Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, November 13, 2015

የጀመርነው ጉዞ የሚደመደመው ዲሞክራሲያዊ ስርአት ሲፈጠር ብቻ ነው!!

የጀመርነው ጉዞ የሚደመደመው ዲሞክራሲያዊ ስርአት ሲፈጠር ብቻ ነው!!

ኢትዮጵያችን ህዝቧ በፈቀደው ስርአትና በመረጠው መሪ ተመርታ በታሪኳ ባይታወቅም ህልውናዋ አደጋ ላይ የወ ደቀበት ወቅት ቢኖር ግን ዛሬ የምንገኝበት የወያኔ ዘመን ብቻ ለመሆኑ ጥያቄ የለውም። ለዚህም ነው ዛሬ አርበኞች ግንቦት ሰባት የተያያዘው ትግል የስልጧን ሳይሆን ሀገር የማዳን የህልውና ትግል የሆነው። ይህ ሀገር የማዳን ሁለገብ ትግል የሚጠ ናቀቀውም በዚያች ምድር አንባገነንነትም ሆነ ዘረኝነት ዳግም የማይታይበት ይልቁንም ህዝብ የስልጣን ባለቤትነቱ ፍፁም ሲረጋገጥ መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል።
እንግዲህ ሀገር ከጥፋት ህዝብም ፖለቲካዊና ሰዋዊ መብቶቹን ተጎናፅፎ በመከባበር በአንድነት የሚኖርበትን ኢትዮ ጵያ ለመፍጠር የተጀመረው ሀገር አድን ትግል ከቀን ወደ ቀን እየጎለበተና አድማሱን እያሰፋ መሄዱ ደግሞ በተቃራኒው ለቆ መው የወያኔ ቡድን ስጋትና ድንጋጤ መፍጠሩ ወያኔ ዛሬም እንደ ትናንቱ የተለመደውን አሰልቺ የባዶ ተስፋ ድራማውን በ ማቅረብ የተገፋውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከትግል ለማዘናጋት ደፋ ቀና ሲል የሚታየው። በተለይም በሰሞኑ የመልካም አስተ ዳደር ችግር በሚል መወያኔ ቱባ ሹማምንት ተደረገ የተባለው ውይይትን እንደ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል።
ነገር ግን ገና ከጅምሩ የወያኔ ዘረኝነት ሀገራችንንና ህዝቧን መውጫ ከማይገኝለት አዘቅት ውስጥ እንደሚከት በአደ ባባይ የተናገሩ ምርጥ የሀገሪቱ ልጆች ስንቶች በግፍ ተገደሉ፤ ስንቶች ወህኒ ተወረወሩ፤ ስንቶች ተሰደዱ … ይህ ደግሞ ዛሬ ከወያኔ ቱባ ሹማምንት አንደበት ሀገራችን የገባችበት የችግር አረንቋን ጥልቀት መስማት የገፈቱ ቀማሽ ለሆነው መላው የኢ ትዮጵያ ህዝብ የአዋጁን በጆሮ ከመሆን ያለፈ ያለሞኑን ሊያውቁት ይገባል።
ዋናው ዛሬ ለምንገኝበት የመልካም አስተዳደር ችግር መፍትሄ የሚገኘው የችግሩ ዋነኛ ፈጣሪዎችና ጎንጓኞች ባማረ ወንበር ተቀምጠው በቴሌቪዥን መስኮት የሚያቀርቡት ዲስኩር ሳይሆን ዘረኝነትንና አንባገነንነትን ከሀገሪቱ ምድር ላይ ጠራ ርጎ በምትኩ እያንዳዱ ኢጥዮጵያዊ ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ የተከበረበት፤ የኢኮኖሚ ብልፅግናና ማህበራዊ ፍትህ የ ሚ ያገኝበት፤ የዜጎች ህይወት ደህንነትና ጥቅም የተከበረበትና የህዝቧ አንድነትና ትስስር የጠነከረበት ሀገር ሲኖረን መሆኑን አምኖ ለተግባራዊነቱም እየተቀጣጠለ ከሚገኘው ሀገር አድን ትግል መቀላቀል ብቻ ነው። ለዚህም ደግሞ እያዘ ቀዘቀች ያለ ችው የወያኔ ፀሀይ ፍፁም ከመጥለቋ በፊት ጊዜው ዛሬ ብቻ መሆኑን አጥብቀን ማሳሰብ እንወዳለን።
በሌላ በኩል ደግሞ ዘረኛውና ዘራፊው የወያኔ ቡድን የደገሰልህን ግፍና ሰቆቃ ቀማሽ የሆንከው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በልጆችህ የተለኮሰውን የነፃነትና ሀገር የማዳን ትግል ችግራችን፤ ሰቆቃችንና መከራችን አብቅቶ ሁላችንም በሰላም በ እኩልነት፤ በፍትህና በአንድነት የምንኖርባት ሀገር ለመፍጠር መሆኑን አምነህ የጀመርከውን ፍልሚያ በመላው ሀገሪቱ ውስ ጥ ይበልጥ የማቀጣጠሉን ስራ በወያኔ ባዶ የተስፋ ዲስኩር ሳትዘናጋ የብርሀኑን ቀን ለማቅረብ በተቀናጀ መልኩ ትግልህን መ ቀጠል እንደሚገባህ አርበኞች ግንቦት ሰባት አጥብቆ እያሳሰበ የተጀመረው ወደ ነፃነት ጉዞ የሚደመደመው ሀላችንንም በእክ ልነትና በአንድነት አቅፋ የያዘች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ስትሆን ብቻ መሆኑን በድጋሚ ቃል ይገባል። ለዚህ ሁላችን ለምንመኛት ኢትዮጵያ እውን መሆን እኛ ከትግሉ የመጀመሪያ ረድፍ የተሰለፍን ልጆችህ የነፃነትና የሀገር ማዳን ትግላችን የሚጠይቀውንና አስፈላጊውን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንን በማረጋገጥ ነው።
ድል ለአርበኞቻችን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials