Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, September 10, 2014

የኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽማቸውን ወንጀሎች ለዓለም ማህበረሰብ የማጋለጥ ተግባር በጀርመን ሀገር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-
የኢትዮጵያ መንግስት በተከታታይ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጽማቸውን ወንጀሎች ለዓለም ማህበረሰብ የማጋለጥተግባር በተለያዩ ሃገሮች በተለይም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ህገወጥ እገታ ተከትሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል።ሰላማዊ ሰልፎች አሁንም በበርካታ ከተሞች እየተደረገ ሲሆን በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያውን ገዢስርዓት ህገወጥ ተግባራት የሚያስረዱ ጽሁፎችን አዘጋጅተው ለጀርመን ነዋሪዎች እያዳረሱ ሲሆን የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን እርዳታ ከሰብዓዊ መብት አኳያ እንዲያጤን የሚጠይቅ ፊርማም እያሰባሰቡ  ይገኛሉ

በጀርመንሀገር የሚገኙ በEPCOU ስር የተሰባሰቡ  ኢትዮጵያውያን የወያኔ አምባገነን ስርአት በንጹህ ዜጎቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ለጀርመን መንግስትና ህዝብ ለማሳወቅ በጀርመን በተለያዩ ከተሞች የሚያደርጉትን የፊርማ ማሰባሰብ በመቀጠል ቅዳሜ September 6 ቀን 2014 በፍራንክፈርት ከተማ ደማቅ የሆነ የፊርማ ማሰባሰብ ያደረጉ ሲሆን በተከታታይም በ13/09/2014 በ Aschaffenburg ከተማ ላይና በተጨማሪም በኑሩንበርግና በሬገንስቡርግ ከተማ በማድረግ Oktober 8/2014 በሙሉ የተሰባሰበውን ፊርማ በርሊን ከተማ ላይ በሚደረገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለሚመለከታቸው የጀርመን ባለስልጣን መስሪያቤት የሚቀርብ ሲሆን በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይም ከጀርመን የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ስለ በሀገራችን ውስጥ ስላለው የሰብዓዊ መብት እረገጣ የሚያስረዱ በአውሮፓና በሌሎች አሀጉር የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ተጠሪዎች ተጋብዘው የሚገኙ መሆናቸውን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን -------------
" ትግላችን የፈረነጅ አሽከር ሆኖ በስደት ለመኖር ሳይሆን በሀገራችን
ዲሞክሪያሲያዊና ህዝባዊ ስርዓት ተመስርቶ
ከብሄራዊ ውርደት ለመላቀቅ ነው!!"
የተባበረች ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
Epcou Germanyy

No comments:

Post a Comment

wanted officials