ጽዮን ግርማ / VOA
ፍሪደም ሃውስ (Freedom House) መቀመጫውን እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገና በመናገር ነጻነት ላይ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡ይህ ተቋም መንግሥታት ለሕዝቦቻቸው የሚሠጡትን የኢንተርኔት ነጻነት አጥንቶ እያንዳንዱ ሀገር ያለበትን ደረጃ ‹‹Freedom on the net 2015 ›› በሚል ርዕስ ስር ሪፖርት አውጥቷል፡፡ በዚህ ሪፖርት ሰንጠረዥ‹‹ኢትዮጵያ ከቻይና፣ከሦሪያ እና ከኢራቅ ቀጥሎ ምንም ዓይነት የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ተብላለች፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ—
ፍሪደም ሃውስ(Freedom House) የተሰኘው ተቋም “Freedom on the net 2015” የተሰኘው ይህ ሪፖርት በዛሬው ዕለት በቀረበበት ወቅት፤ሪፖርቱን ያዘጋጁት ባለሞያዎች፣የዩኒቨርስቲ መምሕራንንና ተመራማሪዎች፣የጎግል መስሪያ ቤት ባለሞያ፣ከመናገር እና ከመጻፍ ነጻነት ጋር የሚሠሩ ተቋማት ተወካዮች በአጠቃላይ ከሰብዓዊ መብት ጋር የሚሠሩ ግለሰቦችና የድርጅት ተወካዮች ተገኝተው ሪፖርቱን አዳምጠዋል፡፡ ተወያይተዋል፡፡
ማንኛውም ሰው የኢንተርኔት የመረጃ መረብን ተጠቅሞ ያለምንም ቅድመ ምርመራ እና ችግር ሐሳቡን በነጻነት የማስተላለፍ መብት እንዳለው የሚጠቅሰው ይህ ሪፖርት በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥታት የሕዝቦቻቸውን የኢንተርኔት ነጻነት እያፈኑ፣አገልግሎቱንም እየዘጉ ከዛ ባለፈ ደግሞ እያሠሩ እንደሚገኙ ይጠቅሳል፡፡
አገራት ለሕዝቦቻቸው የሚሰጡትን ነጻነት በሦስት ቀለማት ከፍሎ ያስቀመጠው የሪፖርቱ አንድ አካል የኾነው አንድ ሠንጠረዥ ኢትዮጵያ ከቻይና፣ከሦሪያ እና ከኢራቅ ቀጥሎ “የባሰ አፈና” ባለባቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ ያስቀምጣታል፡፡ በሌላኛው የሪፖርቱ ክፍል ደግሞ “ኢትዮጵያ የኢንተርኔትም ኾነ የመናገርና መጻፍ ነጻነት ያለባት አገር አይደለችም” ይላታል፡፡
Source: VOA Amharic
No comments:
Post a Comment