Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, September 20, 2014

በኩላሊት ህመም የሚሰቃየው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በቂ ህክምና ሳያገኝ ወደ ዝዋይ እንዲመለስ ተወሰነ

ዘጋቢ ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከአዲስ አበባ
webshet taye
በዝዋይ ወህኒ ቤት ቆይታው ለከፍተኛ የኩላሊት ህመም በመዳረጉ የተሻለ ህክምና ያገኝ ዘንድ በማረሚያ ቤቱ ክሊኒክ ሪፈር የተጻፈለት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ አዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቢዘዋወርም የናፈቀውን የተሻለ ህክምና ሳያገኝ ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዲመለስ መወሰኑን ለጉዳዮ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ውብሸት ከቤተሰቦቹ ራቅ ባለ የዝዋይ ማረሚያ ቤት የእስር ጊዜውን እንዲገፋ በመደረጉ በየጊዜው መጎብኘት የተሳናቸው ቤተሰቦቹ በቅርበት ሊጎበኙት ወደሚችሉበት ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወር ሲጠይቁ መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ምክትል አዘጋጅ ወደ ቃሊቲ እንዲዘዋወር ከተደረገ በኋላም ጤንነቱ ምንም አይነት መሻሻል ባለማሳየቱ ህክምና የማግኘት መብቱ እንዲከበርለት የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡
ጋዜጠኛው ህክምና ለማግኘት በሚጠባበቅበት ሰዓት ወደ ዝዋይ እንዲመለስ መወሰኑ በቤተሰቦቹ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘ አበበ ቀስቶና አቶ በቀለ ገርባ በተመሳሳይ መልኩ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ህክምና ማግኘት ወደሚችሉበት ቃሊቲ እንዲዘዋወሩ ቢደረግም ህክምና የማግኘት መብታቸውን የቃሊቲ አመራሮች ባለማክበራቸው ከእነህመማቸው እንደሚገኙ ምንጮቼ ጠቁመዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials