Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, November 15, 2015

Breaking News:-ረዳት ፓይለት ሃይለምድህን አበራ ወንጀለኛ አይደለህም ነጻ ነህ ተባለ

Breaking News:-ረዳት ፓይለት ሃይለምድህን አበራ ወንጀለኛ አይደለህም ነጻ ነህ ተባለ


ኀዳር ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ረዳት አብራሪ የነበረውና በድርጅቱ ውስጥ ያለው ዘረኝነትና አድሎዋዊ አሰራር ስራዬን በነጻነት ለመስራት አላስቻለኝም በሚል ምክንያት ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የሆነውን ከአዲስ አበባ ተነስቶ በካርቱም በኩል አቋርጦ ወደ ጣሊያን ይበር የነበረን ቦይንግ 767-300 አውሮፕላን በመጥለፍ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ካሰረፈ በሁዋላ ጉዳዩን ሲከታተለው የነበረው ፍርድ ቤት ክሱ እንዲነሳ ወስኗል። ረዳት ፓይለት ኃይለመድህን አበራ ተላልፎ እንዲሰጣቸው የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ጉዳዩን ሲያይ የነበረው የስዊዘርላንድ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአእምሮ ጠበብቶች የሕክምና ውጤትን በመንተራስ ረዳት አብራሪው የስነልቦና ጭንቀት ተጠቂ በመሆኑ ከክሱ ሙሉ በሙሉ ነጻ እንደሆነና እንደማንኛውም ጥገኝነት ጠያቂ የውጪ ዜጋ ሕክምናውን እየተከታተለ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግለት በይኗል። ረዳት ፓይለት ኃይለመድህን አበራ ተላልፎ እንዲሰጣቸው የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ከመሞከራቸውም በተጨማሪ በሌለበት የ19 ዓመት ከ 6ወራት እስራት ተፈርዶበት እንደነበር ስዊዝ ኢንፎቴክ አክሎ ዘግቧል። ሃይለመድህን አበራ ምንም ጉዳት ሳያደርስ አውሮፕላኑን በሰላም ማሰረፉ ይታወቃል። ስዊዘርላንድ ውስጥ ጥገኝነት መጠየቅ እንደሚፈልግና ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለስ ዋስትና እንዲሰጠው በወቅቱ ጠይቆ ነበር።

No comments:

Post a Comment

wanted officials