Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, September 25, 2014

የመስቀል አደባባዩን በዓል ፍት ህን እንዲጠየቅበት ጥሪ ተላለፈ

የፊታችን አርብ 16/1/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ታላቅ ሐይማኖታዊ ፕሮግራም(የደመራ በአል) ይካሄዳል፡፡ በዕለቱም የገነተ ፅጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ተረኛ የባህሉ አዘጋጅ ነው፡፡
በቦታው የአገር ውስጥ ፓትርያርክ የሆኑት እንዲሁም ብጽዕ ሊቀነ ጳጳሳት እና የአዲስ አበባ አገር ስብከት አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እና ሊቃውንተ ቤ/ክ የሚገኙ ሲሆን፤የመንግሰት ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ ቱሪስቶች እና በብዙ መቶ ሺህ የሚገመቱ የእምነቱ ተከታዮች፣የተለያዩ የውጪ አገር የመገናኛ ብዙሃን በመስቀል አደባባይ በበአሉ ላይ ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም በዕለቱ “እኔም ለእምነቴ” በሚል መሪ ቃል፡- 1ኛ. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ በሁን ወቅት የአገር ውስጥ እና የውጪ ተብሎ ስያሚ ተሰጥቶት የሚንቀሳቀሰው ሲኖዶስ፤ ለሁለት ከመከፈሉ ባላይ በቤተክርስቲያናችን ላይ የፈጠረው አሉታዊ ተፅእኖ በመቃውም እርቀ ሰላም እንዲካሄድ፡፡ 2ኛ. በገራችን ባሁን ወቅት ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት፣ የኑሮ ውድነት ፣በሽታ ፣ስደት የመሳሰሉት ችግሮች አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ፡፡
ስለሆነም ቤተ/ክ በይፋ የጾም እና የጸሎት ቀን እንድታውጅ ለመጠየቅ፡፡ ፀሎተ ወንጌል ከተፈፀመ በኋላ የአዲስ አበባ አድባራት ሰንበት ት/ቤ የዕለቱ ቲርቲ ማሳያት ሲጀምሩ “ሃይል የእግዚአብሔር ነው ፣ማዳን የእግዚአብሔር” የሚለውን መዝሙር በተደጋጋሚ በመዘመር ፣በጭብጫባ እንዲሁም ከፍተኛ ድምፅ በማሰማት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ የአንድነትን ተምሣሌታዊነት ለማሣየት እጅ ለእጅ በመያያዝ ደመራው እስኪለኮስ ድረስ ምእመናን ጥያቄዎቻችን በአደባባይ የምንጠይቅበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ መልዕክት በማንኛውም የመገናኛ ዘዴ በመጠቀም ለምእመናን እንዲዳረስ ጥረት እናድርግ፡፡
ኢትዮጵያ እጆቻን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ! አሜን

No comments:

Post a Comment

wanted officials