አሳዛኝ ዜና
አንድነት አመራር የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሰልፉን እንዳይሳተፉ አገደ
‹‹የአንድነት አባላት በደስታ ተቀብለውን ነበር›› የሰማያዊ ፓርቲ አባላት
የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ትናንት ባደረጉት ስብሰባ ሰላማዊ ሰልፉን ውጤታማ እንዲሆን ተቀላቅለው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን በዛሬው ዕለት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሜጋ ፎኖችን፣ ፊሽካዎችንና ጥሩምባዎችን ይዘው የተገኙ ቢሆንም በአንድነት ፓርቲ አመራሮች ሰልፉን እንዳይቀላቀሉ መታገዳቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አባላቱ ‹‹የአንድነት አባላት እኛ በመሄዳችን እያቀፉ ነው የተቀበሉን፡፡ በጣም ደስ ብሏቸው ነበር፡፡ ሆኖም አመራሮቹ እኛ በማናውቀው ምክንያት እንዳንሳተፍ አግደውናል፡፡ ዘለቀ ረዲ፣ ዳዊት ሰለሞንና ተክሌ በቀለን የመሳሰሉት አመራሮች ‹እንነጋገር› ብለው ከወሰዱን በኋላ ወይ ቲሸርታችሁን አውልቁ ካልሆነ ግን ‹ሰልፉን መሳተፍ አትችሉም ውጡልን›› ብለውናል›› በማለት ገልጸዋል፡፡
በተጨማም የአንድነት አመራሮች ‹‹እናንተ ሰልፍ ላይ ፖሊስ እናንተ ላይ የወሰደው እርምጃ እኛ ላይ እንዲደገም አንፈልግም፡፡ በእናንተ ምክንያት እኛ መታሰር አንፈልግም፡፡›› ብለው በኢትዮጵያውይነታቸውም ይሁን እንደ ፓርቲ መሳተፍ የነበረባቸውን ሰልፍ መሳተፍ አለመቻላቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ሰልፉን ለማድመቅ ሰብሰብ ብለው ወደ አንድነት ጽ/ቤት ሄደው የነበሩ 112 የሚሆኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ‹‹ከሰልፉ ውጡልን!›› በመባላቸው እየተመለሱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሌሎች በተናጠልም ሆነ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ሊቀላቀሉ የነበሩ አባላት መሳተፍ አለመሳተፋቸው አልታወቀም፡፡
Abel Efrem
No comments:
Post a Comment