Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, May 8, 2014

ኢህአዴግ /ጅቡ ከሚበላን በልተነው እንቀደስ

                                      ኢህአዴግ /ጅቡ ከሚበላን  በልተነው እንቀደስ
አስገራሚ ሁኔታዎችን በየቀኑ  የምንጋረጥበት የሀገራችንን የትራንስፖርት ገጠመኜን ላካፍላችሁ ና ወደ ጭብጡ እገባለው።
ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳሪስ በሚኒባስ እየሄድን ነበረ። ወደ ቄራ መስመር ቁልቁል አምርተን ጎፋ ካምፕ መገንጠያ ስንደርስ አንድ ሰካራም ሰው ጫንን። ከመግባቱ  ነው ረብሻ የጀመረው። የተቀመጠበት ቅርቡ ወንበር ላይ የነበሩትን ወይዘሮ  “የቤተመንግስት ወንበር መሰለሽ እንዴ ጠጋ የማትይው ወዲ ሸርሙጣ” ሲላቸው ክው አልን። “ከዚህ በላይ የት ልኪድ ልትጨፍርበት ነው እንዴ?” አሉት ሴትዮዋ። “ብጨፍርም የሚያምርብኝ ተምቤናዊ ነኝ”  አለና በሰካራም ኩራት መለሰላቸው በትክሻው እየገፋቸው። እኔም  ነኝ ለማለት ይመስላል ሴትዮዋ እሞ ግደፍ ሰውዬ ክብርህን ጠብቅ  ብለውት በእጃቸው ሲገፉት ያሳዩን በሁሉም ጣቶቻቸው ያጠለቁት ወርቅ ና የትግሬ ሹርባቸው ላይ ዙሪያውን ያንጠለጠሉት ወርቅን ያየ ባለ ጊዜ መሆናቸውን መረዳት አይከብድም የግንባራቸው ብጣት ንግግራቸውም ያሳብቃል ።
ከህወሃት የቀሰሙት ሂሳቸውን የመዋጥ ልምድ ይሁን ወይ ስልታዊ ማፈግፈግ  በሚመስል አካሄድ “ጥል በኛ መሃል አያሰፈልግም ብዬ ነው እንጂ ሌላ ቢሆን አሳስርህ ነበር” ብለውት ሴትዮዋ ከታክሲው ተመናቅረው ወረዱ።  ሰውየው አላቆመም  “በኛ መሃል አያስፈልግም ስትይ  ወጣቶች ይጣሉ እንጂ በኛ በአዛወንቶች መሃል ጥል አያሰፈልግም ማለትሸ  ነው ወይስ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ይጣሉ እንጂ እኛ ትግሬዎች መጣላት የለብንም ማለት ፈልገሽ?”  ሲል የበፊቱ ስድብ ላይ ፈሪ የሚል ቃል አክሎበት በሌለችበት  ከመጠየቁ አንድ ተሳፋሪ አሁንም ቢሆን የሰውን ማንነት ሰለማታውቅ ዝም ብትል ይሻልሃል ፖሊስ ልትጠራብህ ይሆናል የወረደችው ብሎ ንግግሩን እንዲያርም ገሰጸው ። ይባሱኑ እየሳቀ  የተንቤን ትግሬ እንደሆነ ከስራው እንደተቀነሰ ወያኔን እንደማይወድ ይወሸክትልን ገባ።  እየተጠቀሙ ያሉት የ አድዋ ትግሬዎች ብቻ መሆናቸውን አብራራልን ።
ተሳፋሪዎች ማጉተምተም ጀመሩ የታከሲው መጨረሻ ወንበር ላይ የተቀመጥነው አራት ጓደኛሞችም ተጠያየቅን
“ሰካራሙ የተማመነውን ተማምኖ ነው ባክህ  ያው ነው “
“ያውማ አይደለም በስመ ትግሬ ሁሉም አልፎለታል ማለት አይደለም”
“ለመጣላትም የሚያምርበትና የማያምርበት አለ ብላ ከፋፈለችን እኮ ይቺ ትግሬ” ቀጠለ ሌላው
“ተናግሮ አናጋሪ ነው ባካችሁ  ወሬ ቀይሩ” አለ አንዱ ከፊት
“ጆሮ ጠቢ አይደለሁም የፈለጋችሁትን አውሩ”  ሰካራሙ የጋፈው አምቡላ እየተናነቀው ሲል እንደተፈራው ካፉ አምልጦት ከፊቱ ያለው ሰው ላይ  ቮሚቱን ለቀቀው
ባክህ አስወጣው ሰላማችንን አይንሳው የሚለው ተሳፋሪ ድምጽ ቢበረታም ጎተራ ማሳለጫ ላይ  ስለደረስን መኪና ማቆም እንደሚያሰቀጣው ነግሮን ሹፌሩ ነጻነታችንን በሰካራሙ ሽታ አፈኖን ከነፈ ።
“ከሴትዮዋ ጋር ነበር መወረድ የነበረበት እዛው  አልኩት” ከጎኔ ላለው ጓደኛዬ
ጎተራን ተሻግሮ እንደቆመ ሰካራሙ ተምቤናይ ይቅርታ ጠይቆን ከወረደ በሃላ ፍሳሹን  ጠርገን ቀሪዉን መጓዝ ጀመርን አልፎ አልፎ ውል እያለ ቢያስቸግረንም። ሰካራሙ ክፉኛ የተፋበት ሰው ዘግይቶ በሌላ መኪና ሊሄድ ተገዷል።  እኛም ቢሆን አንፃራዊ ሰላም አገኘን አንጂ ሴትዮዋ ነዝታ የወረደችው  ወዳጇ  ሆድ ሊያስብሰን ሌሎች ኢትዮጵያውያን ይጣሉ እንጂ እኛ ትግሬዎች መጣላት የለብንም ሲል ያብራራልን  የመከፋፈል አደጋ ሲያወዛግበን ነበር ።  ሲቀጥልም በኛ መሃል አያሰፈልግም ብዬ ነው እንጂ ሌላ ቢሆን አሳስርህ ነበር ያለችውን በማስታወስ ሰካራሙ ከ ትግሬ ሌላ ቢሆን ኖሮ እዛው ማንኛዋም ልታስረው እንደምትችል ስለነገረችን ሌላ ጊዜ ለመዘናናትም ለመሳፈጥም ከማን ጋር ብለን ተረበሽን ። በመጨረሻም ሰክሮ የልብን ለመናገርም የሚፈቀደው  ለነሱ ብቻ ነው እንዴ? ሲል ጀለሶቼ ብሎ ያቀረበን የታከሲው ረዳት ጠየቀንና አስደመመን።
እንግዲህ በኢትዮጵያም የሆነው  ጉዳይ ይህ ነው ። ከሶሻሊዝም አደባባይ በደርግ  አብዮታዊ ሹፌርነት ወደለየለት ኮሚኒዝም እያመራን ነበረ ። በጊዜ ታክሲነት ያሳፈርናት  ህወሃት ኢህአዴግ በተፋብችብን መርዘኛ የዘረኝነት የመከፋፈል አደጋ በየጊዜው እየተረበሽን እንገኛለን ። ከሰካራም ቃል አቀባዩዋ  ከአፉ በሚወጣው የክፋት የመከፋፈል የዘረኝነት አምቡላ አንገሽግሿቸው ገሚሶቹ ወደሌላ ሀገር ለመሰደድ ተገደዋል ገሚሶቻችንም በየጊዜው  በሃገር እየተነታረክን እየተጠራጠርን እንገኛለን ።
ፋሺሰቶቹ ናዚ ወያኔዎች በጎሳ ብሄረተኝነት ሰክረወ ዕብደታቸወን ልክ እንደ ሂተለር ዘመን በግልጽ ለኢትዮጵያና ለ አለም ህዘብ እያሳዩ  ናቸው።በአረመኔነቱ የሚታወቀው ሂትለር ከዓለም ህዝቦቸ ሰማያዊ አይን ያላቸው ጀርመኖቸ ብቻ ምርጥ እንደሆኑ  በእብሪት እንደተናገረው ሁሉ  የህወሃት መሪ የዘመናችን ሂትለር መለሰ ዜናዊ  ከነሱ በላይ የሰው ዘር እንደሌለ ከጨርቅ ሳይሆን ከወርቅ አንደተፈጠሩ  ሌሎቻችንን በማሳነስ ትምክህተኛነቱን በእብሪት ያቅራራብንን አንረሳውም። ዛሬም ተተኪዎቹ በየቦታው የሚነግሩን ይህን ነው ። በትግሪኛ ፕሮገራሞቻቸውና በየቀኑ በሚለቋቸው የጀብደኝነት ዘፈኖቻቸው ና ቀረርቶቻቸው እንደ ጥጃ እየዘለሉ ያሳዩን  ትግሬነት ከየትኛውም ዘር በላይ እንደሆነ ጎሳቸውን ያለቅጥ አግዝፈው በማምለክ collective Narcissim የሌላውን ሰብዓዊነት ክደው እንደፈለጉ ይፈነጫሉ ።
በጀሌነት የሚያጅቧቸውን አጋር ድርጀቶች ብአዴን ደኢህዴን ኦህዴድ ወዘተ ተለጣፊነት በሚያጎላ መልኩ  በኢሀአዴግ ልሳን ጽሁፋቸው ሳይቀር “በመሪ ድርጀታችን ህወሃት” የሚል ቃላትን ይጠቀማሉ።
የሃገሪቱን ኢኮኖሚም የተቆጣጠሩት የሂትለሩ መለስ ድርጅቶች ናቸው። ኢፈርት በሚባለው ማህበራቸው በግብርና በጤና በባንክ በትራንሰፖርት በ ኢምፖርት ኤክስፖርት በማናቸውም ዘርፎች ማለት ይቀላል ሀብት የሚያግበሰብሱት እነሱ ብቻ ናቸው። ስራ ፌላጊ ወጣት እንደአሸን በፈላበት ኢተዮጵያ ዝቅተኛ ሰራዎች ሳይቀር እየተለዩ የሚሰጡት ለነሱ ከፍተኛ የትምህርት ዕድሎች የሚሰጡትም ለነሱ ለናዚ ወገኖች ብቻ ነው።
የኛ እናቶች ወረፋ ጠብቀው በባስ ሲሄዱ የነሱ ወይዘሮዎች በታክሲ እየተቀናጡ ይሄዳሉ።ያሻቸውን ተናግረውን ያስፈራሩናል ዝም ባልንበት እየገቡ ሰላማችንን ይነሱናል የሚገዙበትን ህገ አራዊት እንዳንቃወም ና በኢኮኖሚ እንዳንደርስባቸው በጎሰኝነት የስካር ማዕበል ወስጥ አየዋኙ ጎሰኝነትን ረጭተውብን ያባሉናል። የህወሃት ግብ  የውሸት የጥላቻ ታሪኮችን እያመረቱ  ትወልድን ለጥላቻ በማነሳሳት እኛን ማደህየትና እርስ በእርስ በዘር እንድንጣላ በማድረግ ሀገሪቱን ምድረ በዳ ማድረግ ነው።
ከአብራኩ የፈለቁ አንዳንድ የትግራይ ልጆች ሳይቀሩ ህወሃትን ሊመክሩት ሊቃወሙት ሲሞክሩ አደጋ ይደርስባቸዋል። ለጊዜውም ቢሆን አስረው ይለቋቸዋል። ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ተባብረው መኖር እንደሚፈልጉ ቢገልፁለትም ህወሃት የተመሰረተበትን  ህዝበ ወያነ ሓርነት ትግራይነት ማለትም ትግራይን አልምቶ የመገንጠል ራእይ ሳያሳካ እንደማይመለስ ይነግራቸዋል። ቆይቶ ትግራይን  መገንጠሉ ሓርነት ማውጣቱ የማይጎዳ ቢሆንም  ክፋቱ እየዘራብን ያለው የዘረኝነት እንክርዳድ ዋናዋን ኢትዮጵያ የሚያፈራርስ ታይም ቦምብ መሆኑ ነው።
በጉዞአችን ላይ ይበጠብጠን የነበረውን ሰካራም አስወርደን በሰላም ወደፈለግንበት መደረሳችንን ከታክሲው ጉዞ ገጠመኝ ተምረናል። ተፍቶብን የሄደው የዘረኝነት አምቡላ ግን አልፎ አልፎ ይሰነፍጠን ነበር።ከታክሲው ወርደንም ግን በእርግጥ በስመ ትግሬ ሁሉም አልፎለታል ማለት እንደማይቻል ከጓደኞቼ ጋር ተወያይተንበታል። የመለስ ዜናዊ ወንድም አንዱ ደሃ በቆሎ ሻጭ መሆኑን ስናውቅ ለፖለቲካ ነው ብለን አማን አንዱ የመከላከያ መኮንን አንዱ በእንግሊዝ ለንደን እየናጠጠ እንደሚኖር  ሌሎቹም በየፊናው ተሰግስገው ደሃም ሃብታምም ሆነው ከህዝባችን ጋር “ስራቸውን” እየሰሩ እንደሚኖሩ ተነጋገርን። ግን ምን አገባን ሲቀልጥም ሴትዮዋ ወያኔ ለምን ወገኗ እየሰደባት በተሳፋሪው ፊት ገመናዋን ሸፍና ከወንድሟ ጋር መጣላት ያልፈለገችበትን ምክንያት አነሳን። ትግሬ ገመናውን ይሸፋፈናል የኔ ዘር ቢሆን ግን እያልን ራሳችንን አዋረድን ከምር ወርቅ ዘር ያሉንን ተቀብለናል ማለት ነው አልኩ ለብቻዬ።
ሲጀመር ስለምን ከታክሲም ከወረድን በላ ማማት አስፈለገ?? እነሱ እየተመነደጉ እኛ  በቤትም በመንገድም ስለነሱ ለወሬ ሱስ እንደዳረጉን ይበልጡንም ስለ ዘራችን እያወራን ታይም ቦምባቸው እንዲፈነዳ እያገዝናቸው መሆኑን የምናስተውለው መቼ ነው??
ከመጀመሪያው ሰካራሙን በታክሲ/ሀገራችን ባንጭነውስ? መረበሹን ካወቅንም ከነካካት ቀዳማይ ወያኔ ሴት ጋር ብናስወርደው ኖሮ ከለየለት የዘረኝነት ትወከቱ እንተርፍ ነበር።
ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተሸረበው ስይሰምር ዘረኝነቱ ስር ሳይሰድ ህወሃት መጦሪያውን አመቻችቶ ከመገንጠሉ በፊት  የሚበጀንን እንምረጥ ።

 ወያኔ ኢህአዴግ ጅቡ ከሚበላን በልተነው እንቀደስ ።ለዚህም ሳይቃጠል በቅጠል ነውና እኛው ዘረኝነቱን ከማራገብ ካሁኑ እንቆጠብ። አብራሃም ዘ ታየ 

No comments:

Post a Comment

wanted officials