Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 10, 2015

አርቲስት ደበበ እሸቱ በምርጥ ተዋናይነት ተሸለሙ

አርቲስት ደበበ እሸቱ በምርጥ ተዋናይነት ተሸለሙ
ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ቀያይ ቀምበጦች በሚለው ፊልም ላይ ባሳየው የተዋናይነት ብቃቱ በካናዳ ቫንኩቨር የGolden Leopard Award ተሸላሚ ሆኗል። አርቲስት ደበበ ሽልማቱን በተወካዩ በኩል ተቀብሏል። የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተሩ ኢትዮዽያዊዉ ቤተ እስራኤላዊዉ ባዚ ጌቴ ሲሆን፣ ፕሮዲዩሰሩ ደግሞ ኢላድ ፔሌግና የእስራኤል የፊልም ስራ ማዳበሪያ ቢሮ ናቸው። በተለያዩ የእስራኤል ከተሞች የተሰራውን ፊልም ለማዘጋጀት አራት ወራት የፈጀ ሲሆን፣ አርቲስት ደበበ አንድ ወር የቤተ እስራኤላዊያንን አኗኗር እና የቤተሰብ ግንኙነት ለማጥናት እንዲሁም ሌላ ተጨማሪ አንድ ወር ቤተ እስራኤላዊያን የእድሜ ባለፀጎች ቀናቸውን በሚያሳልፉበት ማእከል በመገኘት ባህሪያቸውን በማጥናት፣አንዳንድ ጥያቄም በማንሳት፣ ግንዛቤ የማግኛ ጊዜ ማሳለፉን ገልጿል። ፊልሙ በእስራኤል ከተማ በይፋ ከመከፈቱ አስቀድሞ በእየሩሳሌም በተካሄደው አመታዊ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ቀርቦ የክሪቲክ አዋርድን እና የተመልካቾች አዋርድ ተሸላሚ ነበር። አርቲስት ደበበ በሽልማቱ ስነ ስርአት ላይ ለመገኘት ያልቻለው በጊዜ መጣበብና ቀደም ተብሎ በተያዘ የሃኪም ቀጠሮ ምክንያት ነው። አርቲስቱ "ስራው አድካሚ ቢሆንም ለዚያ ድካም እንዲህ ካለ ዝናን ከተጎናፀፈ ፌስቲቫልና ዳኝነቱ የሚለካብት መመዘኛው ነጥብ ሃያል በሆነበት የአምስቱም ዳኞች ይሁንታ በአንድነት ካልተገኘ ሽልማት ማግኘት በማይቻልበት ፌስቲቫል ላይ ለዚህ ክብር መብቃት ከደስታም በላይ የሆነ ልዩ ደስታ ነው። ሽልማቱ የኔ ብቻ ሳይሆን በፌልሙ ስራ ላይ የተሳተፉት፤ በተለይም ምን ጊዜም ከጎኔ ሆነው አለን ከሚሉኝ ውድ ባለቤቴ እና ልጆቼ ጋር የምካፈለው ሽልማት ነው። ብርታቱን ሰጥቶ ለዚህ ያበቃኝን ዓምላክ አመሰግናለሁ።" ሲል አርቲስቱ ሽልማቱ ስለፈጠረበት ደስታ ተናግሯል። ቀያይ ቀምበጦች በተለያዩ የአለም ክፍሎች በመታየት ላይ ነው።
http://ethsat.com/

No comments:

Post a Comment

wanted officials