ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!! ከጥላዬ ታረቀኝ አለማየሁ
ለመረጃ ያህል አሁን እየተሰሙ ያሉ ነገሮች በጣም አስፈሪና አሳዛኝ ናቸው:: ለመሆኑም ይህንን በዝምታ ማለፍ አይቻልም፤ በጥቂቱም ቢሆን እየተሳካለት የሚገኘውን ህዋህት/ኢህዴግ ከመነሻው ጀምሮ ለሀገር ማሰቡ የሚባል ነገር ወደ ጎን በመተው የስልጣን ማርዘሚያ ዘዴዎችን በመቀየስ ይህው 23 ዓመት ሀገሪቱን በጎሳ፤ በጎጥ፤ በብሔር፤ በሀይማኖት ሲከፋፍል ከርሞአል። በመጀመሪያ እሱ በቀደደው ቁምጣ የቡሄር ብሔረሰቦች መብት፤ በማለት ሰራ ግን ከጭፈራ ያልዘለለ መብት ሰጠሁ ብሎ የተወሰኑ በጥቅም በሞቱ አንድ ብሔር እንወክላለን የሚሉ ግን ደግሞ ስራቸው የማይታወቅም ኢትዮጵያን ለመበታተን የተነሱ አካላት ጋር በመደገፍ የህዋህት አሽከር ሆነው ስንመለከት ወይ ሰው ብለን ብዙ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል፤ ለምሳሌ በ1997 ምርጫ ውጤት ከታወቀ በኋላ የትግራይን ህዝብ ለመለየት መሠረቱ እስካሁን የማይታወቅ ህዝብ ከህዝቡ የሚያጋጭ ንግግር ሰምተናል ”እቃ ወደ ቀበሌ ትግሬ ወደ መቀሌ” የሚል በመቀጠል ወጣቶችን በማደራጀት አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ በማለት ማህበር አቋቁሞ፤ እዚህ ላይ እና መሰል የተዘሩ የተንኮል ዘሮች ቀናቸውን ጠብቀው አቆጥቁጦ ከማቆጥቆጥም አልፈው ለምልመው ይህው ሀገሪቱ ባለ ብዙ ባንዲራ ባለ ብዙ ሀገር ሆነች። ሁሉም የራሱን ጥግ በመያዝ አንዱ አንዱን ሲጠበቅ ገዥው መደብ ሀገር ሲበዘበዝ ደስ ካለው ከህግ አግባቢ ውጭ ሲገድል ሲያስር ተመልክተናል፤ የፀረ ሽብር ህግ ብሎ አውጥቶ ንፁሃንን በእስር ቤት የሚታገሉ አካላትን እራሱ ሲያሸብር ተመልክተን፤ በፈለገው መጠን ባይባልም በጣም ብዙ ግን የብሔርተኝቶ አስተሳሰብ ያላቸው አፈራ፤ እነሱንም በየኃላፊነት ቦታ ላይ በማስቀመጥ የልቡን አደረሷል፤ በተመቸው ሁሉ ህዝቡ ወደ አንድነት እንዳይመጣ ታግሏ። ለምሳሌ በሀይማኖት ለማጋደል ጀሀዳዊ አረካት ብሎ ተጋድሎ ዓይነት መልከት አዘል ዶክመንተሪ ፊልም አስኮመኮመን ብዙም አየው እኔ ግን በጣም የገረመኝ በዘንድሮ የጥቅምት በአል ጥር 11 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ የታየው ዶክመንተሪ ፊልም ሰው በማግስቱ ይገኛል ብዬ አልጠበኩም ነበር፤ ግን ህዝቡ የተዋለደ እና በወንድማማችነት የተቆራኘ በመሆኑ ኢቲቪን ታዝቦ ዝም አለ፤ አልተሳካም በቅርቡ ደግሞ ባህር ዳር እስታዲየም ላይ በተነሳው የሁለት ወንድማማቾች ግጭት ከማን የመጣ እቅዱ ነው? ይህን አውግዘን ሳንጨርስ በገዛ ሀገራቸው አማራዎችን ይውጡልን የሚሉ አካላት ተገኙ ግን ጥያቄው ይህ የኦሮሚያ ወንድሞቻችን ጥያቄ ነው? ሌላው ብዙ ነው ጎራ ፈርዳ ቤንሻንጉል ላይ የተደረጉት ድርጊቶች ስንመለከት ሀገሪቱ ምን እንሆነች ነው ብለን ቆዝመናል ጭራሽ ይባስ ብሎ ወንድማቶችን የሚጨርስ የሚያጋድል መሠት የሌለው ታሪክ በዚህ ዘመን የማይታሰቢ ኢትዮጵያ ሊበታትን የሚችል ማስታወሻ ይህን መነሻ ስራ ይሁን ሴራ በማይታወቅ መልኩ የአንድ ብሔር ንጉስ ጡት ቆርጠዋል ብለው ሀውልት ገነባ፤ በአኖሌ ሀውልት ችግሩ መገንባቱ አይደለም የሚዘው ያዘለው መልዕክ ምንድነው? የሚለውን ማጤን ያስፈልጋል የሚያስቡ መንግስት ነኝ የሚል አካል ይህን