Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, September 18, 2014

የመምህራንና የተማሪዎች ስልጠና በልዩነት እንደቀጠለ ነው



የመምህራንና የተማሪዎች ስልጠና በልዩነት እንደቀጠለ ነው

መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለሁለተኛ ዙር እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ ስልጠና በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በአለመግባባት ሲቀጥል፣
በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ተማሪዎች በመሰላቸት ውይይቶችን እንደማይከታተሉ ከተሳታፊዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
የተለያዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ተማሪዎች  ውይይቱ አሰልቺ በመሆኑ አብዛኛው ተማሪ የግሉን ስራ እንደሚሰራና ውይይቱን እንደማይከታተል ገልጸዋል።
ለመምህራን በሚሰጠው ስልጠና ደግሞ በአንዳንድ የማሰልጠኛ ቦታዎች መምህራን ሃሳብ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አሰልጣኞች ግፊት ሲያደርጉ እንደነበር ሰልጣኝ
መምህራን ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት በነበረው ስልጠና ተማሪዎች ጥያቄዎችና ቅሬታዎችን ሲያቀርቡ አሁኑኑ ካልተፈታ የማለት አካሄድን እንዳይከተሉና ትክክለኛ የትግል ስልት እንዲከተሉ መመከራቸው
ይታወሳል።
በማወያያ መመሪያው ላይ «ተማሪዎች የሚያቀርቡዋቸው ጥያቄዎች ተማሪው ትምህርቱን በመልካም ሁኔታ እንዳይማር ማነቆ ሆነው የተጋረጡ ችግሮች እንዲፈቱለትና በዚህም
የመማር ማስተማሩ ሂደት በአግባቡ እንዲከናወን ካለው የኃላፊነት መንፈስ በመነጨ መሆን ስለሚኖርበት ጥያቄዎቹ በዚህ መንፈስ የተመረጡ ሊሆኑ  እንደሚገባ ያስቀምጣል፡፡
አያይዞም ጥያቄዎቹ ሲቀርቡ ከስሜታዊነት በጸዳ ፣ ተጨባጭ ችግሮቹንና ሊፈቱ የሚችሉበትን አግባብ በሚያመለከት ሁኔታ መሆን እንደሚኖርበት፣ ጥያቄዎቹ ለሚመለከተው
የቅርብ አመራር ከቀረቡ በኃላ አስተዳደሩ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት ዕድል  ሊሰጠው ይገባል ብሏል፡፡
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሁሉም ጥያቄዎች በአንዴ ካልተመለሰ የሚል ያልሰከነ የትግል አግባብ መከተል አስፈላጊም ፣ጠቃሚም አይደለም ሲል ያሳስባል፡፡
ተማሪዎች ከመብት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ምንም ዓይነት የሃይልና የአመጽ መንገድ እንዳይከተሉ የሚያስጠነቅቀውና በከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣናት እንደተዘጋጀ የሚገመተው
ይህ ጹሑፍ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን በጽሑፍ ለአስተዳደሩ እንዲያቀርቡ፣ካልተፈታላቸው ለቦርዱ እንዲያቀርቡ አሁንም ካልተፈታላቸው ተወያይተው ለሁከት ዕድል በማይፈጥር
መልክ በሰላማዊ ሰልፍ መብታቸውን ለማስከበር እንዲንቀሳቀሱ ይመክራል፡፡
ከትክክለኛ የትግል ሰልት ውጭ የሚገኝ ስኬት የለም የሚለው ይህው ለተማሪዎች ውይይት የቀረበው  ጽሑፍ ተማሪዎች የሚያቀርቡት ጥያቄ ትክክልም፣ የተሳሳተም ሊሆን
እንደሚችል ጠቅሶ ጥያቄውን ግን ወደሚመለከታቸው አካላት ለማቅረብ ትክክለኛ የትግል ስልት መከተል የሚያስፈግለው ዓላማን ለማሳካት ብቻ ሳይሆን የግድ መሆን ስላለበት
ነው ሲል ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ይሰጣል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials