Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, September 27, 2014

ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያ በምርጫ2007 ለአፍሪካ አርአያ እንድት ሆን አሳሰቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ከፕሬዚዳንት አባማ ጋር በኒዮርክ ተወያዩ
ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት 69ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በኒዮርክ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ማምሻውን ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ተወያይተዋል።
ሪዎቹ ወደ ውይይት ከመግባታቸውም በፊት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ ወደፊት እየተሻገረች መሆኗን በማንሳት በዚህ ሽግግር ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።
ራስን ለማልማት የሰው ሀይል አቅምን ማሳደግ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም በዚህም ሂደት ዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ ፕሮግራሞች ድጋፏን በማድረግ ጤነኛ አምራች ሀይል እንድናፈራ አግዛናለች ነው ያሉት።
በፓወር አፍሪካ ፕሮግራም በኩል ኢትዮጵያ በሀይል ለማት ዘርፍ የግል ዘርፍን እንድታሳትፍ አሜሪካ ላደረገችው ድጋፍም አቶ ሀይለማርያም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በአፍሪካ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፈን እያደረገች ያለችውን ጥረት አንስተው፥ ይህ ስራዋን ከአፍሪካ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ብሎ ለዓለም ሰላም የምታደርገውን ድጋፍ ማሳደግ ትፈልጋለች ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በበኩላቸው በቅርቡ በአፍሪካ አሜሪካ ጉባኤ ላይ በአህጉሪቱ እየታየ ያለውን ብሩህ ነገር እና ለውጥ ለማሳየት ከኢትዮጵያ የተሻለ ምሳሌ የለም ሲሉ ንግግራቸውን ጀምረዋል፤ ኢትዮጵያ በዓለም በፍጥነት እያደጉ ካሉ የዓለም አገራት መካከል አንዷ መሆኗን በማንሳት።
በአንድ ወቅት ራሷን መመገብ አቅቷት የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ ራሷን በምግብ እህል ከመቻል አልፋ እያከናወነች ባለቻቸው የልማት ስራዎች በኩል በአከባቢው ሀይልን ወደ ውጭ ወደ መላክ ደረጃ ተሸጋግራለች ነው ያሉት።
ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ሰሞኑን የገባውን ስምምነት በመጥቀስ ስምምንቱ በአሜሪካ ተጨማሪ የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በዓለም ሰላም ማስጠበቅ ተልእኮዎች ከፍተኛውን ሚና እየተጫወተች ያለች አገር ሆናለች፤ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ተሰማርቶ ውጤታማ መሆን የሚችል ምርጥ ተዋጊ ሀይልም ገንብታለች ሲሉም ነው ያደነቁት።
እናም በአፍሪካ የኢትዮጵያ መሪነት በኢኮኖሚው ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በሰላምና ፀጥታ ዘርፍ መሆኑን በማንሳት የአገሪቱ ጦር ለረዥም ዓመታት ሳይፈቱ የቆዩ ግጭቶችን በማስቆም እየተሳተፈ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህም ሚናዋ ከኢትዮጵያ ጋር መስራት በሚቻልባቸው ለምሳሌም የደቡብ ሱዳን ግጭትን በመፍታቱ ረገድ አብረን እንድንሰራና ይህን አጋርነት ለማሳደግም እንድንፈልግ አደርጎናል ነው ያሉት።
አሁን ዓለም እስላማዊ መንግስት ስለሚባሉት አይ ኤስ አይ ኤል የሚያወራ ቢሆንም በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰውና ከአልቃይዳ ጋር ግኑኝነት ያለው አልሸባብ አይዘነጋም ያሉት ፕሬዘዲዳንት ባራክ ኦባማ፥ አልሸባብን በማዳከቡ ኢትዮጵያ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል።
አሜሪካ ኢትዮጵያን ከመሰሉ አገራት ጋር የመሰረተችው የፀረ ሽብር ግምባር አሁን ወሳኝ ጊዜ ላይ እንደደረሰም ነው የገለፁት።
ፕሬዚዳንት ኦባማ በመጨረሻም ዘንድሮ ኢትዮጵያ ምርጫ እንደምታካሂድ በማንሳት በዚህም አገሪቱ በአፍሪካ አርአያ እንደትሆን የሚነጋገሩበት እድል እንዳለ አስታውቀዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials