Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, September 25, 2014

ቻይና ለአፍሪካ አገራት የማሰቃያ መሳሪያዎችን እንደምትሸጥ አምነስቲ ገለጸ

ቻይና ለአፍሪካ አገራት የማሰቃያ መሳሪያዎችን እንደምትሸጥ አምነስቲ ገለጸ


አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ 130 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች ለአፍሪካ መሪዎች በእስር ቤት ጥቅም ላይ የሚሆኑ የማሰቃያ መሳሪያዎችን ይሸጣሉ።
የኤልክትሪክ ንዝረት ያላቸው   ከብረት የተሰሩ ሹል ዱላዎችና ሌሎችም  የማሰቃያ መሳሪያዎች ለአፍሪካ እና ለእስያ አገራት መሸጣቸው በአህጉራቱ ውስጥ የሚታየውን ሰብአዊ መብት እረገጣ አባብሶታል። በአለም ላይ ስለት ያላቸውን የንዝረት
ብረቶችን የምታመርተው ቻይና ብቻ መሆኗን የጠቀሰው አምነስቲ፣ ፖሊሶች በእስረኞች የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ላይ በማሳረፍ ስቃይ እኢነደሚፈጽሙ አጋልጧል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቻይና የማሰቃያ መሳሪያዎችን የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ወደ ሚፈጽሙ አገራት እንዳትልክ ግፊት እንዲደረግ ጠይቋል

No comments:

Post a Comment

wanted officials