Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 6, 2014

የአንድነትን ሰልፍ አስመልክቶ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በየክፍለ ከተማው የሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ርዕሰ መምህራንን ሰብስበው መመሪያ ሰጧቸው


የአንድነትን ሰልፍ አስመልክቶ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በየክፍለ ከተማው የሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ርዕሰ መምህራንን ሰብስበው መመሪያ ሰጧቸው
------------------------------------------------------------
መጋቢት 27 ቀን 2006 ዓ.ም ጠዋት በአዲስ አበባ የሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ርዕሰ መምህራንን የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ሰብስበው እሁድ ዕለት በተደረገው የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተገኙ መምህራንን ፈትሸው እንዲያወጡና እንዲያጋልጡ የሚል መመሪያ የተሰጣቸው ሲሆን ተማሪዎችን ሰብስበው የኔት ወርክ ችግር እስከ ሰኔ 30 ድረስ እንደሚፈታ ከዚያ በኋላ ምንም ዓይነት ችግር እንደማይኖር ሌሎቹ ችግሮች ግን እንደሚቀጥሉ ለወላጆቻቸው እንዲያስረዱ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸው ስብሰባው ተጠናቋል፡፡ በተያያዘ ዜና እሁድ በደማቅ ሁኔታ የተጠናቀቀው ሰላማዊ ሰልፍ ያስደነገጣቸው ደህንነቶችና ካድሬዎች በሰልፉ ላይ የተገኙ ነዋሪዎች ቤት በመሄድ በማስፈራራት ላይ እንደሚገኙ ለፍኖተ ነፃነት ገለጹ፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials