መልካም አስተዳደር እና ፍትህን ለማረጋገጥ ለትግሉ መስዋትነት መክፈል አለብን።
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የጥቂት ባለስልጣናትን አፈናና ግዴለሽነት የመዋጋትና ነፃ የመውጣት ግዴታ አለበት
ትግሉ ራሳችንን ከአምባገነኖች ነጻ የምናወጣበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ ስለሆነ ከትግሉ ይቀላቀሉ !!!!
ትግሉ ራሳችንን ከአምባገነኖች ነጻ የምናወጣበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ ስለሆነ ከትግሉ ይቀላቀሉ !!!!
ኢትዮጵያ ወያኔ የፖለቲካ ፕሮግራሙ ገልብጦ ባሰፈረው ህገመንግስት ላይ መልካም አስተዳደር እና ፍትህ በወረቀት ላይ ተከትበው ለባለስልጣናት የማጭበርበሪያ ተግባር እየዋሉ ነው:: ትክረት የማይሰጠው እና ተግባር ላይ ያልዋለው ህገመንግስት ዜጎችን መርገጫ እና የመዋሻ ጎተራ ከሆነ አመታቶች አመታትን ወልደው ባለህበት እርገጥ እየተባለ ነው:: በህገመንግስት እና ተከታይ ህጋዊ ድንጋጌዎች በሚል ስም ፍትህ እና መልካም አስተዳደር እየተሸጠ እየተለወጠ እየተረገጡ ዜጎች እፍረት እየተከናነቡ ዝምታን በመምረጥ ተስፋ ቆርጠው እንዲቀመጡ የሚደረገውን ሩጫ ለማክሸፍ እና ነጻነትን ለማረጋገጥ ትግሉ ወሳኝ ምእራፍ ላይ መሆኑን ልብ ማለት አለብን ::
መልካም አስተዳደር እና ፍትሕ በመጓደሉ የሕዝብ ልብ እየቆሰለ - ተስፋው እየተሟጠጠ -እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁምን እያሰኘ - ኢትዮጵያ ለእኔ ምኔ ናት እያስባለ ነው፡፡ህዝቦች ፍትሕና መልካም አስተዳደር አለ ብለው ስለማይተማመኑ ስለማይኮሩ እና ምንም የፍትህ እና የአስተዳደር እርካታ ስለማያገኙ በህጎች ላይ ምንም እምነት የላቸውም ፣ በህገመንግስት ላይ ሰፍረዋል የተባሉ ህጎችን ለመጠቀም አይደለም ወረቀቱንም ለመንካት በጣም ከባድ እና አደገኛ ሆኖባቸዋል::በግለሰቦች እና በአሸባሪው የወያኔ መንግስት ሰዎች ፍትሕ ላጣ ዜጋ፣ መልካም አስተዳደር አጥቶ ለሚንገላታ ዜጋ ፍትሕና መልካም አስተዳደር እንዲኖር በአንቀጽ ተደንግጓል እያልን ብናወራ ዋጋ አይኖረውም፡፡ በተግባር ሕዝቡ ሊያገኘው ይገባል፡፡ ሕዝብም እንደ ሕዝብ፣ ግለሰብም እንደ ዜጋ መንግሥት ካለ፣ ሕግ ካለ ማንም ንብረቴን አይቀማኝም፣ ማንም መብቴን አይነፍገኝም፣ ማንም አያጠቃኝም፣ አይገድለኝም፣ አይመታኝም፣ አያሳድደኝም ብሎ መተማመን አለበት፡፡ሆኖም ይህ ሁላ ነገር የለም ህዝቡ በስርአቱ ላይ እምነት ስላጣ ወደ ትግሉ በመቀላቀል ነጻነቱን ለምረጋገጥ ሊት ተቀን እየሰራ ነው ::
ኢትዮጵያውያን ፍትሕና መልካም አስተዳደር በማጣታቸው አገር በጠላት እና በድህነት ሲወረር ከመከላከል ይልቅ የላሸቀ ሞራላቸውን ይዘው እንዲሰደዱ እየተደረገ ነው ፡፡ መንግስት ከህዝብ ጋር እጅ ለእጅ መያያዝ ሲገባው ህዝብን እንደጠላት እያየ የህዝብን አንገት ሰባራ አድርጓል፡፡ ፡፡ ሕግን ከማክበር እና ግዴታውን ከመፈጸም ይልቅ መሪ እንዳለለው መንጋ ተበታትኖ እና ለወንጀል ተቧድኖ ከፍተኛ በደል በሃገር ላይ ይፈጽማል:: በሃገር ከመኩራት ይልቅ በየሰው አገር በመሰደድ ለብሄራዊ ውርደት ተዳርጓል::፡፡ጠንካራ አልሚ ፍትሐዊ ዜጎች በየሰዉ ሃገር አስታዋሽ አተው በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ ግሽበት ምች ተመተው እየተንከራተቱ ነው፡፡ የዚህ የወያኔ ጁንታ ሰለባ የሆናችሁ ሁሉወደ ትግሉ ጎራ እንድትቀላቀሉ እና ነጻነታችሁን እንድታረጋግጡ ለመናገር እፈልጋለሁ
በሃገሪቱ ሰፍነዋል የተባሉ ህጎች የህዝብን ፍትህ እና መልካም አስተዳደርን የማግኘት መብት የሚያረጋግጡ ሳይሆኑ የሚረጋግጡ ናቸው::በየቦታው እና በየጊዜው ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን ከሚደፈጥጡ ባለስልታናት በዲስኩር መልክ ብቻ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር እንደተረጋገጠ ይነገራል እንጂ ዝግጁነቱ ተግባራዊነቱ እና ቁርጠኝነቱ የለም:: ስለዚህ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የጥቂት ባለስልታናትን አፈና እና ግዴለሽነት የመዋጋት እና ራሱን ነጻ የማውጣት ግዴታ አለበት ::
መልካም አስተዳደር እና ፍትህ ጠይቀን የሚሰጠን መብት እና የባለስልጣናት ችሮታ ሳይሆን ራሳችን በትግላችን ልናረጋግጠው የሚገባ መብታችን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: በወያኔ እና በጭፍሮቹ ላይ የተባበረ ክንዳችንን በአንድነት አንስተን ለጋራ ጥቅሞቻችን በመታገል ድል መቀናጀት የራሳችን ግዴታ እና መብት መሆኑን ማወቅ ይገባናል
No comments:
Post a Comment