ስኖውደን ተሸለመ
ስኖደን የተሸለመዉ በዓለም የማትደፈረዉን ሐያል ሐገር በማጋለጥ ለመናገር ነፃነት መከበር መቆሙን በማረጋገጡ ነዉ።ለወትሮዉ የተሸላሚዎች ሥም ዝርዝር በይፋ የሚነገርበት የሲዊድን ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ግን መስሪያ ቤት ግን የዘንድሮ ተሸላሚዎች ስም ዝርዝር ከቢሮዉ እንዳይነገር አግዷል
የዩናይትድ ስቴትስን መንግሥትን የሥለላ ሴራ በማጋለጡ ከሐገሩ ለመሰደድ የተገደደዉ የቀድሞዉ አሜሪካዊ የሥለላ ድርጅት ባልደረባ ኤድዋርድ ስኖደን «አማራጭ ኖቤል» የተሰኘዉን ሽልማት አገኘ።መንበሩን ስቶክሆልም-ስዊድን ያደረገዉ ሸላሚ ድርጅት RightsLivelihood እንዳስታወቀዉ ስኖደን የተሸለመዉ በዓለም የማትደፈረዉን ሐያል ሐገር በማጋለጥ ለመናገር ነፃነት መከበር መቆሙን በማረጋገጡ ነዉ።ለወትሮዉ የተሸላሚዎች ሥም ዝርዝር በይፋ የሚነገርበት የሲዊድን ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ግን መስሪያ ቤት ግን የዘንድሮ ተሸላሚዎች ስም ዝርዝር ከቢሮዉ እንዳይነገር አግዷል።
No comments:
Post a Comment