Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, November 16, 2015

የብሪታንያ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጤንነት ያሳስበኛል አለ









የብሪታኒያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙትን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የጤንነት ሁኔታ አሳስቦት እንደሚገኝ በድጋሚ ገለጠ። የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ አስመልክቶ ትናንት ሰኞ በዚህ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ በሚገኘው የብሪታኒያ ኤምባሲ ለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ምላሹን በጽሑፍ የሰጠው ኤምባሲው አቶ አንዳርጋቸው ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ያሉበት ሁኔታ በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በአጠቃላይ አሳሳቢ መሆኑን አስታውቋል። በኢትዮጵያና በብሪታኒያ መካከል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ እንደሚገኝ በደብዳቤው የጠቀሰው ኤምባሲው ሀገሪቱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቋሚነት እንዲጎበኙና የህግ ምክር እንዲያገኙ ግፊትን እያደረገች እንደሆነ አመልክቷል።የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የሚቀጥል መሆኑን ልናረጋገጥ እንወዳለን ሲል ኤምባሲው ለሰልፈኞች በሰጥው ምላሽ አክሎ ገልጿል ። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዴቪድ ካሜሩንን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ደብዳቤ መጻፋቸውን አስታውቋል። ነዋሪነታቸው በዚህ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማና አካባቢዋ የሆነ ኢትዮጵያውያን በየሁለት ሳምንቱ በመሰባሰብ በብሪታኒያ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ እንደሚገኝ ይታወቃል ። በዋሺንግተን ዲሲ ከተማና አካባቢዋ በሚገኘው ግብረ ሀይል አስተባባሪነት በመካሄድ ላይ የሚገኘው ይኸው ሰላማዊ ሰልፍ የብሪታንያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚፈቱበትን ሁኔታ እንዲያመቻፍ የሚያሳስብ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪዎች ለኢሳት አስረድተዋል። የብሪታኒያ ባለስልጣናት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ ከማንሳት ተቆጥበው እንደማያውቁ የብሪታኒያ ኤምባሲ ለሰልፈኞቹ በሰጠው ምላሽ አክሎ አመልክቷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials