Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, November 25, 2015

በእውቀቱ ሥዩም===ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ቦታ የምታገኘው መንግስትን ብቻ ነው

 


እንግሊዝ ሀገር በሄድኩ ጊዜ የዛሬ ስንት እና ስንት መቶ አመት አካባቢ ሼክስፒር በጠጣበት ቡና ቤት ጠጥቼ ሼክስፒር በሸናበት ታዛ ስር ሸንቼ ወደ ሀገሬ የመመለስ ዕድል ገጥሞኛል።
.
ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ያለ ዕድል ማግኘት አይታሰብም። ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ቦታ የምታገኘው መንግስትን ብቻ ነው።
.
ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ከሳምንት በፊት ጤና ጣቢያ የነበረው ከሳምንት በኋላ ፖሊስ ጣቢያ ሆኖ ታገኘዋለህ እናም በሽተኛ ለመጠየቅ ያመጣኸውን ፍራፍሬ እስረኛ ጠይቀህበት ትመለሳለህ።

በዚህ አይነት:-
ከሳምንት በፊት ሙዚየም ከሳምንት በኋላ ጅምናዚየም።
.
ከሳምንት በፊት ላይብረሪ ከሳምንት በኋላ እኔ ነኝ ያለ ግሮሰሪ።
.
የሰውም ለውጥ ፍጥነት እንዲሁ ነው:-
ከወር በፊት ተላላኪ ከወር በኋላ አስመጭና ላኪ።
.
ከአመት በፊት የከባድ መኪና አሽከርካሪ ከአመት በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ።
ከአመት በፊት አድማ በታኝ ከአመት በኋላ የኳስ ተንታኝ ሆኖ ታገኘዋለህ።
.
በነገራችን ላይ የኳስ ነገር ሲባል አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ከሶስት ወራት በፊት መሰለኝ በአትሌቶችና በባለስልጣናት መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም የኳስ ግጥሚያ ተደርጎ ነበር። እና ኮመንታተሩ አትሌቶች ኳስ ሲይዙ
‘ኦ ••••• ቀነኒሳ ኳስ በእጁ ነክቷል አደገኛ ስህተት ‘ እያለ ትችት ሲያዘንብባቸው ይቆይና ባለስልጣኖች ኳስ ሲይዙ ይቅለሰለሳል።
.
.
‘አሁን ጀነራል ኳስ ይዘዋል ‘ ። ጀነራል አታለው አለፋ ለማለት ፈለገና አታለው የሚለው ቃል ክብር የሚነካ ስለመሰለው ጀነራል መስዋዕትነት ከፍለው አለፉ …..

No comments:

Post a Comment

wanted officials