እኩይ ተግባር ሲፈጽም ለሀገሩ ነው ለስልጣኑ ነው የቆመው ብለን ማጤን ይጠብቀናል ብቻ መርጋቱ ዋጋ አለው ባይ ነን። ሰሞንኑ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል ማስተር ኘላን ይጠቃለል፤ አይጠቀላል የሚለው ውዝግብ በጣም በርካታ የኦሮሚያ ተወላጅ የሆኑ ወንድሞቼ ተምረን ያልፍልናል ብለው ዮኒቨርስቲ ገበታው ሳለ ቤተሰቡ በጉጉት ነገ ልጄ ትልቅ ደረጃ ይደርሳል፤ እያለ በጉጉት በሚጠበቅበት ወቅት ህጉ በማይፈቅደው መልኩ ከህግ ውጭ የመመረቂያ ወረቀት በመስጠት ፈንታ በጥይት ግንባር ግንገሩን በማለት ለቤተሰቡ ሬሳ የላከው መንግስታችን የዛችት 1997ቱ ሳይቀንስ አንድ ነገር አሻሽሎ ብቅ አ። የተከበሩ አቶ አባዱላ ገመዳ ትንሽ ተሳስተናል ግን ባንክ ሲዝረፍ ነው የተገደሉት አሉን ሰው ሲስተም አንኳን አይቀይርም ተቀበሉና አቶ ኩማ ደመቅሳ ከበስተጀርባቸው የሆነ ሀይል አለ አሉ እረ የጉድ ሀገር ስለዚህ በዚህ ብጥብጥ መሀል የብሔር ግጭት እንዲኖር ካድሬዎች እየሰሩ ነው ብሎ ኢሳት ቲቪ ነገሩ ወደሌላ አቅጣጫ እንዳያመራ ጥንቃቄ ይደረግ ሲል እያስጠነቀቀ፤ ይህንን ግን ችላ በማለት የአማራ ተወላጅ ነህ እየተባለ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የስንቱ ቤት ሲደበደቡ የዕሪታ ድምፅ ሰማን። አሁን ልብ ብለን ማጤን ያለብን ነገር እንዴት የሁለቱ ብሔሮች ግጭት ተከሰተ? በዚህ ውስጥ እነማን ተሳተፉ? የሚለውን አንጥረን ማውጣት ካልቻልን እና በዚህ ከቀጠለ በመላው ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተዋለደ አማራ በመላው አማራ የተዋለዱ ኦሮሞ በምን መነጠል ይቻላል? ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ ብሔራቸው ኦሮሞ ግን ደግሞ ጀግና ኢትዮጵያዊ ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር በብሔር አለማመናቸው ባለቤታቸው አማራ ተወላጅ ነበረች፤ እሳቸው ሁለቱን ብሔር እንዴት አድርጎ መለየት ይቻላል? ብለው ታግለዋል። ትግላቸውም አሸናፊ ሆኖ ሁለቱን ብሔር ማስማማት ችለዋል። እኔም በአካል ሄጄ ስለአንድነታቸው ያላቸውን ስሰማ ያ ትውልዱ ያስብላል በአሁን ሰዓት ያለውን የተመለከቱ በመሆኑም እንድ አዋቂ በቀልድም ሆነ በምር መልክ እንዳዋቂ መልዕክት ያስተላልፉ ወገኖች አለጥፉም። ለምሳሌ ታማኝ በየነ ክልል ስንወጣ በምንም መልኩ ፓስፖርት እንዳንጠየቅ ያለበት አጋጣሚ አይረሳኝም፤ በጣም ሊታሰብበት ወያኔ የአህአዲግ በሚመቸው መልኩ ማስተር ኘላን ብሎ ያወጣው እቅዱ ሳይሳካለት ሲቀር የሁለት ብሔር ግጭት ለማስመሰል ከፍተኛ እንቅስቃሴ አያደርግም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። የኛ ጥያቄ የብሔር አይደለም የኢትዮጵያዊነት ነው ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት የኢህደግ ሴራ በሚመቸው መልኩ ጉዳዩን እያስኬዱ ያሉ የህዋህት ታማኝ ካድሬ መሆናቸውን ብዙ ማረጋገጫ አለ በመሆኑም የመብት ጥያቄን ወደብሔር በመቀየር በማተራመስ ላይ በመሆኑ ልክ እንደ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ጀግና የሚያስፈልግበት ወቅት ነው ስለዚህ በጣም ይታሰብበት
No comments:
Post a Comment