የጦር ሰራዊቱ በውስጥ ተቃውሞ እየተናጠ ነው። የበአል እረፍት የጠየቁ 26 መኮንኖች ታስረዋል።
- ሰራዊቱ በወያኔ መንግስት ላይ ተስፋ በመቁረጡ ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ እየሾለከ ነው፡፡
- በርካታ ወታደሮች ከነትጥቃቸው ከካምፕ ጠፍተው የት እንደገቡ አይታወቅም።
- የወያኔ ጄኔራሎች ዘረፋ እንደቀጠለ ነው ። ወታደሮች በድህነት አለንጋ እየተገረፉ ነው።
በአንድ ብሄር የበላይነት የሚመራው የወያኔ የጦር ሰራዊት የሰሜን እዝ ለአዲስ አመት ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሄድ ፍቃድ የጠየቁ እና በመብት ጥያቄዎች ጥርስ ተነክሶባቸው ሪኮርድ አለባቹህ የተባሉ ወታደራዊ መኮንኖችን ፈቃድ በመከልከሉ በተነሳ አለመግባባት ክነሃሴ ወር ማብቂያ ጀምሮ 26 መኮንኖች በእዙ የጨለማ ክፍል ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ተናግረዋል።ከከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ጀምሮ እስከ ተራ ወታደሮች ድረስ እየከዱ ነው ያሉት ምንጮች ሰራዊቱ ባለው የወያኔ መንግስት ላይ ተስፋ ቆርጧል።
በሰራዊቱ መሃል ውስጥ ውስጡን ያለው ክፍፍል እና አለመግባባት ከተለያዩ የጦር ክፍሎች በተሻለ በሰሜን እዝ ውስጥ የሚሰሩ መኮንኖች ያለውን አድሎዊ አሰራር እየተቃወሙ ጥያቄ በማንሳታቸው ከተቃዋሚ ሃይላት ጋር ግንኙነት ፈጥረው ነው ተብለው በተልይየ ጊዜ ሪፖርት የቀረበባቸው ሲሆን በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ወያኔው መጠላቱን አምነው ያልተቀበሉ ጄኔራሎች የትግራይ ተወላጅ ያልሆኑ መኮንኖችን የተቃዋሚዎችን ጥያቄ ታስተጋባላችሁ በሚል ሰበብ ከሰራዊቱ በማግለል እና በማሰር ላይ ናቸው ያሉት ምንጮች የቤተሰብ ጥየቃ የበአል እረፍት ተይቀው አለመግባባት የተፈጠረባቸው አሁንም የሚደረገውን አድልዎ በመቃወም ተበሳጭተው የመብት ጥያቄ ያነሱትን መኮንኖችን እያፈኑ ወደ እስር ቤት እየወረወሩ ይገኛሉ ብለዋል።
ቁጥርቸው 68 የሚሆን ወታደሮች በሽሬ አከባቢ ከሚገኘው ካምፕ ከነትጥቃቸው ለቅኝት ከወጡበት ወዴት እንድሄዱ እና የት እንደገቡ እንደማይታወቅ እና የድንበሩ አከባቢ ውትርትም ያየለ መሆኑን ምንጮቹ ሲገልጹ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሰሜን እዝ ያንድ ወገን የበላይነት ይወገድ...ተቃውሞ ብሄራዊ እንጂ ክልላዊ አይደለም....ለሃገር እንጂ ለግል የሚል አቁዋም ይወገድ ...የሚሉ እና ሌሎች የመብት ጥያቄዎችን መኮንኖቹ በማንሳታቸው የወያኔ ጄኔራሎች በመደናገጣቸው የመከላከያ ደህንነት ሃይሉን አጠናክረውታል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወታደሩ በድህነት አለንጋ እየተገረፈ ባለበት በዚህ ወቅት በመከላከያ ዉስጥ ባለው ዝርክርክ እና ብልሹ አሰራር የሃገር ንብረት እና የህዝብ ሃብት በጀኔራል መኮንኖቹ እየተዘረፈ ሲሆን ዘመዶቻቸውን እያመጡ በተለያየ መንገድ እያሸሹ መሆኑን ታውቋል:: በተለያዩ የመከላከያ ግቢዎች ዉስጥ የቆሙ የተበላሹ መኪኖች እየተሰበሰቡ ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች በኪሎ እየተሸጡ ሲሆን ገንዘቡንም ጀነራሎቹ በሚስቶቻቸው እና በልጆቻቸው ስም እንዲሁም በዲያስፖራ ዘመዶቻቸው ስም በውጭ አገራት ባንኮች እያስቀመጡት ሲሉ ምንጮች ተናግረዋል::
በተለያዩ መንገዶች ከመንግስት ካዝና ወጪ እየተደረገ በቢዝነሱ እንዲሳተፉ የሚደረጉት የጄኔራሎቹ ሚስቶች ሲሆኑ ደርግን ለመጣል የታገልነው እኛ ብቻ ነን በኢል መዘባበት የተለያዩ ንብረቶችን ከመስሪያቤቱ በዱቤ እያወጡ የማይከፍሉ ሲሆን ልጆቻቸው በዉጭው አለም በዉድ ዋጋ እየተማሩ መሆኑን የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ተናግረዋል:: የአድዋ ተወላጅ የሆኑ ጄኔራሎች በተለየ ሁኔታ በወርቅ ንግድ ዉስጥ የገቡ ሲሆን የተለያዩ የማእድን
አገር በቀል ድርጅቶችን እያባረሩ ራሳቸው ዘመዶቻቸዉን በማስቀመጥ ከጨረታ ውጪ ስራዉን እየሰሩት መሆኑን ጥቆማው ያስረዳል።
No comments:
Post a Comment