Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 16, 2014

መድረክ ግንቦት 10 ቀን ለታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ የአዲስ አበባና የአካባቢዋን ነዋሪዎች ጠራ

መድረክ ግንቦት 10 ቀን ለታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ የአዲስ አበባና የአካባቢዋን ነዋሪዎች ጠራ


See full size image
መድረክ በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ መንግስት ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን በኃይል ለማፈን የሚወስዳቸው የኃይል እርምጃዎች እና ተፅዕኖዎች በአስቸኳይ ቆመው የሀገራችን ወቅታዊ እና መሰረታዊ ችግሮች በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ አግባብ እንዲፈቱ መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡
ስለዚህም የአዲስ አበባ እና የአከባቢዋ ነዋሪዎች ልክ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ከአራት ኪሎ በስተምስራቅ ወ.ወ.ክ.ማን አለፍ ብሎ ከሚገኘው የግንፍሌ ወንዝ ድልድይ ተነስቶ በሺ ሰማኒያ፣ በሚስማር ፋብሪካ እና በቀበና ወንዝ ድልድይ አድርጎ እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት ከሚያልፈው መንገድ ላይ ወደ ባልደራስ ታጥፎ በኤካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ኳስ ሜዳ /ታቦት ማደሪያ/ በሚባለው የመሰብሰቢያ ቦታ ድረስ በመገኘት የሰላማዊ ሰልፉ ተካፋይ እንዲሆኑ መድረክ ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል፡፡

ቀን ፡ እሁድ ግንቦት 10 ቀን ከ3 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት
ቦታ፡ መነሻው ከግንፍሌ ወንዝ ድልድይ ሆኖ መድረሻው በኤካ ክ/ከተማ በወረዳ 8 ኳስ ሜዳ ድረስ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials