Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 17, 2015

ኢህአዴግ አባሎቹን ሂሳዊ ደጋፊና እና ጽንፈኛ ተቃዋሚ ሲል ከሁለት ከፈላቸው





ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሲመክር አሉኝ የሚላቸውን ደጋፊዎች በሁለት እንደሚከፍላቸውና ሁለቱም ለግንባሩ በስልጣን ለመቆየት ቀዳሚ የስጋት ምንጭ ናቸው ሲል ፈርጇቸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪዎች አቶ በረከት ስምኦን፣ የጠ/ሚኒስትሩ ሌላው አማካሪ አቶ አለበል ደሴ፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፣ የመረጃ መረብ ደህንነት የህዝብ አስተያየት ትንተና ክፍል ፣ የሁሉም የፖለቲካ ድርጅት ጽ/ቤት ሃላፊዎች በተወያዩበት መድረክ ላይ የድርጅቱ አባላት ምን እንደሚመስሉ አስተያየት ተሰጥቶበታል።

ኢህአዴግ እንደሚለው ግንባሩ በአንድ በኩል “ከኢህአዴግ ጋር አብሮ በመስራት ድክመቶችን እያስወገደ አስተማማኝ አብዮታዊ ሃይል ሆኖ እንዲፈጠር እድል ሊሰጠው ይገባል የሚሉ በአጭሩ ሂሳዊ ደጋፊዎች የሚባሉትን ደጋፊዎች የያዘ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ” ኢህአዴግ ጸረ ህዝብና ጸረ ዲሞክራሲ መሆኑን በግልጽ ያስመሰከረ ሃይል ነው በሚሉ ደጋፊዎች የተከበበ በመሆኑ፣ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ የሚቻለው ኢህአዴግ ተገርስሶ ዲሞክራሲያዊ መንግስት መመስረት ይኖርበታል” የሚሉ አባሎቹን የያዘ ነው ብሎአል።
ሁለቱም ሃይሎች ለግንባሩ ህልውና አደገኛ መሆናቸውን በግምገማው አስቀምጧል። በሌላ በኩል የኢህአዴግ መንግስት በገጠመው ከፍተኛ ርሀብ የተነሳ ለምርጫ ቅስቀሳ የተጠቀማባቸውን ትልልቅ ፕሮጀክቶችን መሰረዙ ታውቋል፡፡

ኢህአዴግ በረሃቡ ምክንያት በዚህ ዓመት አይጀመሩም ካላቸው ፕሮጀክቶች መካከል ስልጤ ዩኒቨርስቲ ፤አዊ ዩኒቨርስቲ ፤ ራያ ዩኒቨርስቲ ፤ ጋፋት ዩኒቨርስቲ ይገኙበታል።
የኢኮኖሚ ፋይናንስ ሚንስቴር በሩብ ዓመት የመላ ሐገሪቱ የገንዘብ ፍሰት ግምገማ ላይ እንዳስታወቀው፣ መንግስት ለረሃቡ ማስታገሻ ከካዝናው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ በማድረጉ ለምርጫ ቃል የተገቡ የዩኒቨርስቲ ፤ የሆስፒታል ፤የመንገድ ፤ የሐይል ማመንጫ ስራዎችን በዚህ ዓመት ለማከናወን አይችልም ብሎአል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials