Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, November 25, 2015

ኤርትራዊው ታዳጊ ስደተኛ በኢትዮጵያ ራሱን አጠፋ Eritrean sucide in Ethiopia



ኤርትራዊው ታዳጊ ስደተኛ በኢትዮጵያ ራሱን አጠፋ
በቅርቡ ብዛት ያላቸው ታዳጊ ኤርትራዊያን ስደተኞች ከሚገኙበት የኢትዮጵያ የስደተኞች ካምፕ ራሳቸውን ለማጥፋት ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረጋቸውን አንደኛው ግን ራሱን ማጥፋቱን ቫይስ የተሰኘው የዜና አውታር ዘግቧል፡፡ወደ አውሮፓ ለመሻገር ኤርትራዊያን ወጣቶች በብዛት በባህር ሰምጠው መቅረታቸው የዕለት ተዕለት ዜና በሆነበት በዚህ ወቅት ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች ራሳቸውን ለማጥፋት መሞከራቸውና አንዱ ለሞት መዳረጉም አስደንጋጭ መሆኑን መረጃው ጠቁሟል፡፡
ጆብ ኦንያንጎ በኢትዮጵያ የስደተኞች ካምፕ የቶርቸር ጥቃት ለደረሰባቸው የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ለቫይስ በሰጡት መረጃ ‹‹የሚበዙት ስደተኞች ወደሶስተኛ አገር የሚሄዱበት ዕድል እንደሚፈጠርላቸው ተስፋ በማድረግ ይጠባበቁ የነበሩ ናቸው፡፡የጠበቁት ነገር ባለመሆኑም ተስፋ መቁረጥ ውስጥ በመግባታቸው ራሳቸውን ለማጥፋት እንደምክንያት ሆኗቸዋል››ብለዋል፡፡
ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነም በሰሜን ኢትዮጵያ ወደሚገኘው የስደተኞች ካምፕ በቀን 100 ኤርትራዊያን ታዳጊዎች ይገባሉ፡፡
መድሃንዬ አለም በካምፑ ለስደተኞች የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ሁኔታውን በማስመልከትም በካምፑ ለሶስትና ለአራት አመታት የቆዩ ስደተኞች እንደሚጨነቁና ራሳቸውን ለማጥፋት በአብዛኛው እንደሚሞክሩ ተናግረዋል፡፡
Source: Vice News

No comments:

Post a Comment

wanted officials