰባኪያን የስደተኛው ሲኖዶስን ስም ለማጥፋትና ሰባኪያኑን ከሕዝቡ ለማግለል የሚያደርጉትን ሴራ ሕዝብ ሊቃወመው ይገባል::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች አዳዲስ ጳጳሳት ሆነው የሚሾሙትን እጮዎች ስም ዝርዝር አድርሰውናል – ከሰሞኑ ዝርዝራቸውን እናሳውቃችኋለን::

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48090#sthash.I41s6O4n.dpuf

No comments:

Post a Comment

wanted officials